Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

African Economic Conference to be Held in Ethiopia

aec-2023-october-1500 617 va

The African Economic Conference (AEC) serves as the primary pan-African platform for addressing emerging economic opportunities and challenges. This year, the conference will take place from November 16-18, 2023, adopting a hybrid format with the physical venue at the UN Conference Centre in Addis Ababa, Ethiopia.

[…]

Ethiopia: Authority Drafts a Petroleum Control Bill

Petroleum and Energy Authority 1

The Ethiopian Petroleum and Energy Authority (EPEA) announced that a petroleum control bill aimed at regulating and overseeing the operations of oil marketing and distribution was being drafted. The bill serves to establish a structured operating system and enable legal and administrative actions against any illicit activities discovered.

[…]

Ethiopia Substitutes USD 350 Million Worth of Imports

MoI Logo

In the first quarter of the current fiscal year, Ethiopia replaced imports amounting to USD 350 million.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - 30 October 2023

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 30 October 2023.

[…]

በምስራቅ ቦረና ተቃውሞ ትምህርትና የጤና አገልግሎት ከተቋረጠ ወራት አስቆጥሯል

Photo- Oromia regional government

ዋዜማ- ከአዲስ አበባ 700 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኘው የምስራቅ ቦረና ዞን በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረ አዲስ የዞን አደረጃጀት ነው።

በተለይም ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ስር ካሉ ወረዳዎች አንዷ በነበረችው ጎሮ ዶላ ወረዳ በየጊዜው በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች እረፍት አልነበራትም፡፡ አስር ወራት ያስቆጠረው ተቃውሞና አለመረጋጋት ወትሮም እንደነገሩ የነበረውን የትምህርትና የጤና አገልግሎት አስተጓጉሎታል።

የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ)መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ሃያ አንደኛ የክልሉን ዞን በማድረግ አዲስ ያዋቀረውን የምስራቅ ቦረና ዞን አደረጃጀት ይፋ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በዞኑ ስር ካሉ 18 ወረዳዎች አንዷ የሆነችው የጎሮ ዶላ ወረዳ “በምስራቅ ቦረና ዞን ስር መካከል አንፈልግም” ያሉ የወረዳዋ ነዋሪዎች ያለማቋረጥ የተቃውሞ ስልፍ እያደረጉ ነው፡፡

ነጌሳ ጎዳና የዕድሜ ባለጸጋ ሲሆኑ በወረዳው ሐረ ቀላ ከተማ ለረዥም ዘመናት የኖሩ አባት ናቸው የጎሮ ዶላ ወረዳ እንደ ወረዳ ከተዋቀረችበት 1994 ዓ.ም ጀምሮ በምስራቅ ጉጂ ዞን ስር ስትተዳደር እንደነበር እና ነጌሌ ቦረና ደግሞ የዞኑ ዋና ከተማ እንደሆነች ይናገራሉ፡፡

የነዋሪዎች ተቃውሞ ዋነኛው ምክንያት የክልሉ መንግሥት ወረዳዋን በአዲሱ የምስራቅ ቦረና ዞን ስር ለማካለል ሲወስን ሕዝቡን አላወያየም የሚል እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

እንዲሁም አደረጃጀቱ ወረዳዋ ከጉጂ ዞን እንዲሁም ከዋና ከተማዋ ከነጌሌ ቦረና ስታገኝ የነበረውን ተቋማዊ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ የሚያቋርጥ በመሆኑ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ተቃውሞውን ሲያሰማ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ሌላ የወረዳው ነዋሪ ጃርሶ ጉዬ በበኩላቸው በየጊዜው በሚደረጉ ተቃውሞዎችም በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ የሚደርሰው ውድመት ከፍተኛ ነው። ለአብነትም ባለፈው ነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም ላይ ድምጻቸውን በሰላማዊ መንገድ ሊያሰሙ በወረዳው ሀረ ቀላ ከተማ የወጡ ከ 2 ሺሕ በላይ ሰዎችን ለመበተን የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ በሰዎች ላይ ሞት እንዲሁም ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ መሆኑን እንዲሁም ከ 2መቶ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ተናግረዋል፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በወረዳው አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩ አመራር እንደነገሩን ደግሞ በዚሁ ተደጋጋሚ ተቃውሞ ምክንያት የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ሥራ ካቆሙ ሦስት ወራት አልፏቸዋል ያሉ ሲሆን የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም እንዲሁ ከቀን ወደ ቀን እየተቀዛቀዘ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡

አሁን እንደ ትምሕርት ቤት፣ጤና ጣብያ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራ እየሰሩ አየደለም በማለት ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም በወረዳው ስር ካሉ 80 አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት እስካሁን የተማሪ ምዝገባ እንኳን አለማድረጋቸው፣ በዚህም ምክንያት 60 ሺህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

የተማሪዎቹ ምዝገባ የዘገየውም በወረዳዋ ያለማቋረጥ በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያት ሲሆን ሰልፉም ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጋር ወደ ግጭት ስለሚያመራ የደህንነት ስጋት ማስከተሉን ነዋሪዎች ይናገራሉ።፡፡

አብዛኛዎቹ መምህራን ከደመወዝ ክፍያ መዘግየት ጋር ተያይዞ ስራ ካቆሙ ወራት መቆጠራቸውን እና ችግሩ እንዲፈታና ተማሪዎች ወደትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ከክልል እስከ ዞን በየደረጃው ላሉ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታችንን ብናቀርብም ችግሩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም ሲሉ የትምህርት ዘርፍ ሀላፊዎች ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ከጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለዋዜማ ያስረዱት የሀረቀላ ጤና ጣቢያ የጤና ባለሙያ ተመስገን ደደቻ በወረዳው ካሉ 5 የጤና ጣቢያውች መካከል አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው በከተማዋ የሚገኘው ሀረቀላ ጤና ጣቢያ ብቻ ነው ያሉ ሲሆን እሱም ቢሆን ከፍተኛ የሆነ የመድኃኒት እና የህክምና ቁሳቁስ እጥረት እንዳለበት አውስተዋል፡፡

ዋዜማ ስለጉዳዩ የጎሮ ዶላ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑትን ጌቱ ጩሉቄን ያነጋገረች ሲሆን ካለው የጸጥታ ስጋት አንጻር አካባቢው ላለፉት አምስት ዓመታት በኮማንድፖስት ወይም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር እንደምትተዳደር ገልፀዋል፡፡

ምንም እንኳን ወረዳዋ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ብትተዳደርም በየጊዜው “ማን እንደጠራው የማይታወቅ” ሰልፍ ይደረጋል ለዚህም ሲባል የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ሰልፉን ለመበተን በሚወስዱት እርምጃ በሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በወረዳዋ በተለይም “የተለየ ተልዕኮ ያላቸው” ወጣቶች በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፉን ሲያያደርጉ መንገድ ከመዝጋት ጀምሮ ተሽከርካሪዎችን ማቃጠል፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ ጥቃት ማድረግ እና ሌሎችንም ተግባራትን ሲፈጽሙ ተስተውሏል ብለዋል፡፡

አካባቢው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ለዓመታት ሲንቀሳቀስበት የነበረና አሁንም የሚንቀሳቀስበት እንደሆነ የገለጹት ጌቱ ለዚህም ሲባል በኮማንድ ፖስት ስር እንድትተዳደር መደረጓን አብራርተዋል፡፡

አስተዳዳሪው አክለው እንደተናገሩት በወረዳው ችግሮች ከዕለት ወደዕለት እየተባባሱ መጥተዋል በማለት ለዚህም መፍትሄ የሚሆነው ተቀራርቦ መነጋገር ብቻ ነው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጃርሶ ቡሌ በበኩላቸው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከስምንት ወራት በፊት ይፋ ባደረገው አወቃቀር መሰረት በጉጂ ዞን ሥር የነበሩ ጎሮ ዶላን ጨምሮ ዱብሉቅ፣ ኦቦርሶ፣ አሬር፣ ዋጪሌ እንዲሁም ቦርኖርን የመሳሰሉ ወረዳዎች በአዲሱ አደረጃጀት ወደ ምስራቅ ቦረና ዞን መካለላቸውን አስረድተዋል፡፡

ይህም “የጉጂ ሕዝብ ከሃያ ዓመታት በላይ ሲጠይቀው የነበረ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነው።” በማለት ወረዳዎቹ ወደ ምስራቅ ቦረና ዞን መካለላቸው ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለው በክልሉ መንግሥት ስለታመነበት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አሁንም አልፎ አልፎ የሚታዩ አመጾች ከዚህ በላይ ዋጋ እንዳያስከፍሉ ከአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በየደረጃው ካሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ጋር ተከታታይ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይም የአከባቢው ማኅበረሰብ ለዘመናት ሲጠቀምቀት የነበረውን “ጃርሱማ” የተሰኘ በአገር ሽማግሌዎች የሚመራ ባሕላዊ የግጭት አፈታትን ዘዴን በመጠቀም የመንግሥት አካላት ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀራርበው ለመነጋገር እና ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ [ዋዜማ]

ዋዜማ ይህን ዘገባ ያቀረበችው በኢንተርኒውስ የገንዘብ ድጋፍ ታግዛ ነው

The post በምስራቅ ቦረና ተቃውሞ ትምህርትና የጤና አገልግሎት ከተቋረጠ ወራት አስቆጥሯል first appeared on Wazemaradio.

The post በምስራቅ ቦረና ተቃውሞ ትምህርትና የጤና አገልግሎት ከተቋረጠ ወራት አስቆጥሯል appeared first on Wazemaradio.

[…]

በቦረና ዞን ተከስቶ በነበረው ድርቅ ሳቢያ ተፈናቅለው በመጠለያ ያሉ  ዜጎች ለከፋ ፆታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል

Photo- Reuters

ዋዜማ- ለተከታታይ አምስት ዓመታት ዝናብ በመስተጓጎሉ በተከሰተ አስከፊ ድርቅ ከ 300 ሺሕ በላይ የቦረና ዞን ነዋሪዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚሁ ተፈናቃዮች ግማሽ ያህሉ ሴቶች ናቸው፡፡

በዞኑ ትልቁ ወደ ሆነው እና ከ 10 ሺሕ በላይ አባወራ ወይም ከ60 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች ወደሚገኙበት ዱብሉቅ የተፈናቃዮች መጠለያ በማቅናት ዋዜማ ቅኝት አድርጋለች፡፡

በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ በሚገኙ ሴቶች ላይ በተደጋጋሚ ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን እና እስከአሁን ድረስ የተመዘገበ 71 የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መድረሱን የዱብሉቅ የተፈናቃዮች ጣቢያ ተጠሪ አወሉ ዋቆ ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡

በባህል ተፅዕኖና ህፍረት ሳቢያ የጉዳቱ ሰለባ ሆነው ችግራቸውን ያልተናገሩ በርካታ ተጎጂዎች በመኖራቸው ቁጥሩ ከፍተኛ እንደሆነ መገመት እንደሚቻል የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኞች ነግረውናል። ወንጀለኞችን ለይቶ ለሕግ ለማቅረብ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡

በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የሚፈጸምባቸው አብዛኛዎቹ ሴቶች እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ እና ለአቅመ ሔዋን ያልደረሱ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡

ችግሩን እጅግ ውስብስብ ያደረገው በመጠለያ ጣቢያው በሚገኙ ቤቶች ውስጥ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የማይተዋወቁ ሰዎች በመኝታ ሰዓት ጭምር በአንድ ላይ ስለሚተኙ ሴቶቹ ለጾታዊ ጥቃቱ ተጋላጭ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡

ጥቃቱ የደረሰባቸው ሴቶች ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እና ላልተፈለገ እርግዝና ሊጋለጡ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት መኖሩን አውስተዋል፡፡

በሌላ በኩል ጥቃቱ የደረሰባቸው ተለይተው የሚታወቁ ሴቶችን አካላዊ እና ስነልቦናዊ ክትትል ማግኘት እንዲችሉ በአቅራቢያው ምንም አይነት የጤና ተቋም አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡

ኃላፊው አክለው እንደገለጹት አስገድዶ መድፈር ብቻ ሳይሆን በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ተፈናቃዮች አብረው ከመኖራቸው የተነሳ ያለ ዕድሜ ጋብቻን የመሳሰሉ ተግባራት ሲፈፀሙ መስተዋሉን ጠቁመዋል፡፡

ይህም የሆነው ቀድሞም በአካባቢው እንደዚህ አይነት ተግባር በማኅበረሰቡ ዘንድ እንደ ባሕል ይታይ ስለነበረ በመጠለያ ጣቢያው ውስጥም ይህንኑ ተግባር ሊፈጽሙ መቻላቸው አውስተዋል፡፡

ይህንንም በማስመልከት ድርጊቱ ጎጂ እንደሆነ ለማስገንዘብ ከተፈናቃዮች ጋር ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ አዘጋጅተው እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ከጾታዊ ጥቃቱ በተጨማሪ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ(ሞዴስ) እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንደሌሉ የተናገሩ ሲሆን ተፈናቃዮቹ አሁን ባሉበት ሁኔታ ስለንፅህና መጠበቂያ ማሰብ ቅንጦት ነው የሚሆነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በወር አበባ ጊዜ ለከፍተኛ ሰቀቀን እና ጭንቀት እንደሚዳረጉ ለማወቅ መቻሉን ኃላፊው አውስተዋል፡፡

ድርቁ በተከሰተበት እና ሰዎች ወደ መጠለያ ጣቢያው እየገቡ በነበረበት ወቅት በመንግሥት፣በረድኤት ድርጅቶች፣በግለሰቦች እና በሌሎች በጎ አድራጊ ተቋማት ሲደረግ የነበረው ድጋፍ መልካም እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በወቅቱ ለዕለታዊ ፍጆታዎች የሚውሉ የምግብ ግብዓት፣ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ እና ሌሎችም በበቂ ሁኔታ የነበሩ ቢሆንም አሁን ድጋፉ መቀዛቀዙን ያስረዱት ኃላፊው በዚህም ምክንያት በተለይም በሴት ተፈናቃዮች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የዞኑ አደጋ ስጋት መምሪያ ኃላፊ ሊበን ሳራ እንደተናገሩት በዞኑ ከ300 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ እንደሚገኙ ያስረዱ ሲሆን በርካቶቹ ኤልወያ እና ዱብሉቅ በተሰኙ ጣቢያዎች ውስጥ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡

ከሁሉም በተለየ በዱብሉቅ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በሚገኙ ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት እንደሚፈጸም ሪፖርቶች ይደርሱናል በማለት ገልፀዋል፡፡

ችግሩ በዋናነት የቤቶቹ ጥበት እና የማይተዋወቁ ስዎች ጭምር በአንድ ላይ መተኛታቸው እንደሆነ በመግለፅ ለዚህም ቤቶቹን አስፍቶ ለመስራት እና የመኝታ ቦታዎቻቸውን ለመለየት በመምሪያው በኩል ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ከጾታዊ ጥቃቱ በተጓዳኝ የሰብዓዊ ድጋፍ መቀዛቀዝ ተፈናቃዮችን ለረሀብ እና ረሃቡ ላስከተለው በሽታ እየዳረጋቸው እንደሚገኝ ሊበን አብራርተዋል፡፡

አብዛኛው የአካባቢው ማኅበረሰብ አርብቶ አደር በመሆኑ እና ድርቁ ባስከተለው ረሀብ እንሰሳቶቻቸው ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በማለቃቸው ወደመጡበት የመመለስ እና መልሶ የማቋቋሙን ስራ እጅግ ፈታኝ አድርጎታል፡፡ በዱቡሉቅ ወረዳ ብቻ ከ43 ሺሕ በላይ የቀንድ ከብቶች በድርቁ ምክንያት መሞታቸውን ገልፀዋል፡፡

ለተፈናቃዮቹ መጠነኛ ድጋፍ ሲያደርግ የነበረው ጆፕ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት እንደነበር የገለጹ ሲሆን እሱም ቢሆን አሁን ላይ በአካባቢው ካለው የጸጥታ ስጋት አንጻር ድጋፉን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ካቆመ ሰንብቷል ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ እየተደረገላቸው ስለነበረው ድጋፍ ለዋዜማ ሲያስረዱ ለአንድ አባወራ የሚደርሰው ዱቄት ከአስር ጣሳ የማይበልጥ መሆኑን በመግለፅ ይህ ደግሞ ለሁለት ቀን የምግብ ፍጆታ እንኳን በቂ እንዳለሆነ አውስተዋል፡፡

ከትምህርት ጋር ተያይዞ የተፈናቃዮቹ ቁጥር ካለው የትምህርት ቤት የመቀበል አቅም ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ በትምህርት ገበታ ላይ ያልሆኑ ልጆች በርካታ መሆናቸውን ወላጆች ገልጸዋል፡፡

የዞኑ አስተዳደር እና አደጋ ስጋት መምሪያ ችግሩን ለመፍታት እና ተፈናቃዮቹ ከመጠለያ ጣቢያው ወጥተው ወደቤታቸው የሚመለሱበትን ሆኔታ ለመፍጠር አቅደው ወደ ስራ መግባታቸውንም ጠቁመዋል፡፡ [ዋዜማ]

ዋዜማ ይህን ዘገባ ያቀረበችው በኢንተርኒውስ የገንዘብ ድጋፍ ታግዛ ነው

The post በቦረና ዞን ተከስቶ በነበረው ድርቅ ሳቢያ ተፈናቅለው በመጠለያ ያሉ ዜጎች ለከፋ ፆታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል first appeared on Wazemaradio.

The post በቦረና ዞን ተከስቶ በነበረው ድርቅ ሳቢያ ተፈናቅለው በመጠለያ ያሉ ዜጎች ለከፋ ፆታዊ ጥቃት ተጋልጠዋል appeared first on Wazemaradio.

[…]

የእምዬ ምኒልክ አዳራሽ

በአንድ ጊዜ 8ሺ ሰው በአንድ ቀን ደግሞ እስከ 40ሺ ሰው የሚስተናገድበት ትልቅ የድግስ አዳራሽ በአዲስ አበባ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ከ120 አመት በፊት ሲሠራ የነበረው የምህንድስና፣ ቅርጽና ይዘት፣ የመንግሥታዊ ድግሡ ታዳሚዎች ማንነትና የግብሩ ሥርአት፣ “ቀድሞም ጠቢብ ነበር ሰለሞን አባቱምኒልክ ይበልጣል ሰው ይዞ መብላቱ” ዳግማዊ ምኒልክ ሰዉ ሁሉ አንድ ጊዜ ተሰብስቦ የሚበላበትን ትልቅ አዳራሽ ለመስራት በመወሰን፣ በ1889 […] […]

በአንድ የባንክ ፍቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ማስመጣትም ሆነ መላክ ተከለከለ

Photo credit -ECC

ዋዜማ- የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ተገልጋዮቹ በአንድ የባንክ ፍቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ወደ አገር ቤት እንዳያስገቡም ሆነ ወደ ውጪ እንዳይልኩ ትእዛዝ ማስተላለፉን ይመለከታቸዋል ላላቸው አካላት ከጻፈው ደብዳቤ ዋዜማ መገንዘብ ችላለች።

ኮሚሽኑ እዚኽ ውሳኔ ላይ የደረስኩት፣ አንዳንድ ላኪዎች እና አስመጪዎች በአንድ የባንክ ፍቃድ በተለያየ ጊዜ ምርቶችን መላክ እና ማስመጣት የሚፈቅደውን ህግ፣ የአገርን ጥቅም በሚያሳጣ እና በሕገ ወጥ መንገድ እየተጠቀሙበት እንደሆነ ስለደረስኩበት ነው እንዳለ ከደብዳቤው ተረድተናል። እስከ አሁን ጥቅም ላይ የነበረው የጉምሩክ ሥርዓት፣ የተገልጋዮችን ሥራ ለማቅለል ሲባል አስመጪዎች እና ላኪዎች በባንክ የተፈቀደላቸውን አንድ የባንክ ፍቃድ ሰነድ በመጠቀም፣ እቃዎችን በተለያዩ ጊዜያት እንዲያስገቡ እና እንዲልኩ ይፈቅዳል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ የጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለሙያ፣ “በአንድ የባንክ ፍቃድ በተለያየ ጊዜ ምርት ማስገባት መፈቀዱ ለብዙ ያልተገቡ አሰራሮች መንገዶችን ከፍቶ ቆይቷል” ሲሉ ለዋዜማ ተናግረዋል። ባለሙያው እንደገለጡት፣ “በአንድ የባንክ ፍቃድ በተለያየ ጊዜ ምርቶችን ማስመጣት መፈቀዱ፣ አስመጪዎች የተፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሬ ከሚችለው በላይ ምርቶችን በተለያዩ ጊዜያት እንዲያስገቡ ሁኔታዎችን አመቻችቷል”ም ብለውናል። ባለሙያው ለማሳያነትም በሚል፣ ወደ አገር ውስጥ በገፍ የገቡትን መኪኖች ያነሳሉ።

መንግስት በነዳጅ ለሚሰሩ መኪኖች ባንኮች የውጭ ምንዛሪ እንዳይፈቅዱ ካዘዘ ዓመት ቢያልፍም፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መኪኖቹ ሲገቡ የቆዩት፣ ለእነዚኽ መኪኖች የውጭ ምንዛሬ እንዲከለከል ከመደረጉ በፊት በተገኘ የባንክ ፍቃድ ምክንያት መሆኑንም ጨምረው ያነሳሉ።

ዋዜማ እንደተረዳችው ከሆነ፣ በክፍልፋይ ጊዜ በአንድ የባንክ ፍቃድ በተለያዩ ወቅቶች ምርቶችን ማስገባት መፈቀዱ፣ አስመጪዎቹ ባንክ ከፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ በላይ የሚያወጡ ምርቶችን የማስገባት ዕድሎችን እንደመፍጠሩ፣ በዚኽም ባንኩ ከፈቀደላቸው ውጭ ጥቅም ላይ ያዋሉት ገንዘብ ከጥቁር ገበያ የተገኘ ነው የሚለውን ጥርጣሬ ከማሳደጉ ባለፈ፣ አሰራሩም ሕገ ወጥ ገበያን አበረታቷል የሚል አተያይን በጉምሩክ ኮሚሽኑ በኩል አስይዟል።

የጉምሩክ ኮሚሽኑ፣ ከኅዳር 10 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ የባንክ ፍቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርትን ማስገባት የሚከለክለውን አሰራር እንደሚተገብር ገልጿል። ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በጻፈው ደብዳቤም፣ የንግድ ባንኮች ፍቃድ ሲሰጡ ይህንኑ ታሳቢ እንዲያደርጉ ማሳሰቡንም ዋዜማ ራዲዮ መረዳት ችላለች። [ዋዜማ]

The post በአንድ የባንክ ፍቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ማስመጣትም ሆነ መላክ ተከለከለ first appeared on Wazemaradio.

The post በአንድ የባንክ ፍቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ማስመጣትም ሆነ መላክ ተከለከለ appeared first on Wazemaradio.

[…]

የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ

በ116ኛው የሠራዊት ቀን ሲከበር ንግግር ያደረጉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “ዐጼ ምኒልክ የጦር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያቋቋሙበትን ቀን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ኾኖ እንዲከበር ተደርጓል” በማለት ቀኑ ለምን እንደተመረጠ ይፋ አደረጉ። ከዚህ ሌላ ፊልድ ማርሻሉ በንግግራቸው፤ ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ከጀግኖች የተረከብናትን ኢትዮጵያ እንደተከበረች እና ማንነቷ እንደተጠበቀ ለማስቀጠል ወታደራዊ ዝግጁነታችንን አሳድገንና ቁመናችንን አዘምነን ማንኛውንም ተልዕኮ በላቀ ብቃት ለመፈጸም […] […]

Ethiopia Launches Program to Improve Honey Productivity and Quality

UNIDO Honey

Ethiopia has unveiled a new program which aims to enhance the productivity and quality of honey, supported by the Norwegian government and the United Nations Industrial Development Organization (UNIDO).

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.