Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

የመንግስት ሰራተኞች ዝቅተኛውን የደሞዝ ወለል እንዲሻሻል ጥያቄ ቀረበ

Daniel Bekele (PhD) head of EHRC-FILE

ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በየአመቱ ሚያዚያ 23 ቀን የሚከበረውን ዓለማቀፍ የላብ አደሮች ቀን አስመልከቶ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የሰራተኞች ዝቅተኛ ደመወዝ ተመን ክፍያ ወለል የሚወስነውን ቦርድ በአስቸኳይ እንዲቋቋም ጠየቀ፡፡

ኮሚሽኑ ቅዳሜ ሚያዚያ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አመሻሹ ላይ ባወጣው መግለጫ በ2012 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክርቤተ ጽድቆ ወደ ስራ የገባው የዝቅተኛ ደመወዝ ተመን፣ እንዲሁም የሰራተኛ ማህበራት መቋቋምን የሚመለከቱ ህግጋት የተካተተበትን የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ እንደመልካም ጅምር እንደሚወስደው በመግለጽ በቀጣይ በአዋጁ መሰረት እንዲቋቋም የሚፈቅደውን የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በአስቸኳይ እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጸድቆ ወደ ስራ የገባው የአሰሪና ሰራተኞች አዋጅ ቦርድ ጉዳዩን በሚከታተለው ሚንስትር ወይም አግባብ ባለው ባለስልጣን የሚሰየሙ አንድ ሰብሳቢ፤ ስለአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ብቃትና ልምድ ያላቸው ሁለት ባለሙያዎች፣ ከአሠሪ ማኅበራት የሚወከሉ ሁለት አባላት፤ ከሠራተኞች ማኅበራት የሚወከሉ ሁለት አባላት እና ከአሠሪዎችና ከሠራተኞች ማኅበራት የሚወከሉ አንድ አንድ ተተኪ አባላት የሚኖሩት የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ እንደሚቋቋም ደንግጓል፡፡

አዋጁ ለሚቋቋመው ቦርድ በስራ ላይ የሚነሱ የሥራ ክርክሮችን ማየት፣ ተከራካሪዎችን የማስታረቅ፣ ትዕዛዝና ውሣኔ የመስጠት፤በማናቸውም የሥራ ቦታ ወይም ድርጅት በሥራ ጊዜ በመግባት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የመሰብሰብና ምስክሮችን የመስማት ወይም ሠነዶች እንዲቀርቡ የማድረግ ወይም በድርጅቱ ውስጥ በማናቸውም ሰው ይዞታ ስር የሚገኙ ሌሎች ዕቃዎችን የመመልከትና በርካታ ሃላፊነቶችን ይሰጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በ2012 ዓ.ም ለበርካታ ወራት ካካሄደው የክትትል ስራ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትላልቅ ኢንዳስተሪያል ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የሚከፈላቸው የክፍያ መጠን መሰረታዊ የኑሮ ደረጃን ለማሟላት በቂ አለመሆኑን እንዳረጋገጠ ገልጿል፡፡

የተለያዩ ጥናቶች መካዳሄቸውን በመጥቀስ በኢትዮጵያ ካሉ ተቀጣሪዎች ውስጥ ቢያንስ ግማሽ የሚሆኑት በድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ በክትትል ስራው የተገኘው ግኝት እንደሚያመላክት ያሳየው የኮሚሽኑ መግላጫ ከዚህ ውስጥ 18 በመቶ የሚሆኑት የከፋ ድህነት ውስጥ እና 31 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ መካከለኛ ደረጃ በሚባል ድህነት ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ላለፉት ሶስት አመታት የቀጠለውና ዘንድሮም የታየው ዋጋ ግሽበት 35 በመቶ መድረሱን በመግለጽ ይህ እየተባባሰ ከመጣው የዋጋ ንረት፣ በአለማቀፍ ደረጃ ከታየው የሸቀጦች የዋጋ መናር፣ የጸጥታ ችግር፣ ድርቅና ፍልስት ጋር ተደማምሮ የምግብ ነክ ሸቀጣቀጦች ዋጋ እንዳሻቀበ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ለሰራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ አለመደረጉ ሁኔታውን እንዳባባሰው ኮሚሽኑ በመግጫው አትቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የኢትዮጵያ ሰራኞች ማህበርና የሌሎች ማህበራት የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲወሰን የሚያነሱትን ሃሳብ እንደሚደግፍ በመግለጽ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን መወሰን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ሰራተኞች ሁሉንም ችግራቸውን ባይፈታም የተስተካከለ የኑሮ ደረጃን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ከሆኑ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች ጋር ተዳምሮ የሚወሰደው እርምጃ ወሳኝ እንደሚሆን ዋና ኮሚሽነር ዳንዔል በቀለ በመግለጫው አመላክተዋል፡፡

በየአመቱ የሚከበረው የሰራኞች ቀን በ2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለ47 ኛ ጊዜ ይከበራል፡፡ [ዋዜማ ራዲዮ]

The post የመንግስት ሰራተኞች ዝቅተኛውን የደሞዝ ወለል እንዲሻሻል ጥያቄ ቀረበ appeared first on Wazemaradio.

[…]

የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የምርመራ ጋዜጠኝነት መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ

EBA Director Mohamed Ibrahim-FILE

ዋዜማ ራዲዮበኢትዮጵያ ግልጽና ተዓማኒነት ያለውና የምርመራ ጋዜጠኝነት በስርዓት ሊመራ የሚችል መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ኢድሪስ ገለጹ፡፡

የዋዜማ ሪፖርተር ከፓርላማ እንደዘገበው የምርመራ ጋዜጠኝነት በጥሩ ስነ-ምግባር እና ቀድሞ በሚታይ አሰራር በጥንቃቄ የሚመራ ካልሆነ ማህበራዊ ፍትህን በማምጣት ፋንታ የግል ጥቅማቸውን ማስከበር ለሚፈልጉ አካላት ያለአግባብ ሊውል ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ዋና ዳሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ከስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም ከህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋር በመሆን ኮሚቴ ተዋቅሮ የምርመራ ጋዜጠኝነት እንዴት ሊመራ እንደሚገባ የሚያሳይ የአዘጋገብ መመሪያ እያዘጋጁ መሆኑን የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤተ የህግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን የ 9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ግምገማ ባደረገበት ሚያዚያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ነው፡

የምርመራ ጋዜጠኝነት በመመሪያና በአሰራር ካልተመራ የታሰበለትን ዓላማ ሊያመጣ ስላማይችልና የሚፈጥረው ችግር ከፍተኛ በመሆኑ፣ እንዲሁም ወደ ምርመራ ጋዜጠኝነት የሚሰማሩ ጋዜጠኞች ተገቢው ጥበቃና ከለላ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ረቂቁ ይህንን አሰራር ሊያግዝ በሚቸል መልኩ እየተዘጋጀ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ረቂቁ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤትን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ሚና ምን መሆን እንዳለበት የሚያመላከት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ረቂቅ መመሪያው ተዘጋጅቶ እንደተጠናቀቀ የሚዲያ ተቋማትን በማሳተፍ ግብዓት ተጨምሮበት ጸድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ.ር አቢይ አህመድ ከሁለት ወራት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አዳራሽ ባደረጉት ንግገር የመገናኛ ብዙሃን የምርመራ ጋዜጠኝነትን በስፋት በመስራት ሌቦችን ማጋለጥ እንዳለባቸው በመጥቀስና የተመወሰኑ ሚዲየዎችን ስም በመጥቀስ የምርመራ ጋዜጠኝነት በስፋት እንደሚሰሩና እያንዳንዱን መስሪያቤትና ኮንትራት እየበረበሩ ማውጣት ይጀምራሉ ማለታቸው ይጣወሳል፡፡

በዚህም የምርመራ ዘጋባ ወቅት ምርመራን ሊያስቆም የሚሞክር ማንኛውም ባለስልጣን ጊዜ አልፎበታል ስራቸሁን በሚታይ መልክ ግልጽ አድርጋቸሁ ስሩ በሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር፡፡ [ዋዜማ ራዲዮ]

The post የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የምርመራ ጋዜጠኝነት መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ appeared first on Wazemaradio.

[…]

ኢትዮዽያ የተቋረጠው የለጋሾችና አበዳሪዎች ድጋፍ እንዲለቀቅላት ተማፅኖ አቀረበች

Ethiopian delegation confer with Samantha Power of USAID – Photo USAID

ዋዜማ ራድዮ- ከአንድ ሳምንት በላይ በዩናይትድ ስቴትስ ቆይታ ያደረገው የኢትዮጵያ መንግስት የልዑካን ቡድን ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ የተቋረጠው የአበዳሪዎችና የለጋሾች ድጋፍ እንዲቀጥል ብርቱ ተማፅኖ ማቅረቡን ዋዜማ ለጉዳዩ ጋር ቅርብ ከሆኑ የለጋሽ ድርጅቶች ምንጮች ሰምታለች

በገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራውን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ የተካተቱበት የልዑካን ቡድን በዓለም ባንክና በዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከተካፈለ በኋላ ከተለያዩ የለጋሽና አበዳሪ ድርጅቶች ተወካዮችና ከአሜሪካ መንግስት የሕዝብ እንደራሴዎች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቶቹ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተሀድሶ ከጫፍ ለማድረስ የለጋሾች ድጋፍ እጅጉን እንደሚያስፈልግና የተቋረጡ ብድሮችና ድጋፎች መለቀቃቸው ሀገሪቱን ወደተረጋጋ መንገድ ለመመለስ ትልቅ ድርሻ እንዳለው የልዑካን ቡድኑ አስረድቷል።

የሰሜኑ ጦርነት በመንግስት ሳይፈልግ ተገዶ የገባበት እንደነበርና ጉዳዩን በሰላም ለመፍታት በመንግስት በኩል ዝግጁነት መኖሩን ገልጸዋል። ይህን የመንግስት ዝግጁነት ለማረጋገጥም የተኩስ አቁም መታወጁን አስታውሰዋል።

ጦርነቱ ካስከተለው ስብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ባሻገር በዓለማቀፍ ደረጃ የተፈጠረው የአቅርቦት መስተጓጎል ኢትዮጵያንም ክፉኛ የተጫናት መሆኑን አውስተዋል።

መንግስት ከዚህ ቀደም የወሰደውን ዓለማቀፍ ብድር አከፋፈል በተመለከተም ሀገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንፃር ተመልክቶ የብድር አከፋፈሉን የጊዜ ሰሌዳ እንዲሻሻል (የዕዳ ሽግሽግ) የማግባባት ስራ የልዑካን ቡድኑ አንዱ የቤት ስራ እንደነበረም ስምተናል።

የልዑካን ቡድኑ በተለይ ከአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት ሀላፊ ሳማንታ ፓወር ጋር በነበረው ውይይት መንግስት ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትንና ያለገደብ እንዲፈቅድ የባንክና የመገናኛ አውታሮችን ሙሉ በሙሉ እንዲከፍት ይህም የአሜሪካን መንግስትን ሙሉ ድጋፍ ለማግኘት መሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ መሆኑ ተገልጦለታል።

የልዑካን ቡድኑ የስብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን ለማሻሻል መንግስት ብርቱ ጥረት እያደረገ መሆኑን ይሁንና በሕወሓት አማፅያን በኩል ተደጋጋሚ ዕርዳታ ማስተጓጎል አጋጥሞ እንደነበረ አስረድተዋል።

በመንግስት በኩል በትግራይ ክልል መስረታዊ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል ፈቃደኝነቱ መኖሩንም ተናግረዋል።

ውይይቱን የተከታተሉ የለጋሽ ድርጅት ወኪል እንደነገሩን የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደም አሻፈረኝ ያለባቸውን ጉዳዮች ሳይቀር በመቀበል በአስቸኳይ የብድርና ዕርዳታ ድጋፍ እንዲደረግለት ቀጥተኛ ጥያቄ አቅርቧል።

ይህ ጥያቄ ከቀረበላቸው አንዷ የአለም የገንዘብ ድርጅት ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጄቫ ናቸው።

የአለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ከኢትዮጵያ ጋር አቋርጧቸው የነበሩ መርሀ ግብሮችን ሊቀጥል እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሯ ክሪስታሊና ጆርጄቫ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ፍንጭ ሰጥተዋል።

የአለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤም) በ2012 አ.ም የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እንዲያደርግና ማሻሻያዎቹ ለሚፈጥሩት ጫና በምላሹ የ2.9 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦት(extended credit facility)እንደሚሰጥ ተስማምተው ነበር።

የብር የውጭ ምንዛሬ ተመንን በፍጥነት ማዳከምም አንዱ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተወሰደ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ነው። ሆኖም ከ2.9 ቢሊየን ዶላሩ ውስጥ 300 ሚሊየን ዶላሩ በአፋጣኝ ከተለቀቀ በኋላ ቀሪው ብድር ሳይለቀቅ ቆይቷል።

የኢኮኖሚ ማሻሻያው እንደሚፈለገው አለመሄድን ለዚህ በምክንያትነት የሚያቀርቡ ቢኖሩም በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ አሜሪካ በአይ ኤም ኤፍ ውስጥ ያላትን የድምጽ ብልጫ ተጠቅማ ጫና በማሳደሯ ነው ብድሩ የተቋረጠው የሚሉ አሉ።

ነገሮች በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ የተራዘመ የብድር አቅርቦት መርሀግብሩ የሚተገበርበት ጊዜ በዚህ አመት ከወራት በፊት በማለቁም አይኤምኤፍ ለወራት በኢትዮጵያ ምንም አይነት መርሀ ግብር ሳይኖረው ቆይቷል።በዚህም ሳቢያ የገንዘብ ተቋሙ ከወራት በፊት ከ2023 በሁዋላ የሚኖረውን የሀገራትን የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ሲያወጣ ኢትዮጵያን ዘሏት እንደነበር የሚታወስ ነው።

ባለፈው ሳምንት ግን የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ባወጣው ትንበያ ኢትዮጵያን አካቶ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በዚህኛው የፈረንጆቹ አመት 2022 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ3.8 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ፣ የዋጋ ንረት አሁንም ከፍተኛ ሆኖ እንደሚቀጥል እንዲሁም የኢትዮጵያ ዕዳ ምጣኔ ከአመታዊ የሀገር ውስጥ አጠቃላይ ምርት አንጻር እየቀነሰ እንደሚመጣ የሚያሳይ ሪፖርት አውጥቷል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የዋዜማ ራዲዮ ምንጮች እንደገለጹልን አይ ኤም ኤፍ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ አንድ ቡድን ልኮ ወቅታዊ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን ገምግሞ የተለያዩ መርሀ ግብሮች የሚቀጥልበት ሁኔታን ያመቻቻል ተብሎ ይጠበቃል።

በአቶ አሕመድ ሽዴ የተመራው የልዑካን ቡድኑ ምንም እንኳን በዋናነት የኢኮኖሚ ጉዳዮችን እንዲያስፈፅም የተላከ ቢሆንም በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል የተለያዩ የአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎችን አግኝቶ ለመነጋገርና የመንግስትን አቋም ለማስረዳት ሞክሯል። [ዋዜማ ራዲዮ]

The post ኢትዮዽያ የተቋረጠው የለጋሾችና አበዳሪዎች ድጋፍ እንዲለቀቅላት ተማፅኖ አቀረበች appeared first on Wazemaradio.

[…]

PROSPECTS OF COLLABORATION IN THE HORN OF AFRICA AND THE RED SEA REGION

By Kidane Alemayehu April 29, 2020 1.Abstract The main purpose and objective of this paper is to identify the main challenges being encountered by the countries and people of the Horn of Africa as well as those adjacent to the Red Sea. It is well known that the region is bestowed by immense natural resources including water, rich soil, oil and a significant geo-political importance. However, it is also recognized for being a region of repeated conflicts and a seemingly ceaseless insecurity. Nevertheless, with the highly encouraging initiatives by the current Ethiopian Prime Minister, H.E./Dr. Abiy coupled, hopefully, with a

The post PROSPECTS OF COLLABORATION IN THE HORN OF AFRICA AND THE RED SEA REGION appeared first on Zehabesha – Ethiopian News, Opinions, Videos and more…24/7.

[…]

BRAD “GOTTA PAY 2 PLAY” SHERMAN CHARGING $$$$ TO SNIPER ATTACK ETHIOPIA

By Alemayehu G. Mariam/ April 27, 2022 Brad Sherman, congressman/politician for/on sale! It has been humorously said the word “politics” is derived from the word “poly” meaning “many”, and the word “ticks” meaning “blood sucking parasites”. Jesse Unruh, the late formidable speaker of the California’s state assembly remarked, “Money is the mother’s milk of politics”. Politics is also said to be the second oldest profession. Brad Sherman (D-CA) is the supreme practitioner of politicks in the tradition of “blood sucking parasites”. He gets paid in the blood money stolen by the terrorist TPLF from Ethiopia for more than a quarter

The post BRAD “GOTTA PAY 2 PLAY” SHERMAN CHARGING $$$$ TO SNIPER ATTACK ETHIOPIA appeared first on Zehabesha – Ethiopian News, Opinions, Videos and more…24/7.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - April 29, 2022

ECX

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX), of items traded on April 29, 2022.

[…]

How Kim’s New Nuclear Capabilities Up the Ante

Katrin Fraser Katz and Victor Cha/FA April 29, 2022 In the early months of 2022, as the world was transfixed by Russian President Vladimir Putin’s war on Ukraine, North Korean leader Kim Jong Un seemed to sense an opportunity. Since the invasion began, he has tested a slew of ballistic missiles, including hypersonic and long-range weapons, with relatively little international scrutiny. Kim’s objective is clear: he aims to develop weapons capable of overwhelming U.S. national missile defense systems. U.S. President Joe Biden’s national security team has been understandably preoccupied with Ukraine, but North Korea’s nuclear missile technology is rapidly advancing

The post How Kim’s New Nuclear Capabilities Up the Ante appeared first on Zehabesha – Ethiopian News, Opinions, Videos and more…24/7.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - April 28, 2022

ECX

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX), of items traded on April 28, 2022.

[…]

Ethiopia, South Sudan Review Implementation of Road Building Agreements

ethiopia-south-sudan-review-road-agreements

Nebil Mahdi, Ethiopia’s Ambassador to South Sudan, has met and discussed with Simon Mijok Mijak, Minister of Roads and Bridges of the Republic of South Sudan, focusing on implementing previously held agreements to interconnect the two Countries by road infrastructures.

[…]

The frontline voices: Tigrayans speak on the realities of life under an insurgency regime

April 28, 2022in Commentary, Foreign Affairs, Foreign Policy Program, In the Media, Latest News, Security studies / counterterrorism By Ann Fitz-Gerald April 28, 2022 Ethiopians of Tigrayan descent, residing both inside and outside of Tigray, have contacted this researcher to request greater scrutiny of grassroots Tigrayan opinion on the ongoing conflict in Northern Ethiopia. These “silenced voices” have been characterized by many Western analysts and English-language media as supportive of the Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF), a vanguard armed group that exercises authoritarian control of both the “Tigray government” and the “Tigray Defense Forces.” Researchers’ access to the Tigray region is carefully controlled by this armed

The post The frontline voices: Tigrayans speak on the realities of life under an insurgency regime appeared first on Zehabesha – Ethiopian News, Opinions, Videos and more…...

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.