Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

ስለ ተሐድሶ ኑፋቄ ..... በወጣትነት ለቀሪ ዕድሜ ሁሉ የሚተርፍ የተሳሳተ ውሳኔ ስለሚወስኑ ሰዎች ....

ስለ ተሐድሶ ኑፋቄ ….. በወጣትነት ለቀሪ ዕድሜ ሁሉ የሚተርፍ የተሳሳተ ውሳኔ ስለሚወስኑ ሰዎች ….

————————–

++ ተሐድሶ ውስጥ የሚገቡ ወጣት ልጆች መዘዙን አልተረዱም ገና፤

++ የዕውቀትም የዕድሜም ውሱንነት ወደ ተሳሳተ መንገድ ያደርሳል፤

++ ውሳኔህን መለስ ብለህ ተመልከት፤

++ “እልህ ሃይማኖት ይሆናል» ነውና በእልህ የተሳሳተ መንገድ አትከተል፤

———————-

በየፌስቡኩ “ተሐድሶ ነን» ብለው ያወጁ ብዙ ሰዎችን ስመለከት ለጋ ዕድሜያቸው ከፊታቸው ላይ የሚነበብ ወጣቶች መሆናቸውን አየኹ። በርግጥ የሚያሰማሯቸው በክፋት ያረጁ ሰዎች መሆናቸውን አውቃለኹ። “ተሐድሶ ሁሉ ወጣት ነው» ማለቴ እንዳልሆነ በደንብ ተረዱልኝ። ስለ ተሐድሶ እና ስለ ተልዕኳቸው ላለፉት 20 ዓመታት በደንብ ጠንቅቄ አውቃለኹ። ገና “ተሐድሶ መናፍቃን» የሚባለው ቃል ሳይታወቅና ምንነታቸው ገና ምሥጢር ከነበረበት ዘመን ጀምሮ ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፈናል። የምናገረው ከዚያን ዘመን ጀምሮ ስለማውቃቸው ጥፍራቸው የዘረዘረ፣ ቀንዳቸው የከረከረ ተሐድሶዎች ሳይሆን ገና በለጋ ዕድሜ ላይ ስላሉት እና በጥቃቅን ነገር ስለተደለሉት ስለ ወጣቶቹ ነው።

————-

ወጣትነት የዋህና አስቸጋሪ ዕድሜ ነው። በእግዚአብሔር ቸርነት ቀና ቀናውን መንገድ ለመሔድ ካልተቻለ በስተቀር በቀላሉ ሕይወት ሊበላሽየሚችለበት “የሁሉን አውቃለሁ» ባይነት ቅራኝነት ያለበት ዘመን ነው። ከሃይማኖት አንጻር ያለውን ብቻ ነው የማነሣው።

በወጣትነት ከዕውቀት እጅግ ጥቂቱን ከማወቃችንም በላይ በተለይ ከሃይማኖት ዕውቀት ደግሞ እጅግ ኢምንቱን ነው የምንረዳው። ባልረጋ እና እሳት በሆነ የወጣትነት ሰውነት ዕውቀት መንፈሳዊ ለማደርና ለመኖር ብዙ ትቸገራለች። በዚያ ላይ የአውቃለኹ ባይነት እሳት ስናነድድባት ደግሞ ሕይወታች በድንቁርና ጨለማ የተዋጠች ትሆንና እኛ ግን በብርሃን የተሞላን እንዲመስለን ታደርገናለች።

ከዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ አንዱ ደግሞ በቅጡ ስላልተረዳናት ቤተ ክርስቲያነችን እና በቅጡ ስለማናውቀው ባህላችን የምንወስደው ፈጣን ድምዳሜ እና የምንሄደው የተሳሳተ መንገድ ነው። ወዳጄ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት የሚላት አንዲት ጥሩ አባባል አስታውሳለኹ። “መቸም ከዚህ በፊት የነበሩ አባቶቻችን በሙሉ ያልተገለጠላቸው አዲስ ዕውቀት እና አዲስ መንፈሳዊ ጥበብ በዚህ ዘመን ለእኛ አይገለጥም» የምትል። ቃል በቃል በትክክል ማስታወሴን እንጃ። ሐሳቡን ከተረዳችሁልኝ ይበቃል። (ራሱ ዳንኤል ይጨምርበት)

እንግዲያማ፤ ከቤተ ክርስቲያን ትምህርት ወጥተው በፕሮቴስታንት መሠረተ እምነት የተቃኘ ኦርቶዶክሳዊነት ለሚፈልጉ ሰዎች “በርግጥ እኒያ ሁሉ ቅዱሳን አባቶቻችን እና ቅዱሳት እናቶቻችን ያልተገለጸላቸው አዲስ ዕውቀት» አገኘን ብለው ሲያስቡ መሳሳታቸውን ሊረዱ ይችላሉ። ሌላ ማስረጃም አያሻቸው። እንግዲህ መንገድን መመርመር ነው።

————-

“እልህ ሃይማኖት ይሆናል» እንደሚባለው በእልህ ከያዙት የማይመለሱ ብዙ ሰዎች አሉ። መንገዳቸው የተሳሳተ መሆኑን ያወቁ ሰዎች ቢመለሱ ለእነርሱ ሽንፈት አይደለም። እንዲያውም ከእግዚአብሔር ትልቅ ዋጋ ያገኙበታል። “ተሳስቼ ነበር» ማለት ደካማነት አይደለም። ደካማነት የሚሆነወ በዓለም ሚዛን ለሚመስኑን ሰዎች ብቻ ወን። በእግዚአብሔር ሚዛን ግን ጠንካራነት ነው። ዕድሜ ለንስሐ፤ ዘመን ለፍስሐ የሚሰጥ አምላክ በመሳሳታችን ሳይሆን በመመለሳችን እጅግ ይደሰታል። “የሰማይ መላእክት» ጭምር ደስ ይሰኛሉ። ወንጌል እንዳስተማረችን በየሉቃስ ወንጌል 15፥7 “እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።» እንዲሁም በምዕ. 15፥10 “እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።» መላእክት ጭምር የሚደሰቱበት ተግባር ጥፋትን እና ኃጢአትን ማመን ከሆነ ማመኑ ያስከብራል እንጂ አያስነቅፍም።

ይሁን እንጂ ከዚህ የተሐድሶ መንገድ የሚመለሱ ሰዎች በቀላሉ እንዲመለሱ “የማርያም መንገድ» ማዘጋጀት ይገባናል። ተመልሻለኹ ስላለ ተመልሷል ማለት ሳይሆን የተሳሳተውን ነገር አቅርቦ ትክክለኛውን ትምህርት ማግኘቱን ማረጋገጥ፣ ከተመረዘው የኑፋቄ ትምህርት ወጥቶ ርቱዕ የሆነችውን ትምህርት ማግኘቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። መጀረሚያም የወሰደው የተሳሳተ ትምህርት ከሆነ ሲመለስ ደግሞ የተስተካከለ ትምህርት ማግኘት አለበት። ገና ለገና ተመልሷል ብሎ ዐውደ ምህረት ለዐውደ ምሕረት “መስክር» እያሉ ማቆም ከበፊቱ የባሰ ጥፋት ያመጣል።

———

በ1980ዎቹ እና 90ዎቹ “ምስክርነት» በሚባል ፋሽን መሰል የዐውደ ምሕረት ዝግጅት ከሌላ እምነት የመጡ ሰዎች እንዲናገሩ ይደረጉ ነበር። ሰዎቹ ለምን እንደመጡ ሳያውቁ፣ ትክክለኛውን ትምህርት ሳይማሩ፣ ብቻ “መስክር» እየተባሉ ቁጥር አንድ ሰባኪዎች ሆነው ነበር። የሚሰማቸው ሕዝብ እኮ በእምነቱ ያለ ሕዝብ ነው። እነርሱ ናቸው አዲሶቹ። ማነው ለማን የሚነግረው?

—–

አሁንም ቢሆን ሊመለሱ ለሚፈልጉ ሰዎች ትምህርት መስጫ መንገድ መመቻቸት አለበት። ከዕጽ ሱስ ለሚመለሱ፣ ከተለያየ አደጋ ለሚያገግሙ ሰዎች “የማገገሚያ ቦታ፣ Rehabilitation) እንደሚዘጋጀው ሁሉ ከኑፋቄ ድቀት እና ስብራት ለመጠገን ለሚመለሱ ሰዎች ከዚያ ስብራታቸው የሚድኑበት ትምህርትና ሕክምና የሚሰጥበት ቦታ መዘጋጀት አለበት። መምህራን ይህንን ማሰብ አለባቸው። ማጋለጡ ብቻ ዘላቂ መፍትሔ አያመጣም።

—–

አሁን ጥሪዬ ገና በለጋ ዕድሜያቸው ዘማሪ፣ ሰባኪ ተብለው በፋሺንም መልክ ይሁን በጓደኛ ጉትጎታ ለ”አገልግሎት» ብለው ሳያውቁት የቤተ ክርስቲያን ጠላት ለሆኑት ልጆች ነው። አሁን በለጋነታችሁ የወሰናችሁት ውሳኔ በዕውቀትም በዕድሜም ስትጎለምሱ፣ ከሁሉም በላይ በእግዚአብሔር ቸርነት በቃሉ ወተት ስታድጉ የምትፀፀቱበት ስለሚሆን አሁን መንገዳችሁን ቆም ብላችሁ ተመልከቱ። ራሳችሁን ለመመልከት እንዳትችሉ ያላችሁበት ማዕበል ፋታ ስለማይሰጣችሁ ለጻድቁ ኢዮብ እንደተባለው “ይህን ስማ፣ ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ።» (ኢዮብ 37፥14)። ከዚያ ጊዜ በራሱ ስሕተታችሁን ያሳያችኋል።

———-

[…]

The Rise of Aksum

Zeinab Badawi travels to the little-visited country of Eritrea and neighbouring Ethiopia, to chart the rise of the Kingdom of Aksum. Described as one of the four greatest civilization of the ancient world, Zeinab examines archaeological remains – in both countries – dating from many hundreds of years before Christ. She explains how the Kings of […] […]

The Rise of Aksum

Zeinab Badawi travels to the little-visited country of Eritrea and neighbouring Ethiopia, to chart the rise of the Kingdom of Aksum. Described as one of the four greatest civilization of the ancient world, Zeinab examines archaeological remains – in both countries – dating from many hundreds of years before Christ. She explains how the Kings of […] […]

Ambassador Garment on Expansion Spree

As part of expansion of its investment portfolio, Ambassador Garment and Trade PLC is restructuring its well-established business, and unveiled a plan the previous week to invest close to 350 million birr that will go to the setting up of a new plant, which will lie at 25,000 sqm of land at Gelan, Oromia Regional […] […]

Ethiopia Real Estate: High-End, High in Demand

Back when the government announced the 40/60, 20/80 ad 10/90 housing schemes to address the ever-expanding demand for residential houses in Addis Ababa and large cities, the kind of turnout, which was expected at Commercial Bank of Ethiopia, although high, did not match what was actually seen on the ground. All three programs saw interest […] […]

“ለኢህአዴግ ነገሮች እየከበዱ ነው” ኦባንግ

“እነሱ (ምዕራባውያን) ገፍተው የገደል አፋፍ ላይ ቢያስቀምጡህ እንኳ ክፉ ቃል አይጠቀሙም። በተግባር ግን ያሳያሉ። በጀት ሲቀንሱ ምልክት ነው። የጦር ካምፓቸውን ሲያነሱ ምልክት ነው። ፊት ሲነሱ ምልክት ነው። ከሶማሌ እንዳትወጣ እያሉ ሲለምኑና ዶላር ሲያፈሱ ኖረው የራስህ ጉዳይ ካሉህ ትልቅ ምልክት ነው። መከርንህ፣ ነገርንህ አሁን የራስህ ጉዳይ ነው፣ ለራስህ እወቅ፣ ሁሉም ነገር ባንተ እጅ ነው ሲሉህ ምልክት […] […]

የፓርላማ አባላት በድንገት ከዕረፍት ተጠሩ

ዋዜማ ራዲዮ- የሙስና ተጠርጣሪዎች ቁጥር በየዕለቱ እያሻቀበ ባለበት በአሁኑ ወቅት ለእረፍት የተበተኑ የፓርላማ አባላት በሚቀጥለው ሳምንት መጀመርያ ወደ መዲናው ገብተው ሪፖርት እንዲያደርጉ በምክትል አፈጉባኤዋ መታዘዛቸው ታውቋል፡፡
ፓርላማው በዚህ ጥድፊያ ለምን እንደተጠራ ባይታወቅም ምናልባት ከሰሞኑ ያለመከሰስ መብቱ የሚነሳ ባለሥልጣን ይኖር ይሆን የሚለውን ግምት አጠናክሮታል፡፡ በሰኔ መጨረሻ የተበተነው ፓርላማ ለመጨረሻ ጊዜ የተመለከተው ጉዳይ ሰኔ 22 ኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ይገባኛል የሚለውን ልዩ ጥቅም በተመለከተ ሲሆን ‹‹በቂ የመወያያ ጊዜ ያስፈልጋል›› በሚል ጉዳዩን ወደ 2010 ማዛወሩ ይታወሳል፡፡
ፓርላማው በመጪው ዓመት የመጀመርያ ወር የመጨረሻ ሳምንት ሥራውን እንደሚጀምር ቢታወቅም አሁን በፍጥነት እንዲሰበሰብ ጥሪ መደረጉ በርካታ መላምቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፡፡ በተለምዶ አብዛኛዎቹ የፓርላማ አባላት በእረፍት ጊዜያቸው ወደመረጣቸው ሕዝብ ተመልሰው ይሄዳሉ ቢባልም ይህ ተግባር በኢህአዴግ አባላትና አጋር ድርጅቶች በተሞላው ሸንጎ እምብዛምም የተለመደ አይደለም፡፡ ይልቁንም ክረምቱን አብዛኛዎቹ የምክር ቤቱ አባላት በገርጂና በፒኮክ በሚገኙ አፓርትመንቶቻቸው ሻይ ቡና እያሉ የሚያሳልፉት ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡
በምን ጉዳይ ለመምከር ምክር ቤቱ በዚህ ጥድፊያ ጥሪ ሊያስተላልፍ ይችላል በሚል በዋዜማ የተጠየቁ አንድ የቀድሞ የምክር ቤት አባል ምናልባት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በ4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያበቃው እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በኦገስት 9፣ 2017 መሆኑ ይታወቃል፡፡

The post የፓርላማ አባላት በድንገት ከዕረፍት ተጠሩ appeared first on Wazemaradio.

[…]

Moroccan Football Legend Abdelmajid Dolmy Dies

Rabat – Moroccan football legend Abdelmajid Dolmy died on Thursday in Casablanca. He was 64 years old. The cause of his sudden death is still unclear, but according to media reports, Dolmy succumbed to a heart attack. The news of his death spread quickly on social media with several thousands of Moroccans sharing it on […] […]

“በምኒልክ ዘመን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኦርሞን ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ትሰቅል ነበር (የወያኔ ካድሬ አምቦ)”። ለሚለው መስፍን ፈይሳ ሮቢ የሰጠው መልስ – ( መደመጥ ያለበት)።

ሐምሌ 22 ቀን 2009 ዓ.ም.

አዲሱ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ “በምኒልክ ዘመን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኦርሞን ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ትሰቅል ነበር (የወያኔ ካድሬ አምቦ)”። ለሚለው መስፍን ፈይሳ ሮቢ የሰጠው መልስ – ( መደመጥ ያለበት)።

መስፍን ፈይሳ ሮቢ ወያኔ ል 40 ዓመት ያካሄደውን …

[…]

በጉጂና በአማሮ ነዋሪዎች መካከል ለተነሳው ግጭት ተጠያቂው የሕወሓት አገዛዝ መሆኑ ተገለፀ ።

በጉጂና በአማሮ ነዋሪዎች መካከል ለተነሳው ግጭት ተጠያቂው የሕወሓት አገዛዝ መሆኑ ተገለፀ ። Minilik Salsawi

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ የተነሳው ግጭት እጅግ አሳሳቢም መሆኑን በአከባቢው የሚኖሩ የመንግስት ሰራተኞች ይናገራሉ ። በምዕራብ ጉጂ ዞን በመንግስት ስራ ላይ …

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.