Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

About

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ሃሳባችንን የምንገልጽባቸው የምናነባቸው ነጻ የዜና ማሰራጫዎች ፤ የመወያያ መድረኮች ፤ የምንጦምርባችው መጦመሪያዎች ማግኘት ቀላል አልነበረም፡፡ እድሜ ለቴክኖሎጂ ዛሬ ዛሬ በየቤታችን ቁጭ ብለን ሃሳባችንን በቀላሉ ማንሸራሸር መንገዶች በዝተዋል፡፡ይህንን ስንል ግን እንደሚጠበቅባቸው አድገዋል ማለት አይደለም፡፡ ለአንድ ሕብረተሰብ ንቃተ ዕሊና ማደግ ትልቅ አስተዋጽዖ ከሚያደርጉ ነገሮች ትምህርት እና ሚዲያ ናቸው፡፡

ያሉንን የዜና ማሰራጫዎች ፤ የመዝናኛ ድረ ገጾች እንዲሁም መጦመሪያዎች ስንመለከት ሦስት ነገሮች እንደሚጎሉ በቀላሉ መረዳት ችለናል፡፡

የመጀመሪያው ትንሽ ቢሆኑም ያሉትን ፈልጎ የማግኘት ፤ አዲስ መረጃን በተቀናጀ መልኩ ማግኘት ነው፡፡ ይህንን ስንል ዛሬ ምን አዲስ ነገር አለ ብሎ ለመፈለግ ያሉትን ድረ ገጾች ሁሉ ፈልጎ ማግኘት ፤ አግኝቶም ገጽ በገጽ መመልከጽ ግድ ይላል፡፡ ሐበሻ 360 ይህንን ቀዳዳ ለመድፈን የተመሠረተች ናት፡፡ ሐበሻን አስመልክቶ የሚወጥ መረጃዎች ያላቸው ድረ ገጾችን ፤ መጦመሪያዎች ፤ የዩቲውብ መረጃዎች በተቀናጀ መልኩ ታቀርባለች፡፡

እነዚህን መረጃዎች በቀላሉ ማግኘት እንዲቻል በዝርዝሩ ውስጥ አልተካተተም የሚሉትን ድረ ገጽ በቀላሉ የሚያስገቡበት ዘዴ በመጀመሪያው ገጽ ላይ አሰናድተናል፡፡

ሁለተኛው እና ዋነኛው ችግር ጡመራን በየቀኑ ወይም በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም በቋሚነት ማከናወን የማይችሉ ነገር ግን ባመቻቸው ጊዜ ለሕዝብ ይጠቅማል ያሉትን መጦመር ለሚፈልጉ መድረክ የሚሆን መጦመሪያ አለመኖሩ ነው፡፡ አቅሙ፤ ጉልበቱ እና እውቀቱ ያላቸው በቋሚነት መጦመር የሚፈልጉ የራሳቸው ድረ ገጽ አዘጋጅተው የሚሰሩትን ሁሉ ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ይህን ማድረግ የማይችሉ ባመቻቸው ጊዜ እንዲጽፉ እና በውስጣቸው ያለውን እምቅ ሃሳብ እንዲተነፍሱ ሐበሻ 360 ታስፈልጋቸዋለች፡፡ በሐበሻ 360 ተመዝግበው በቀላሉ መጦመር ይችላሉ፡፡

ሦስተኛው የአንድ ማሕበረሰብን ችግር ፤ እድገት ወዘተ ለመገምገም እና የወደፊት አቅጣጫ ለመወሰን መጠይቅ /ሰርቬይ/ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ መማር ከግምት በቁጥር ወደ ተሰፈረ ደረጃ ማደግ ነውና፡፡ ስለዚህ ሐበሻ 360 ለማሕበረሰባችን የሚጠቅሙ መረጃዎችን ከማሕበረሰቡ ትሰበስባለች ማጠቃለያ ውጤቱን እና ማብራሪያውን ታቀብላለች፡፡