Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

Egypt fears the Sudan crisis complicates the Egypt-Ethiopia negotiations over the GERD

JONATHAN GORNALL A peaceful resolution of the row over Ethiopia’s dam may hinge on who emerges victorious in Sudan’s power struggle Experts say a prolonged conflict could throw both Sudan and Egypt’s water and food …

Egypt fears the Sudan crisis complicates the Egypt-Ethiopia negotiations over the GERD Read More »

The post Egypt fears the Sudan crisis complicates the Egypt-Ethiopia negotiations over the GERD first appeared on Zehabesha Latest Ethiopian News, Videos, Photos & Headlines.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - 28 April 2023

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 28 April 2023.

[…]

Ethiopia-Pakistan Business Forum to be Held in Karachi

Ethiopia Pakistan Business Forum

Ethiopian Embassy in Islamabad announced that Ethiopia-Pakistan Business Forum would be held in Karachi during the second week of May. The forum has a goal of enhancing bilateral trade between Ethiopia and Pakistan.

[…]

Ethiopia Gains USD 907 Million from Coffee and Tea Export

coffee-plantation

Ethiopia gained USD 907.56 million in nine months by exporting more than 169 thousand tons of coffee, tea, and spices. Germany, Saudi Arabia, the United State, Kenya, the United Kingdom, China, and India were the major export destinations.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - 27 April 2023

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 27 April 2023.

[…]

በኦሮሚያ ፣ በሶማሌና በደቡብ ክልሎች በተከሰተው ድርቅና ጎርፍ መንግስት ሀላፊነቱን በአግባቡ እንዳልተወጣ ዕምባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ

Photo credit Save the Children

ዋዜማ-የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በኦሮምያ ፣ ደቡብና ሶማሌ ክልሎች በድርቅና ጎርፍ ለተፈጠረው አደጋ የሰጠው ምላሽ ዳተኛነት የታየበትና ከሚጠበቀው በታች በመሆኑ ችግሩን የባሰ እንዳወሳሰበው አስታውቋል፡፡

በድርቅና ጎርፍ አደጋ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተደረገ ያለውን የሰብአዊና ቁሳዊ ድጋፍ ፣መሰረታዊ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የመልሶ የማቋቋም ስራ በተመለከተ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ያጠናቀረውን ሪፖርት ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ለጋዜጠኞች ይፋ አደርጓል፡፡

ተቋሙ ሶስት ቡድኖችን በማደራጀት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን፣ በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እና በሶማሌ ክልል በዳዋ ዞኖች በተመረጡ 10 ወረዳዎች እንዲሁም በመጠለያ ጣቢያዎች ከመጋቢት 11 እስከ መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የቁጥጥር ስራ ማከናወኑን አስረድቷል፡፡

ባደረገው የመስክ ጉብኝትም የደረሰባቸውን ግኝቶች በተመለከተ የህዘብ አንባ ጠባቂ ተቋም የአስተዳደር በደሎች መከላከል ዳይሬክተር አቶ አደነ በላይ ማብራሪያ

በዳሰሳ ጥናቱ የተፈተሹና መረጃ የተሰባሰበባቸው አካላት መካከል የክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤቶች፣ የክልሎች የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፤ የዞኖችና ወረዳዎች ኃላፊዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ ለአደጋ መከላከል የተቋቋሙ ግብረ ኃይሎችና በድርቅና ጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎች ናቸው፡፡

በኦሮሚያ ክልል – ቦረና ዞን በአራት ወረዳዎች በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ተፈናቅለው የሚገኙ 59፣561 ዜጎች በ20 መጠለያዎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከ 1 ሚሊየን 300 መቶ ሺ በላይ እንሰሳት መሞታቸውን በሪፖርታቸው ገልፀዋል።

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በሁለት ወረዳዎች በተከሰተ ድርቅና ጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለዉ በመጠለያ ጣቢያ ዉስጥ የሚገኙ ዜጎች 63፣970 ናቸው፡፡ በዚሁ ዞን በድርቅና በጎርፍ የሞቱ እንስሳት 76,200 ያህል መሆናቸው በጥናቱ ተለይቷል፡፡

በሱማሌ ክልል /ዳዋ ዞን ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ዳዋ ዞን በአራት ወረዳዎች ተፈናቅለው በአራት መጠሊያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ብዛት 16፤344፣ በድርቅ ምክንያት ሃብት የወደመባቸው ዜጎች 19፣044 ናቸው፡፡ በዚሁ ክልል በድርቅ የሞቱ የቀንድ ከብቶች፣ ግመሎች እና ፍየሎች ብዛት 334 716 ፣ በአደጋ ላይ ያሉና አስቸኳይ መኖ የሚያስፈልጋቸው እንስሳት 420,160 ሲሆኑ በጎርፍ ምክንት የሞቱ ደግሞ 8,330 ናቸው፡፡

የዋና እንባ ጠባቂ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው በቦረና ዞን የተፈጥሮ ድርቅ በተከታታይ ዓመታት የተከሰተ ቢሆንም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የሚቀርበዉን ሪፖርት በመቀበል ዜጎችና እንስሳት የጉዳቱ ሰለባ እንዳይሆኑ የቅድመ መከላከልና አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄ ባለመደረጉ በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በዚሁ ዞን የተፈጠረውን ድርቅና ጎርፍ አደጋ አስመልክቶ ጠንካራና ግልጽ የመረጃ ልዉዉጥ አለመኖር፣ ድርቁን ተከትሎ የሚመጣዉን በሽታ ለመከላከል የተደረገው ዝግጅት አናሳ መሆን፤ ለአደጋ ጊዜ የሚከማቸዉ እህል በፌደራል መንግስት እጅ የሚመራ በመሆኑ በክልል ደረጃ የሚከማች እህል ባለመኖሩ የሚደረጉ እርዳታዎችን በጊዜና በወቅቱ ማቅረብ እንዳልተቻለ ተጠቅሷል፡፡

በደቡብ አሞ ዞን የተደረገው ጥናት ክልሉ በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ እንዲደረግላቸው ለፌደራል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር በተደጋጋሚ ጊዜ ጥያቄ ቢቀርብም ምንም አይነት ምላሽና እገዛ አለመደረጉን ያሳያል፡፡

በዚሁ የደቡብ ኦሞ ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች ለእርዳታው ሲባል ካላቸው የሰው ሃይል በላይ ሰው ማስመዝገብና አመራሮችም ጭምር በእርዳታው ውስጥ ለመካተት ጥረት ሲያደርጉ መታየቱንም ተመላክቷል፡፡

የሶማሌ ክልል ላይ የተካሄደው ጥንቅር እንደሚያሳየው ደግሞ በድርቅ ምክንያት ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎች ለሚደረግላቸው ሰብዓዊ ድጋፍና እርዳታ እንዲሁም የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አለመሆን እንዲሁም ከድርቁ ባለፈ በአሁኑ ሰዓት በተከሰተ ጎርፍ ለተደራራቢ አደጋ ለተጋለጡ ተፈናቃዮችና ሌሎች ማህበረሰብ ክፍሎች ፈጣን ምላሽና አስቸኳይ ድጋፍ አለመሰጠቱ ተገልጿል፡፡

በመንገድ መሰረተ ልማት እና ጎርፍ ችግሮች ምክንያት የሚደረገው ውስን ድጋፍ በአሁኑ ወቅት መቋረጡና ከሚመለከታቸው አካላት ትኩረት አለመኖር፣ ለሴቶች፣ ህጻናት፣ አካል ጉዳተኞችና ለአረጋዊያን ለሚደረገው ልዩ ድጋፍና ጥበቃ የተዘረጉ አሠራሮች አለመኖራቸውን ሪፖርቱ ያትታል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ያጠናቀረውን ሪፖርት አሰመልከቶ ባቀረበው ምክረ ሃሳብ ፓርላማው የተፈጠሩ ክፍተቶችን ባለው የአሰራር ስርዓት መሰረት እርምት እንዲወሰድ ያሳሰበ ሲሆን ልዩ ትኩረት የሚያሻቸው ወገኖች በመንግስት በኩል የሚደረግላቸው ድጋፍ ጊዜውን ያልጠበቀና ተደራሽ ካለመሆኑም ባሻገር ለፌደራል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ለሚያቀርቡት ተደጋገሚ ጥያቄ ፈጣን ምላሽና እገዛ አለመደረጉ አጽንኦት ተሰጥቶት እንዲሰራበት ጠይቋል፡፡

የክልል መንግስታት በተፈጥሮ ድርቅና ጎርፍ ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ውስጥ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስፈልገውን በጀት አስጠንተው ለፈደራል መንግስትና ለሌሎች አጋር አካላት በማቅረብ የድጋፍ ቋት እንዲያዘጋጁ መክሯል። [ዋዜማ]

The post በኦሮሚያ ፣ በሶማሌና በደቡብ ክልሎች በተከሰተው ድርቅና ጎርፍ መንግስት ሀላፊነቱን በአግባቡ እንዳልተወጣ ዕምባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ first appeared on Wazemaradio.

The post በኦሮሚያ ፣ በሶማሌና በደቡብ ክልሎች በተከሰተው ድርቅና ጎርፍ መንግስት ሀላፊነቱን በአግባቡ እንዳልተወጣ ዕምባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ appeared first on Wazemaradio.

[…]

“የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማክበር ቀይ መስመራችን ነው “  የፌደራል ፖሊስ

የፀጥታ መዋቅሩ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለማከበር እየተባባሰ የመጣ ችግር መሆኑን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሳይቀር አቤት ቢሉም የፌደራል ፖሊስ ግን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማክበር “ቀይ መስመራችን” ነው ብሏል። የፌደራሉ ፓሊስ ኀላፊዎችን የፓርላማ ምላሽ ተመልክተነዋል። አንብቡት

Demelash Gebremichael, Head of Federal Police

ዋዜማ-የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባላፉት ዘጠኝ ወራት 26 ቢሊዮን ብር የሚገመት የአገር ሀብት በመመዝበር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ጉዳይ እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ህገወጥ ንግድ፣ ኮንትሮባንድ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ጨምሮ በርካታ አይነት ትልልቅ ወንጀሎች ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የገለጸው ሚየዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም የተቋሙን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅተ ነው፡፡

በዚሁ ሪፖርት ላይ የምክርቤት አባላቱ የፌደራል ፖሊስ በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድቤት መቅረብ ሲኖርባቸው ሳይቀርቡ ከህግ ውጭ ከሳምንት በላይ በእስር ላይ መቆየት፤ የፍርድቤት ትዕዛዝ አለመከበር ለአብነትም ፍርድቤት ቀርበው ፍርድቤቱ ጥፋት አላገኘሁባቸውም ብሎ የሚያሰናብታቸውን ሰዎች ፖሊስ አልፈታም ማለቱንና ይህንንም ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ምልከታ ስራው ማረጋገጡን ጠቅሶ ፣ ለምን እንዲህ ሆነ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል፡፡

በተመሳሳይ የፍርድቤት ትዕዛዝ ተግባራዊ አለመደረግን በተመለከተ ከምክርቤቱ እንደቀረበው የፌደራል ፖሊስ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በፍርድቤት እንዲቀርቡ ከታዘዙ 2, 945 ተከሳሽ ውስጥ ፖሊስ ይዞ ወደ ፍርድቤት ማቅረብ የቻለው 1,169 ወይንም የተጠየቀውን 39 በመቶ የሚሆነውን ብቻ ነው፡፡

ከምክርቤቱ የተነሳውን ጥያቄ አስመልከተው ማብራሪያ የሰጡት ዋና ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካዔል ፤ የፍርድ ቤት ውሳኔ አለመፈጸምን በተመለከተ ሲመልሱ ‹‹የምጠረጥረው ስህተት እንዳይሆን ነው፤ እኛም መብት አለን፤ ተጠርጣሪው አደጋ ያደርሳል ብለን ስናስብ ነገር ግን ፍርድቤት ተጠርጣሪውን ሊለቅብን ሲል በየደረጃው እየቀረብን እናመለክታለን፤›› ብለዋል፡፡

በዚህ ጊዜ ውስጥ ተጠርጣሪው አልተለቀቀም ተብሎ የሚቀርብ ከሆነ ደግሞ የህግ አካሄድ ስላለ ህጉን ማየት ነው ያሉት ኮሚሽነር ደመላሽ ፤ አሁን እየታየ ያለው ፍርድቤት ዋስትና ከፈቀደ ለምን አትለቁም የሚል ነው፤ ነገር ግን መልቀቅ በሌለብን ቦታ ላይ የህግ ሂደቱን እየተከተልን የምንሰራቸው ስራዎች ስላለሉ ህጉ በደንብ ሊታይ ይገባል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የህግ የበላይነት ይከበር፤ ይህ አገር ሰላም ይኑረው ከተባለ ሀላፊነቱ የምክርቤቱ፣ የፍርድቤቱ፤የህዝቡ፤ የፖሊሱ ፤ የሰብዓዊ መብት ውስጥ ያሉትም ሆነ የሌላውም አካል መሆኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ‹‹በጣም የምንጠነቀቀውና እያወቅንና ቀጥሎ ችግር እንደሚፈጥር እየታወቀም ቢሆን የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ማክበር ላይ ነው›› ብለዋል፡፡

የፍርድቤት ትእዛዝ መከበር ቀይ መስመር እንደሆነ የገለጹት ኮሚሽነር ደመላሽ፤ ፍርድቤቶች ግልጽ የሆነ አቋም ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉ ጋዜጠኞች ጋር በተገናኘ፤ አንዱና ትልቁ ንትርክ የተለያዩ ሃይሎች አደረጃጀቶችን በመጠቀም በአገር ወስጥና ከአገር ውጭ ተቀናጅተው ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ እያገኙ፤ አንዳንዶቹም የገቢ ምንጭ አድርገውት የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ወደ ፍርድቤት ሲቀርቡ የፍትህ አካላት ከእኛ ጎን ሊቆሙና ሁኔታው ስርዓት እንዲይዝ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል ኮሚሽነር ደመላሽ፡፡

በመሆሙም በዚህ ጉዳይ ላይ ከፍርድቤቶች ጋር የጋራ መድረክ ቢፈጠር ካልሆነ ደግሞ ቋሚ ኮሚቴው ለፍርድ ቤቶች አጽንኦት ሰጥቶ በጋራ መቆም ያለብን ይመስለኛል ብለዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 26 ቢሊዮን ብር የመንግስትና የህዝብ ሃብት የመዘበሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ሃብቱን የማዳን ስራ እየሰራና ምርመራ እካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተቋማቸው የሪፎርም ስራ ካካሄደ ወዲህ ‹‹ፍርድ-ቤት በየትኛውም ጊዜ በደብዳቤም ይሁን በሌላ መንገድ የወሰንኩት ውሳኔ አልተከበረልኝም በሚል በእኛ ላይ ያቀረበልን አቤቱታም ይሁን ቅሬታ የለም›› ብለዋል፡፡

ፍርድቤቶች አካባቢ የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ ችግር አለ ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ፌደራል ፖሊስ ሰበር ችሎት ድረስ በመሄድ የተለያዩ ጉዳዮችን ይዞ መጠየቅ እንደሚችልና የምርመራ ሂደቱን በተለያየ ደረጃ ለማስኬድ ከጊዜ ቀጠሮ ጀምሮ እስከ ሰበር ችሎት ድርስ ይግባኝ ለመጠየቅ ህጉ እንደሚፈቅድላቸው ተናግረዋል፡፡

‹‹ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ላይ ምርመራ እያካሄድን ነው፤ ከዚህ አንጻር ተፈላጊ የሆኑ ሰዎች ዛሬ ወጥተው ነገ የማይገኙበት ሁኔታ ስለሚፈጠር እኛ ደረጃውን ጠብቀን እስከሰበር ችሎት ድረስ ይግባኝ እየጠበቅን ጉዳዩን ለማየት በሚል የምንከተለው አካሄድ አለ፤ ነገር ግን እኔ እስከማቀውቀው ድርስ እስካሁን ትዕዛዜ አልተከበረም በሚል ከፍርድቤት የመጣ ጉዳይ የለም›› ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ዘላለም በቁጥጥር ስር ዋሉ ጋዜጠኞችን በተመለከተ፤ እነዚህ አካላት ይህን መንግስትና ህገመንገስት በሃይል ለመጣል ትላልቅ ዶክሜንቶች አዘጋጅተው ፤ በትላልቅ ክንፎችና መዋቅር ተደራጂተው በሚዲያና በጋዜጠኝነት ሽፋን ፍቃድ ወስደው የሚሰሩ አክቲቪስት ነን ባዮች ናቸው ብለዋል፡፡

ከአንድ ወር በፊት የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ወደ ተመረጡበት አካባቢ በመሄድ ህዝብ አወያይተው ከተመለሱ በኋላ ከህዝብ የተነሱ ጥቄዎችን በተመለከተ ከመንግስት አስፈጻሚ አካላት ጋር ባደረጉት ውይይት የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት የፍርድቤት ውሳኔ አለመከበር አብይ ችግር መሆኑን አንስተው ከፓርላማው ጭምር እገዛ እንደሚፈልጉ መድረክ ላይ ጠይቀው ነበር፡፡ [ዋዜማ]

The post “የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማክበር ቀይ መስመራችን ነው “ የፌደራል ፖሊስ first appeared on Wazemaradio.

The post “የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማክበር ቀይ መስመራችን ነው “ የፌደራል ፖሊስ appeared first on Wazemaradio.

[…]

PM Abiy confirms the shooting dead of Girma

Prime Minister Abiy Ahmed confirmed the shooting to death of Girma Yeshitila, head of the Amhara region Prosperity Party this afternoon. The PM said that Girma was a victim of those who could not overcome …

PM Abiy confirms the shooting dead of Girma Read More »

The post PM Abiy confirms the shooting dead of Girma first appeared on Zehabesha Latest Ethiopian News, Videos, Photos & Headlines.

[…]

How do you define an ethnic government in power that negotiates with itself?

I am at a loss in understanding what is going on in Ethiopia now. Pretoria, Nairobi and now beautiful Zanzibar. Ethiopia is ruled by the Oromo Prosperity Party. Innocent civilians, most prominently Amhara, are slaughtered by the …

How do you define an ethnic government in power that negotiates with itself? Read More »

The post How do you define an ethnic government in power that negotiates with itself? first appeared on Zehabesha Latest Ethiopian News, Videos, Photos & Headlines.

[…]

Negotiation between the Oromo Prosperty Party (OPP) and Oromo Liberation Army (OLA) Army in the Tanzanian island of Zanzibar

The nNegotiation between the Oromo Prosperty Party (OPP) and Oromo Liberation Army (OLA) Army in the Tanzanian island of Zanzibar is on its second day. According to sources who spoke to the BBC, prominent Oromo Historian, Professor …

Negotiation between the Oromo Prosperty Party (OPP) and Oromo Liberation Army (OLA) Army in the Tanzanian island of Zanzibar Read More »

The post Negotiation between the Oromo Prosperty Party (OPP) and Oromo Liberation Army (OLA) Army in the Tanzanian island of Zanzibar first appeared on Zehabesha Latest Ethiopian News, Videos, Photos & Headlines.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.