Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

Ethiopia: Only Twenty Shades Available in Industry Parks, IPDC

IPDC LOGO

The Industrial Parks Development Corporation (IPDC) announced a significant increase in investment in the country’s industrial parks. Out of a total of 177 shades, 157 are now occupied by investors, leaving only 20 available for new investments.

[…]

Ethiopia to Lift Tariffs for 5,700 Goods

Tarrif One

The Ministry of Trade and Regional Integration revealed that the African Trade Ministerial Council has accepted Ethiopia’s proposal to trade 5,700 goods, constituting 90% of products, within the African Continental Free Trade Area (AfCFTA).

[…]

የትምሕርት ስርዓቱ ስብራት

በእጅጉ የፖለቲካ መዳፍ ያረፈበት የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ሊጠገን የማይችል የሚመስል ስብራት ገጥሞታል። ይህ ስብራት በተማሪዎችና በወላጆች ላይ ከሚያደርሰው ብርቱ ተፅዕኖ ጎን ለጎን ለሀገራዊ ድባቴም ዳርጎናል። የዚህ የትምህርት ስርዓታችን ችግር ምንጩ ምንድነው? ከችግሩ ለመውጣት የሚረዳ የመፍትሄ አማራጭስ ይኖር ይሆን? ዋዜማ በ “ከስምንተኛው ወለል” የስቱዲዮ ውይይት በዘርፉ አንቱ የተባሉ ባለሙያዎችን ጋብዛ አወያይታለች። ተከታተሉት

The post የትምሕርት ስርዓቱ ስብራት first appeared on Wazemaradio.

The post የትምሕርት ስርዓቱ ስብራት appeared first on Wazemaradio.

[…]

የአማራ ክልል እና የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ 

የሕወሓት አጋር የሆነውና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት መፈራረሙን ዋዜማ ስምታለች። በምስጢር የተያዘው ስምምነት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለህዝብ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ዝርዝሩን ያንብቡት

ዋዜማ- የአማራ ክልል መንግሥት እና በትጥቅ ትግል የሚንቀሳቀሰው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) ድርድር ተቀምጠው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ዋዜማ ሰምታለች።

የክልልነት ጥያቄ አንግቦ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዞን የሚንቀሳቀሰው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) እና የክልሉ መንግሥት በተለይ ባለፈው 2015 ዓ.ም ተደጋጋሚ የሰላም ንግግሮችን ሲያደጉ ነበር።

ይሁን እንጂ በአገር ሸማግሌዎች አመቻችነት የተሞከረውን ሽምግልና ታጣቂ ኃይሉ አልቀበልም በማለቱ መስተጓጎሉ የሚታወስ ነው።

ሁለት ጊዜ የተሞከረው የሽምግልና ጥረት ከከሸፈ በኃላ፣ የክልሉ መንግሥት ከታጣቂ ኃይሉ የሰላም ስምምነት ተብሎና ደረጃው ከፍ ብሎ እንዲደረግ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሎ ሁለቱ ወገኖች ተደራድረዋል።

ድርድሩ የተካሄደው አዲስ አበባ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ለስምምነት የበቃው ተደራዳሪ አካላት በተደጋጋሚ ተገናኝተው ሰፊ ንግግር ካደረጉ በኋላ ነው።

ሁለቱ ወገኖች የመጨረሻው ድርድር አድርገው የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ከተደራዳሪዎቹ አንዱ ለዋዜማ አረጋግጠዋል፡፡

በድርድሩ ሁለቱን ወገኖች በማቀራረብ በዋና አደራዳሪነት የተሰየመው፣ መከላከያ ሚኒስቴር መሆኑን ዋዜማ ከድርድሩ ተሳታፊዎች ሰምታለች።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የድርድሩ ተሳታፊ ሰምምነቱ ይፋ የሚደረግበት ጊዜ ምስጢራዊነት አንዱ የስምምነቱ አካል መሆኑን ነግረውናል። የስምምነት ሰነዱን ይዘት በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ምንጩ ምንም እንኳን የሰነዱን ዝርዝር ከመናገር ቢቆጠቡም፣ በጥቅሉ “ለሁሉም በሚጠቅም መልኩ ተስማምተናል” ሲሉ ገልጠውታል። ሰፊ ክርክር የተደረገበት ነው የተባለለት ድርድር እንደ ክልልም ይሁን እንደ አገር ጠቃሚ በሆነ አግባብ ተፈጽሟል ተብሏል።

በተለይም ታጣቂ ኃይሉ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ ሰላም እንደሚፈጥርና ሁለቱን ተሰማሚ ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ምንጩ ጠቁመዋል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውና የሰላም ንግግሩን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ ሌላኛው የዋዜማ ምንጭ፣ ስምምነቱ በአዴን በኩል ትጥቅ መፍታትና ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሸጋገር ላይ የሚያጠነጥን መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ መንግሥት በኩል ደግሞ አዴን ያነገበውን ራስን በራስ የማስተዳደር ብሎም የክልልነት ጥያቄ ማስተናድ የሚሉት ጉዳዮች ዋናዎቹ መሆናቸውን ምንጩ አመላክተዋል።

በአማራ ክልል መንግሥት እና በአዴን መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት በመጭው ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በድርድሩ ላይ ከአማራ ክልል መንግሥት በኩል የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው የመሩት ቡድን ተሳትፏል።

እንዲሁም በአደራዳሪነት በተሰየመው መከላከያ በኩል ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተሳትፈዋል። በዋና አደራዳሪነት የተቀመጠው መከላከያ የሰላም ስምምነቱ ተዋዋይ ወገኖች፣ ያቀረቧቸውን መከራከሪያ ነጥቦች አቀራርቦ የጋራ መግባባት የተደረሰበትን ሰነድ አፈራርሟል።

ባለፈው ዓመት በተደጋጋሚ ሲሞከር የነበረው የሰላም ንግግር በወቅቱ ያልተሳካው፣ ታጣቂ ኃይሉ ከድርድር በታች ያሉ የሰላም መንገዶችን አልቀበልም፣ የምንታገልበትን አላማ በድርድር ማስጠበቅ አለብኝ በማለት ነበር።

በ2013 ዓ.ም የተጀመረው የታጣቂ ኃይሉ እንቅስቃሴ፣ ዋና አላማ አካባቢውን በክልልነት የማደራጀት መሆኑን ሲገልጥ ነበር።

አዴን ዋነኛ አላማውን “የአገው ክልላዊ መንግሥት መመስረት” ነው ብሎ የተነሳ የፖለቲካ ፓርቲ ተገንጣይ ክንፍ ነው። ታጣቂ ኃይሉን የሚመሩት በተፎካካሪ ፖርቲነት በአካባቢው የሚንቀሳቀስው የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ውስጥ እስከ ሥራ አስፈጻሚ አባልነት ሚና የነበራቸው ናቸው።

የዛሬዎቹ የአዴን መሪዎች ከአገው ብሔራዊ ሸንጎ ከተገነጠሉ በኋላ፣ ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጋር ተሰልፈው በሰሜኑ ጦርነት ተሰታፈዋል።

በወቅቱ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ቁርሾ ውስጥ ገብቶ ከነበረው ህወሓት ጋር የተሰለፈው አዴን፣ ከጦርነቱ መቋጨት በኋላ የተወሰኑ የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎችን ይዞ ቀይቷል።

አዴን በፌዴራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል የተፈረመውኝ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አልቀበልም ብሎ መቆየቱ የሚታወስ ነው። በዚህም በትግራይ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ የተወሰኑ በዋግ ኽምራ ዞን ሚገኙ የወረዳ ቀበሌዎችን ተቆጣጥሮ ቆይቷል።

የአዴን አመራሮች በዋናነት መቀመጫቸውን በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ አድረገው ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው የሚታወስ ነው። አጋራችን ከሚሉት ህወሓት ጋርም ያላቸው ግንኙነት በጋራ ተሰልፎ ከመዋጋት የዘለቀ ነበር።

የአዴን ታጣቂ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በዋግ ኽምራ ዞን ሰፊ እንቅስቃሴ የነበረው ቢሆንም፣ በሰላም ስምምነቱ በኋላ በውስን ቀበሌዎች ላይ ተገድቧል።

የሦስት ዓመት ገደማ ዕድሜ ያለው አዴን ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ያለው ቅርበት መሬት የረገጠ እንዳልሆነም ይሰማል። ውልደቱና አብዛኛውን ዕድሜውም ከሰሜኑና የትግራይ ጦርነት ወቅት ጋር የተገናኘ ነው።

አዴን ይዞት የተነሳው አገውን ክልል የማድረግ አላማ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ለማረጋገጥ እንደሆነ ሲገልጥ ይደመጣል።

ዋዜማ የተመለከተችው ስለ አዴን እንቅስቃሴ አላማና መዳረሻ የሚያትተው አስረጅ ማብራሪያ “አገው የብሔር ጭቆናና የግዛት ወረራ ተፈጽሞበታል” ይላል። [ዋዜማ]

The post የአማራ ክልል እና የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ first appeared on Wazemaradio.

The post የአማራ ክልል እና የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ appeared first on Wazemaradio.

[…]

ለዛሬ ታቅዶ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኞች ምዘና ፈተና ተሰረዘ

Adanech-Abebe

ዋዜማ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ ዛሬ ሊሰጠው አቅዶ የነበረው አወዛጋቢው የመጀመሪያ ዙር የብቃት መመዘኛ ፈተና ባልታወቀ ምክንያት መሰረዙን ዋዜማ ሰምታለች።

ለፈተና የተመረጡት ሠራተኞቹ በአውቶቡስ ወደ ፈተና ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ሲጠባበቁ እንደነበር ለዋዜማ ተናግረዋል።

ዳግማዊ ሚኒልክ ት/ቤት የፈተና ጣቢያ ሊፈተኑ የነበሩ አንድ ሰራተኛ የተወሰኑ ሰራተኞች ስም ዝርዝር ብቻ በመፈተኛ ክፍሎች እንደተለጠፈ ለዋዜማ ገልጸዋል። ፈተናው ሊሰጥባቸው በነበሩ ሌሎች ሶስት ቦታዎችም መሰረዙን ከተፈታኞች ስምተናል።

በቦታው ፖሊሶች ብቻ ስለነበሩ ለምን እንደተሰረዘ የሚናገር አካል እንዳልነበርም ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ፣ የብቃት መመዘኛ ፈተናውን የሚሰጠው አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ ጥናት ባደረጉት የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች እንደሆነ ገልፆ ነበር። ስለምዘናው ዝርዝር መረጃ በዚህ ማስፈንጠሪያ ያገኛሉ

በትናትናው ዕለት ተቃዋሚው እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች ሊሰጠው ያቀደው ምዘና እንዲኹም በምዘናው የሚሰጠው የሠራተኞች ምደባ ባስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል።

ፓርቲው፣ ፈተናና ምዘናው መንግሥት የማይፈልጋቸውን ሠራተኞች በማስወገድ የሚፈልጋቸውን ለመተካት ኾን ብሎ ያዘጋጀው ስልት መኾኑን ለመገመት አያዳግትም ብሏል። ከፈተናው በፊት የፈተናው መልስ በየትምህርት ቤቶች አስቀድሞ ተለጥፎ መገኘቱን ከመረጃ ምንጮቹ መረዳቱን የጠቀሰው ፓርቲው፣ ይህን ተከትሎ ፈተናው ለጊዜው መቋረጡን እንደደረሰበት ገልጧል።

ፓርቲው፣ በአዲስ አበባ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እየሠሩ የሚገኙ ሠራተኞች የብሄር ማንነታቸውን እንዲሞሉ የሚያስገድደው ቅጽ ባስቸኳይ እንዲቆምም ፓርቲው ጠይቋል። በዚኹ መግለጫው፣ የከተማዋ አስተዳደር ሠራተኞች የፈተና አሰጣጡን፣ ምደባውንና “ብሄር” የሚጠይቀውን ቅጽ በሰላማዊ መንገድ እንዲቃወሙ ፓርቲው ጥሪ አድርጓል። [ዋዜማ]

To reach Wazema editors, you can write to wazemaradio@gmail.com

The post ለዛሬ ታቅዶ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኞች ምዘና ፈተና ተሰረዘ first appeared on Wazemaradio.

The post ለዛሬ ታቅዶ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኞች ምዘና ፈተና ተሰረዘ appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopia: Omo Bank’s Capital Reaches Birr 1 Billion

OMO Bank

Omo Bank has announced that it had reached a capital of one billion birr, enabling it to provide comprehensive banking services.

[…]

Ethiopia: Adal Industry to Produce Paper from Enset

Paper from Enset

Adal Industry has commenced paper production from enset in Ethiopia, aiming to meet domestic demand and reduce foreign currency spending on paper imports.

[…]

Ethiopia: Ethio Telecom launches Digital Financial Marketplace

Ethio Telecom

Ethio Telecom launched a Digital Financial Marketplace to boost the financial sector and promote inclusion.

[…]

Ethiopian Airlines Secures Loan to Purchase Aircraft

Ethiopian Airlines Logo

Ethiopian Airlines has secured a USD 450 million loan agreement to finance the acquisition of five new Boeing aircraft—three Boeing 737-8 and two Boeing 777F (Cargo).

[…]

Ethiopia: AvtoVAZ and Ethio Engineering Group to Manufacture Lada Cars

LADA EThio

AvtoVAZ, the Russian state-owned automaker, and Ethio Engineering Group have signed a letter of intent to collaborate on manufacturing Lada cars in Ethiopia.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.