Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

How to raise our children?

[tubepress video=”WxUGItdRLFs”]

Hannah Godefa

[tubepress video=”gVTkMCr5txc”]

ተተኪ ትውልድ ማፍራት

በዲያስፓራ ለምንኖር ኢትዮጵያን ከፊት የተቀመጠልን ትልቅ የቤት ሥራ ቢኖር ተተኪ ትውልድ ማፍራት ነው፡፡ በሀገር ቤት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተሻለ ትውልድ መቅረጽ እንጂ ተተኪ ትውልድ ማፍራ አጀንዳቸው ላይሆን ይችላል፡፡ኢትዮጵያዊነት ፤ ማንነት ፤ ቋንቋ ፤ ባህል ፤ ሃይማኖትና ሥነ ምግባር በቀላሉ ከማኅበረሰቡ ተምሮ ማደግ የሚቻልበት ሀገር በመሆኑ፡፡ ከጎረቤት፤ ዘመድ አዝማድ፤ ጋደኛ ወዘተ የምንማራቸው የማንነታችን መሠረት የሆኑ ብዙ ዕሴቶች መኖራቸውን ሀገሬን ለቅቄ በባዕድ ሀገር መኖር ስጀምር ነው የተረዳሁት፡፡

በስደት ላለን ኢትዮጵያዊያን ልጅ ማሳደግ ቀላል እንዳልሆነ መናገር ለቀባሪው አረዱት አይነት ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ልጆቼን እይልኝ ገበያ ደርሼ እመጣለሁ ከሚባልበት ሃገር መኪና ስር ቁጭ አድርጎ ዕቃ ማቀበል ወደማይቻልበት ሀገር መምጣት እንዴት አስቸጋሪ አይሁን፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ እኛ ተጨንቀን ለልጆቻችን የማናደርግላቸው እነርሱ ግን አብረዋቸው ከሚያድጉ ሕጻናት ፤ ከቤተሰባቸው ፤ ከጎረቤት ወዘተ የሚማሩት ብዙ ቁም ነገር አለ፡፡ ምን አልባት ልጁ እንዴት ቋንቋ እንደተማረ የማያውቅ ብዙ አባት ይኖራል፡፡ በውጪው ሀገር ግን ይህ ዕድል በቀላሉ የለም ፤ እያንዳንዱን ነገር ከቤተሰብ አሊያም ከቴሌቪዥን መስኮት ነው የሚማሩት፡፡

እንግዲህ ጊዜ የሌለው 16 ሰዓት የሚሠራ ወላጅ ሲሆን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከቴሌቪዥን ወይም ከሚያድጉባቸው ዴይ ኬሮች ይሆናል ማለት ነው፡፡ ወልደው ለባዳ ይላሉ ይሔ ነው፡፡ ከልጅነታቸው ጀምሮ በፈረንጆቹ ቋንቋ አድገው በባህላቸው ተውጠው የሚያድጉ ኢትዮጵያዊያን ልጆችን ቤት ይቁጠራቸው፡፡ እንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ መናገሩን እንደ ሥልጣኔ የሚመለከት ወላጅም ሞልቷል፡፡ ልጆች የእንግሊዘኛውን ቋንቋ መማሪያ ጥሩ መንገድ እንደሆኑ አድርጎ የሀገሩን […]