Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

First press conference of “Seb Hidri” Civic Association Tigrai (Video)

First press conference of “Sebhidri” Civic Association Tigrai

[…]

የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ሄደው ጠ/ሚ/ር ዓቢይን ለማውረድ ያቀረቡት ጥያቄ ድራማ

ነባርና ታዋቂ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ መታየታቸው በወፍ በረር ሲዘከር መሰንበቱ ይታወሳል። ከሶስት ሳምንት በፊት የህወሓት ሰዎች አሜሪካ ቤት ለመግዛትና ኑሯቸውን ለማደላደል እንደመጡ ተደርጎ ስም እየተጠቀሰ ሲነገርም ቆይቷል። ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ የሆነ የጎልጉል የዘወትር ታማኝ ዲፕሎማት መረጃ አቀባይ ግን ጉዳዩ ሌላ እንደሆነ ነው የሚናገሩት። እንደ ዲፕሎማቱ መረጃ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ድረስ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ […] […]

ሕዝብ ከስሜትና ከተራ ብሽሽቅ በመራቅ በያለበት የአገሩ ዘበኛ ይሁን!

ቀደም ሲል በሃዋሳ፣ ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ በተቀነባበረ ሁኔታ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ፣ በቤኒሻንጉል በተለያዩ ቦታዎችና በተለይም በአሶሳ የደረሰንና እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥራት ጭፍጨፋ፣ ሕዝብ ወደ ምሬት እንዲሄድ ሆን ተብሎ የሚደረግ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ በጥሞና ለምትከታተሉ ሁሉ፤ በባህር ዳር ለጠቅከላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ቀና ተግባርና የለውጥ ሩጫ እውቅና ለመስጠት የተጠራውን ሰልፍ ለማወክ ከወዲሁ ቦንብ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ለሰማችሁ፣ […] […]

የኦጋዴን ነፃነት ግንባር በኦጋዴን የሚደረገውን የነዳጅ ማውጣት ተቃወመ

Ogaden crude oil inauguration at the presence of PM Abiy Ahmed

Ogaden crude oil inauguration at the presence of PM Abiy Ahmed

ዋዜማ ራዲዮ- የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር በሶማሌ ክልል የተጀመረውን ነዳጅ የማውጣት ፕሮጀክት እንደሚቃወምና የኦጋዴን የራስን ዕድል በራስ መወሰን ሳይረጋገጥ የሚደረግ እንቅስቃሴ ህገ ወጥ ዝርፊያ ነው ብሎ እንደሚያምን አስታወቀ።
የኦጋዴን የነዳጅ ጉድጓድ ተመርቆ የሙከራ ስራ በተጀመረ በሰዓታት ውስጥ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክቶቹ የክልሉን ህዝብ ጭቆናና የመብት ጥሰት ሊጋርዱት አይገባም ብሏል።

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ የክልሉ የፖለቲካ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ አለበለዚያ ግን ተግባራዊ መደረጉን አጥብቆ እንደሚቃወም ተናግሯል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የጀመሩት የፖለቲካ ተሀድሶን በበጎ እንደሚመለከት የገለፀው ድርጅቱ የኦጋዴን የራስን ዕድር በራስ መወሰን መብት እንዲከበር ከዚያም በኦጋዴንና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል በሚኖር ስምምነት ብቻ የተፈጥሮ ሀብቱን በፍትሐዊነት መጠቀም ተገቢ ነው ብሎ ያምናል።
ከ 11 ዓመታት በፊት የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር በቻይና የነዳጅ ፍለጋ ስራተኞች ላይ ባደረሰው ጥቃት 63 ኢትዮጵያውያንና 9 ቻይናውያን መገደላቸው ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት በአካባቢው ሚሊሻ በማደራጀትና ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ከፍቶ ነበር። በድርጊቱም ስፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈፀሙ በተደጋጋሚ ተነግሯል።

The post የኦጋዴን ነፃነት ግንባር በኦጋዴን የሚደረገውን የነዳጅ ማውጣት ተቃወመ appeared first on Wazemaradio.

[…]

Leaders of Ethiopia & Eritrea to meet soon

Addis Ababa, June 28, 2018 –Ethiopia and Eritrea will hold a meeting at leaders-level soon, said the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia. Dr Workneh Gebeyehu, Minister of Foreign Affairs said that Prime Minister Dr Abiy Ahmed of Ethiopia and Eritrean President Isaias Afeworki will meet soon. According to him, the visit by the Eritrean delegation […] […]

ጠ/ሚ/ር አብይ ከኪነ ጥበቡ ማህበረሰብ ጋር

ዛሬ ሰኔ 20፣ 2010 ዓ.ም ጠቅላዩ ከአርቱ ማህበረሰብ ጋር በጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 03፡00-05፡30 ድረስ በኪነ ጥበብ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ምንም እንኳ ከባህልና ቱሪዝም ሚ/ር የታደለው የመጥሪያ ደብዳቤ “ሥልጠና” ቢልም፣ ነገሩ ስልጠና ሳይሆን ውይይት ነበር፤ የውይይት ጊዜ ቢያንስም። ዶ/ር አብይ የ”ሰተቴ” እና “እርካብና መንበር” መፃህፍቶች ደራሲ መሆናቸውንም ነግረውናል። የተወሰኑ ኮፒዎችንም በነፃ አድለዋል። እውነቱን ለመናገር […] […]

በአሶሳ በተከሰተው ብሄር ተኮር ጥቃት በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል

Benshangul

  • መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ረፋዱን ወደ ስፍራው ከደረሰ በኋላ ግጭቱ ረግቧል

ዋዜማ ራዲዮ፡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና ከተማ አሶሳ ስኔ 18 ምሽት ላይ የተቀሰቀሰ ብሄር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተባብሶ ለሰው ህይወት መጥፋትና መቁሰል እንዲሁም መፈናቀል ምክንያት ሆኗል።

ከኦሶሳ ሆስፒታል ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው እስካሁን የስምንት ስዎች ህይወት ሲያልፍ በርካታ ስዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፣ በሆስፒታል እየተረዱ ነው።
“የበርታ ማህበረሰብ አባላት የሆኑ ወጣቶች ከጫት ተራ ጀምረው መሀል ከተማ ድረስ ሰው እየደበደቡ ንብረት ሲዘርፉ የክልሉ ፖሊስ ምንም አይነት መከላከል ሳያደርግልን ህዝቡ ወደ በርታ ሲሄድ ፖሊሶች ተኩሰው 3 ሰው በጥይት መተዋል” ሲል የከተማው ነዋሪ ተናግሩዋል።

“ተድበስቦ ነው እንጂ ከበፊትም በርታዎች “ሀበሻ ይውጣ” እያሉ ትንኮሳ ያደርጉ ነበር” ነዋሪዎቹ እንደሚያስረዱት።
ባለፈው ሳምንት የፊት ጭንብል የለበሱ ሰዎች ከተማ ውስጥ ህብረተሰቡን ሲደበድቡ ነበር ብለዋል ነዋሪዎች፡፡

መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ረፋዱን ወደ ስፍራው ከደረሰ በኋላ ግጭቱ ረግቧል ህብረተሰቡንም አረጋግቷል ፡፡
የአሶሳ ማዘጋጀ ሀላፊ አቶ ቶፊቅ አብዱልቀዩም “መጀመሪያ ጠቡ የተነሳው በወጣቶች መሀከል ነው በግጭቱ 3 ሰዎች ሲሞቱ 1 ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት 4 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን 40 ሰዎች በቁጥጥር ስር ሆነው ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው” ሲሉ ነግረውናል፡፡

” አሁኑ ሰአት የሀይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ወጣቱን እያወያዩ ነው” ብለዋል አቶ ቶፊቅ፡፡

የክልሉ መንግስት ሀላፊዎች በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡን በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። የክልሉ የኮምኒኬሽን ቢሮ ጉዳዩ በከፍተኛ ሀላፊዎች መግለጫ ይሰጥበታል ከማለት ውጪ ምላሽ ለመስጠት ሳይፈቅድ ቀርቷል።

The post በአሶሳ በተከሰተው ብሄር ተኮር ጥቃት በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል appeared first on Wazemaradio.

[…]

“ባድመ የኛ አይደለም!” በረከት ስምዖን

በባድመ ጉዳይ የሰሞኑ የህወሓትና የደጋፊዎቹ የማደናገሪያ ጉንጭ አልፋ ሙግት ብዙዎችን ያሰገረመ ከመሆኑ አልፎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድን በፓርላማ በሚያስጠይቅ መልኩ የቀረበ ትዕይንት ሆኖ አልፏል። ራሱ ህወሓት በቆሰቆሰው እሣት የኢትዮጵያን ሕዝብ በ“ድንበር ተደፈረ” ማጭበርበሪያ ካስማገደ እና የፈንጂ ማምከኛ ካደረገ በኋላ አልጀርስ ላይ የአሸባሪና ወንበዴው ህወሓት መሪ በነበረው መለስ ዜናዊ አማካኝነት ባድመን ለኤርትራ አስረክቧል። ከዚያም አልፎ በሌላው […] […]

ኢኤን ኤን (ENN) ቴሌቭዥን ጣቢያ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ ስርጭቱን ያቋርጣል

Enn

ዋዜማ ራዲዮ- ኢኤን ኤን(ENN) ቴሌቭዥን ጣቢያ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ ስርጭቱን አቋርጦ በይፋ ሊዘጋ መሆኑ ተሰማ።
በመጪው አርብ 110 የሚሆኑ ቋሚ ሰራተኞቹን በይፋ ሊያሰናብት መዘጋጀቱንም የቅርብ ምንጮች ነግረውናል።
የኢኤን ኤን ከስርጭት መውጣት ምክንያት የመንግስት መስሪያቤቶች መረጃ ለጣቢያው መስጠት ማቆማቸው አንዱ ሲሆን የአመት ስፖንሰር የሆኑት ኢትዮ ቴሌኮም እና ንግድ ባንድ በድንገት ውላቸውን ማቋረጣቸው የጣቢያውን ገቢ ማሳጣቱን የኢኤን ኤን ምንጮቻችን ለዋዜማ ጠቁመዋል።
እንደ ምንጫችን ጣቢያው ከዳሽን ባንክ በብድር ሊያገኝ የነበረው 500 ሚሊዮን ብር ብድር በብሄራዊ ባንክ ትዕዛዝ እንዲሰረዝ መደረጉን ነግረውናል።

ኢኤንኤን በሀገሪቱ ህዝባዊ ተቃውሞ በተፋፋመበት ወቅት ሁከት አባባሽና “ብሄር ከብሄር ለማጋጨት የሚቀሰቅስ” ዘገባ በማቅረብ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀርቦበት ነበር።
ለዘገባው ሀሰተኛ ምስል መጠቀሙና ዘገባው የተላለፈበት ሰዓት ተዳምረው ጣብያው “ስውር ተልዕኮ አለው” የሚል ውንጀላ እንዲቀርብበት ምክንያት ሆኗል።

ከሕወሐት አመራሮች ጋር የቀረብ ግንኙነት ያለው ኢኤንኤን መቀመጫውን አዲስ አበባ አድርጎ ወቅታዊ ጉዳዮችንና የመዝናኛ ይዘት ያላቸውን ፕሮግራሞች ያቀርብ ነበር።

The post ኢኤን ኤን (ENN) ቴሌቭዥን ጣቢያ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ ስርጭቱን ያቋርጣል appeared first on Wazemaradio.

[…]

ሕወሐት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አመራር ላይ መግባባት አልቻለም

TPLF-leaders

  • የትግራይ ክልል መገናኛ ብዙሀን ኤጀንሲ የአማርኛና የኦሮምኛ የቴሌቭዥን ስርጭት በቅርቡ ይጀምራል

ዋዜማ ራዲዮ- የትግራይን ክልል የሚመራውና እስከቅርብ ጊዜ በሀገሪቱ የፖለቲካ አመራር የፈላጭ ቆራጭነት ሚና የነበረው ሕወሐት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አመራር ላይ ሁለት የተለያዩ አቋሞችን ለማስታረቅ መቸገሩ ተሰማ።

በድርጅቱ በመካከለኛ ሀላፊነት ላይ ያሉና (የለውጥ ሀሳብ ደጋፊ የሆኑ) ሶስት አባላቱ እንደነገሩን አንዳንድ የሕወሐት አመራሮች
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚከተሉት “መርህን ያልተከተለ” የፖለቲካ መንገድ ራሳቸውንም ሆነ ሀገሪቱን ለከፋ አደጋ ያጋልጣታል ብለው ያምናሉ። ሌሎች አመራሮች በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እየሄዱበት ያለው መንገድ ጉድለቶች ቢኖሩበትም በሂደት እያረሙ መሄድ እንጂ ለውጡን መቃወም ከህዝብ ጋር ያላትመናል ብሎም ወዳልተፈልገ የድርጅት መሰነጣጠቅ እንገባለን ብለው ያምናሉ።

ዶ/ር አርከበ ዕቁባይንና ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ በድርጅቱ ተሰሚነት ያላቸው አመራሮች በኢትዮጵያ በመጣው ለውጥ ውስጥ ሀገሪቱን ወደተሻለ መረጋጋትና ስላም በመመለስ ርዕዮተ አለማዊ ልዩነቶችን በውስጠ ድርጅት መድረኮች በማንሳትና በመከራከር አስፈላጊ ከሆነም በማሻሻል መጓዝ አማራጭ የለውም ብለው ያምናሉ።
በርካታ የቀድሞ አመራሮችን በያዘው ሌላኛው ወገን ግን የትግራይ ህዝብና ሕወሐት መስዋዕትነት የከፈሉለት ዓላማ ሲካድና “በህዝበኝነት” ሲተካ ዝም ብሎ መመልከት “የሰማዕታቱን ደም መካድ” ነው ሲሉ ይከራከራሉ።
ሕወሐት የድርጅቱን መስመር ማስከበር ካልቻለ ከገዥው ፓርቲ ግንባር መውጣት አለበት አለበለዚም ይህን የመስመር ክህደት በአደባባይ ልንዋጋው ይገባል የሚል አስተያየት ይሰጣሉ።

ሁለቱም ወገኖች “ትግሬ ጠል” የሆኑ አስተሳሰቦችና ዘመቻዎች መኖራቸውን በመገንዘብ ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስፋት ስራ መሰራት አለበት የሚል ዕቅድ ነድፈዋል።
በዕቅዱ መሰረት በተለያዩ ክልሎችና በዲያስፖራ የሚደረጉ ህዝባዊ ውይይቶች ይኖራሉ።

በትግራይ ህዝብ ላይ የሚነዙ የተዛቡ አመለካከቶችን ለመቀልበስ በማለም የትግራይ ክልል መገናኛ ብዙሀን ኤጀንሲ የአማርኛና የኦሮምኛ የቴሌቭዥን ስርጭት በቅርቡ ይጀምራል።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሕወሐት አመራሮች በተበተነው የወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ ላይ የትግራይ ህዝብ በአዲሱ የፖለቲካ ለውጥ ሳቢያ የገጠመውን ፈተና በፅናት እንደሚታገልና ማናቸውንም ገንቢ ለውጦች እንደሚደገፍ አብራርቷል።
ወጣት የሕወሐት አባላት ግን ድርጅቱ ተተኪ ማፍራት አልቻለም፣ የሀገሪቱን የፖለቲካ ለውጥ የሚመጥን አመራር መስጠት ተስኖታል፣ ስለዚህም ከክልሉ ህዝብ ጋር ስፊ ውይይት በማድረግ ራሱን ከስረ መሰረቱ ካልቀየረ ሕወሐት ታሪክ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

የትግራይ ተወላጅ ሆነው ስለመነጠልና ስለጥላቻ እያወሩ የክልሉን ህዝብ ከቀሪው ኢትዮጵያ የሚያቃቅሩትን መምከርና መገሰፅ አስፈላጊ መሆኑንም ድርጅቱ ያምናል።
ሕወሐት የልዩነት ሀሳቡን ለማስታረቅ ተከታታይ ስብሰባዎችን እንደሚያደርግና በኢህአዴግ መድረኮች ላይም “የአመለካለት ጥራት” እንዲመጣ እታገላልሁ ብሏል።

The post ሕወሐት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አመራር ላይ መግባባት አልቻለም appeared first on Wazemaradio.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.