Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ በከተማው በርካታ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጣ

ዋዜማ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ፊት ለፊት ለኮሪደር ልማት በሚል የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን ዋዜማ ከተመለከተችው የጨረታው ሰነድ ተረድታለች።

የሊዝ ጨረታው ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውጭ በተቀሩት የከተማው አስር ክፍለ ከተሞች ባሉ ቦታዎች ላይ ወጥቷል። የሊዝ ጨረታው ለአመታት ከተቋረጠ በኋላ ሲወጣ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የጨረታው ሰነድም ከረቡዕ ሚያዝያ 9 2016 አ.ም ጀምሮ መሸጥ የተጀመረ ሲሆን ፣ የሰነድ ሽያጩ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 አ.ም ድረስ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

ለሊዝ የቀረበ ከፍተኛ ቦታ ያቀረበው ክፍለ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ሲሆን ቦሌ  እና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች አንድ አንድ ቦታ ለሊዝ ጨረታ ቀርቦባቸዋል።

በኮሪደር ልማት በፈረሰው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም አካባቢ 22 ቦታዎች ለሊዝ ጨረታ ቀርበዋል። በዚህ አካባቢ ትልቁ ለሊዝ የቀረበው ቦታ 2,179 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ፣ ዝቅተኛ ስፋት ያለው መሬት ደግሞ 650 ካሬ ሜትር ነው።

በደረጃ አንድ ለተመደቡት ለ22ቱም ቦታዎች የሊዝ መነሻ ዋጋ በካሬ 2,213.25 ብር ተቆርጦላቸዋል። ለአንድ ካሬ ከፍተኛ መነሻ ዋጋ የተቆረጠላቸውም እነዚሁ በአራዳ ክፍለ ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም አቅራቢያ ላሉት ቦታዎች ነው።ንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ በመጠን ብዙ (ከ150 በላይ ቦታዎችን) በማቅረብ ቀዳሚው ነው።

የጨረታ ሰነዱ 2,300 ብር እየተሸጠ ሲሆን ፣ ጨረታው ከሚያዝያ 28 2016 አ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ይከፈታል ተብሏል። የጨረታ አሸናፊዎች ቅድመ ክፍያ ያሸነፉበትን መሬት 40 በመቶ ሲሆን ቀሪው 60 በመቶ ክፍያ በአምስት አመታት ውስጥ ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ ይጠበቃል። የሊዝ ዘመኑም ለ60 አመታት ነው። ሁሉም ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎቹም ለቅይጥ አገልግሎት እንዲውሉ ታስቦ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሁኑን የሊዝ ጨረታ ያወጣው ባለፈው አመት መጨረሻ አካባቢ ከወጣው የሊዝ ጨረታ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

በ2015 አ.ም ግንቦት ወር ላይ የከተማ አስተዳደሩ 297 ቦታዎችን ለጨረታ አቅርቦ ነበር። በኋላ ላይ የአስሩ ቦታዎች ጨረታ ተሰርዞ የ287ቱ ቦታዎች የጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ነበር የወጣው።ሆኖም በ2015 አ.ም ሰኔ ወር አጋማሽ አካባቢ ጨረታው ሲከፈት በተለያዩ ቦታዎች ለአንድ ካሬ ቦታ የተሰጠው ዋጋ በእጅጉ ተጋኖ የታየበት ሁኔታ ነበር። በካሬ ከ690 ሺህ ብር በላይ ዋጋ የቀረበበት ቦታም ነበር።

እንዲሁም የ287 ቦታዎች የሊዝ ጨረታን አንደኛ ዋጋ  አቅርበው ካሸነፉት ውስጥ ውል ፈጽመው ቦታውን የተረከቡት ከግማሽ በታች የሆኑት 131 አሸናፊዎች ብቻ ነበሩ። 156ቱ አሸናፊዎች ውሉን ፈርመው መሬቱን አልተረከቡም። ይህም በወቅቱ መነጋገርያ ነበር።

በዚህ ሳቢያ የከተማ አስተዳደሩ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 156ቱን ቦታዎች ሁለተኛ ላይ የተቀመጡ አሸናፊዎች አንደኛ የሆኑት ተጫራቾች ባስቀመጡት ዋጋ መሬቱን እንዲረከቡም ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። የከተማ አስተዳደሩ ከመሬት ሊዝ ሽያጩ ሊያገኝ አቅዶ የነበረውን 12 ቢሊየን ብር ነበር። [ዋዜማ]

The post በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ በከተማው በርካታ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጣ first appeared on Wazemaradio.

The post በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ በከተማው በርካታ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጣ appeared first on Wazemaradio.

Source:: https://wazemaradio.com/%E1%89%A0%E1%8D%92%E1%8B%AB%E1%88%B3-%E1%88%88%E1%8A%AE%E1%88%AA%E1%8B%B0%E1%88%AD-%E1%88%8D%E1%88%9B%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8D%88%E1%88%A8%E1%88%B1-%E1%88%B0%E1%8D%88%E1%88%AE%E1%89%BD%E1%8A%95/?utm_source=rss&utm_medium=rss&utm_campaign=%25e1%2589%25a0%25e1%258d%2592%25e1%258b%25ab%25e1%2588%25b3-%25e1%2588%2588%25e1%258a%25ae%25e1%2588%25aa%25e1%258b%25b0%25e1%2588%25ad-%25e1%2588%258d%25e1%2588%259b%25e1%2589%25b5-%25e1%258b%25a8%25e1%258d%2588%25e1%2588%25a8%25e1%2588%25b1-%25e1%2588%25b0%25e1%258d%2588%25e1%2588%25ae%25e1%2589%25bd%25e1%258a%2595

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.