Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው

Photo —FILE

ዋዜማ – ሕወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገ – ወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑን ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች ያሰባሰበችው መረጃ ያመለክታል።

ከሁለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፈረመው ሕወሓት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን ብልፅግናን በመቀላቀል በሀገራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት መስማማቱን ቢገልፅም ፓርቲውን ለመቀላቀል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።

ከብልፅግና በፊት የነበረው ኢሕአዴግ እኩል የስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውክልና ያላቸው አራት ንዑስ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሆን ብልፅግና ግን አንድ ወጥ ፓርቲ ነው። የብልፅግና የፓርቲ ውክልና በህዝብ ብዛት የሚወሰን እንጂ እንደ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እኩል ውክልና አይኖራቸውም።

አሁን እየተደረገ ባለው ድርድር ሕወሓት የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-ደንብ ተሻሽሎ በፓርቲ ውስጥ አባል ድርጅቶች እኩል የማዕከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ ውክልና እንዲኖራቸው ይፈልጋል። ብልፅግና ግን ሕወሓት የተናጠል ህልውናውን አክስሞ ብልፅግናን እንዲቀላቀልና ውክልናውም በትግራይ ህዝብ ቁጥር ልክ የሚወሰን መሆኑን ይገልፃል።

የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር የጀመሩት ሲሆን ከሁለት ሳምንት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው በጉዳዩ ላይ በስፋት ተነጋግረዋል።

በሕወኋት በኩል ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው …አስፈላጊም አይደለም” ብለው የሚያምኑ አመራሮች ቢኖሩም፣ ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው፣ በተለይም የትግራይን ፀጥታና ደህንነት ለመስጠበቅ ከብልፅግና ጋር አብሮ መቆም አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑም አሉ።

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ዝርዝር ለማንበብ ይህን ማስፈጠሪያ ተጭነው ለቤተኛ አንባቢዎቻችን ያዘጋጀነውን ማመላከቻ ያንብቡ

The post ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው first appeared on Wazemaradio.

The post ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው appeared first on Wazemaradio.

Source:: https://wazemaradio.com/%E1%88%95%E1%8B%88%E1%88%93%E1%89%B5-%E1%89%A5%E1%88%8D%E1%8D%85%E1%8C%8D%E1%8A%93%E1%8A%95-%E1%88%88%E1%88%98%E1%89%80%E1%88%8B%E1%89%80%E1%88%8D-%E1%89%A0%E1%8B%B5%E1%88%AD%E1%8B%B5%E1%88%AD/?utm_source=rss&utm_medium=rss&utm_campaign=%25e1%2588%2595%25e1%258b%2588%25e1%2588%2593%25e1%2589%25b5-%25e1%2589%25a5%25e1%2588%258d%25e1%258d%2585%25e1%258c%258d%25e1%258a%2593%25e1%258a%2595-%25e1%2588%2588%25e1%2588%2598%25e1%2589%2580%25e1%2588%258b%25e1%2589%2580%25e1%2588%258d-%25e1%2589%25a0%25e1%258b%25b5%25e1%2588%25ad%25e1%258b%25b5%25e1%2588%25ad

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.