ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) አንድ ወር ገደማ “በር ዘግቶ” ካካሔደው ግምገማ በኋላ ሊቀ-መንበሩን አቶ አባይ ወልዱን በዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ተክቷል። ፓርቲው ባወጣው መግለጫ “አመራሩ ከገባበት አዙሪት ውስጥ መውጣት አቅቶት[…] […]
|
|||||||
ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) አንድ ወር ገደማ “በር ዘግቶ” ካካሔደው ግምገማ በኋላ ሊቀ-መንበሩን አቶ አባይ ወልዱን በዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ተክቷል። ፓርቲው ባወጣው መግለጫ “አመራሩ ከገባበት አዙሪት ውስጥ መውጣት አቅቶት[…] […] […] […] ከአሜሪካ በኩል የገጠማቸው ጫና ኪም ጆንግ ኡን ሙሉ ትኩረታቸውን የኑክሌር ሚሳኤል ግንባታና ሙከራ ላይ እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ሩሲያ ገለፀች።[…] […] (ኢሳት ዜና–ሕዳር 21/2010)በሔግ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደታቸውን ሲከታተሉ የነበሩት የቦስኒያ ክሮሺያ ጄኔራል በችሎቱ ፊት መርዝ ጠጥተው ሕይወታቸውን አጠፉ። በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ በተፈጸመ የጦር ወንጀል ከዚህ በፊት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸውና[…] […] ቻይና ለሰሜን ኮሪያ ነዳጅ ማቅረቧን እንድታቆም እና “የበለጠ እንድታደርግ” በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክርቤት የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ጠይቋል።[…] […] TPLF Chair Dr Debretsion G/Michael- PHOTO -Fortune ዋዜማ ራዲዮ-በህወሀት ዝግና ምስጢራዊ የማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባዔ የደህንነት ሀላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋና ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አሸናፊ ሆነው ወጥተዋል። ትዕግስትና የመግባባት ችሎታ ለሚያንሳቸው ዶ/ር ደብረፅዮን ዝቅተኛ የካድሬነት ልምዳቸው ተደምሮበት በፓርቲው ውስጥ “ምንም አዲስ ነገር ሊያመጡ አይችሉም” ሲሉ ከወዲሁ ትችት የሚያቀርቡ አሉ። ለመሆኑ አዲሱ የህወሀት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ማን ናቸው? ከመጋረጃ ጀርባ ህወሀት ሰለተነጋገራቸውና ውሳኔ ስላሳለፈባቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ለምን ሸሸገን? ቻላቸው ታደሰ የሚከተለውን ፅፏል ተጨማሪ የድምፅ ዘገባ ከግርጌ ያገኛሉ ኢሕአዴግ መራሹ መንግስት በህዝባዊ አመጽ እና እያደገ በመጣ ብሄር ግጭት በተጠመደበት ሰዓት ካንድ ወር ለበለጠ ጊዜ መቀሌ ላይ ስብሰባ ተቀምጦ የከረመው የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን ዶክተር ደብረ ፂዮን ገብረ ሚካዔልን በሊቀመንበርነት፣ ወይዘሮ ፈትለ ወርቅ ገብረ እግዚያብሄርን ደሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መምረጡን አስታውቋል፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ዶክተር ደብረጺዮንን ሊቀመንበር አድርጎ የመረጠው እንግዲህ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የሕወሃት ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ አባይ ወልዱን በግምገማ ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ካሰናበተ በኋላ ነው፡፡ ህወሀት በሀገራዊ አጀንዳ ላይ ለምን ለብቻው ይነጋገራል? ሕወሃት ለመንግስት አዳዲስ ፖሊሲዎች እና ለሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ይዞ የመምጣቱ ዕድል አነስተኛ ቢሆንም ላለፉት ሦስት ዐመታት ያሳየውን ድርጅታዊ መዳከም ግን በመጭው መጋቢት በሚካደው የኢሕአዴግ ጠቅላላ ጉባዔ አሻሽሎ ለመቅረብ ሲዶልት እንደከረመ መገመት አያስቸግርም፡፡ በርግጥም የዋዜማ ምንጮች እንዳሉት ሥራ አስፈጻሚው በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም የአመራር ብቃት ላይ ተወያይቶ ሁነኛ ውሳኔ ላይ ደርሶ ከሆነ በቀጣዩ መጋቢት በሚካሄደው የኢሕአዴግ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የኢሕአዴግ ሊቀመንበርነቱን እና የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታውን መልሶ ለመያዝ የማሰቡ ነገር ጨርሶ ዝግ አይደለም፡፡ እናም ከመጋቢቱ የኢሕአዴግ ጉባዔ በፊት ወይ በጉባዔው ወቅት ኦሕዴድ እና ብአዴን በጋራ ወይም በተናጥል በፖለቲካ ስልጣን እና ሃብት ክፍፍል ረገድ ሁነኛ አቋም ይዘው ብቅ ካላሉ እና የሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታም ባለበት ከቀጠለ ሕወሃት በቀጣዩ ምርጫ በትምህርት የላቁትን ዶክተር ደብረጺዮንን ለጠቅላይ ሚንስትርነት ይዞ ሊቀርብ ይችላል፡፡ የዶክተር ደብረፂዮን ስውር መሰላል በድርጅቱ ከያዙት ሃላፊነት አንጻር ዶክተር ደብረፂዮን ሊቀመንበር መሆናቸው ባይደንቅም ሰውዬው ግን ለፖለቲካ የሚመጥን ልምድም ሆነ ተፈጥሯዊ ጠባይ ስለሌላቸው በብዙ ወገኖች ዘንድ ግርምት መፍጠሩ አልቀረም፡፡ ደብረ ፂዮን በበረሃ ትግል ወቅትም በሕወሃት ሬዲዮ ጣቢያ በቴክኒኩ ዘርፍ እንጂ በካድሬነቱም ሆነ በድርጅት ፖለቲካዊ አመራር ልምድ ያላቸው ሰው አይደሉም፡፡ ከ1983 ጀምሮ ደሞ ለረዥም ዐመታት በደኅንነቱ መስሪያ ቤት ውስጥ ከአቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ በተጨማሪ የሟቹ ክንፈ ገብረ መድኅን ምክትል ሆነው ሲሰሩ ስለኖሩ አብዛኛው ልምዳቸው ከደኅንነት ሙያ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በደኅንቱ መስሪያ ቤት ውስጥም የመሠረታዊ ደኅንነት ኪነ ሙያ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በማቋቋም በሃላፊነት መርተዋል፡፡ ማሰልጠኛው ነባሮቹን የደህንነቱ ባልደረቦች እና አዳዲስ የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችን ተቀብሎ ለጥቂት ዐመታት ማሰልጠን ጀምሮ የነበረ ቢሆንም የኋላ ኋላ ግን ተቀዛቅዟል፡፡ አባይ ወልዱ በክልል ፕሬዝዳንትነት ይቀጥላል? አሽናፊው አንጃ The post ህወሀት ውሳኔዎቹን ለምን ሸሸገን? ለምሳሌ ስለኤርትራ! appeared first on Wazemaradio. […] በቤሩት በቤት ውስጥ ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች ወጣት ባልና ሚስት አስሪዎቿ ላይ አደጋ አደረሰች በሚል ተከሳ ፍርድ ቤት ቀርባለች።[…] […] ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) ሊቀመንበር ሆኑ። ሕወሓት ለአንድ ወር ያካሄደውን ግምገማ ማጠናቀቁንም ለፓርቲው ቅርበት ያለው የሃገሪቱ የሚድያ አውታር ዘግቧል። ፓርቲው ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄርን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ[…] […] መቀሌ ላይ ሲሰዳደቡ የቆዩት የበረሃ ወንበዴዎች ደብረጽዮንን መሪያቸው አድርገው በመምረጥ የፈትለወርቅን ዋና መሪነት ውድቅ አድርገዋል። ይህ ለስብሃት ነጋ ሽንፈት የሆነው ክስተት በአዜብ ላይ የተጣለው ዕገዳ እንዲነሳ ወደመቀበል ሊገደድ ይችላል እየተባለ ነው። የኤፈርት ጉዳይ አሁንም አከራካሪ ሆኗል። ከልክ ባለፈ ሁኔታ መቀሌ ላይ ሲወነጃጀሉና ሲሰዳደቡ የቆዩት የህወሓት የበረሃና የድህረ በረሃ ወንበዴዎች በመጨረሻ ላይ የስለላውን ማሽን ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን […] […] […] […] |
News
Political Groups |