Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

Voice of Amhara Daily Ethiopian News April 30, 2018

Voice of Amhara Daily Ethiopian News April 30, 2018 […]

OROMIA’s MINERAL WEALTH: A BLESSING OR A CURSE?

“Nepotism is the gold and the conductor’s connection and Ignorance is the prison that the people are kept in the military are not there for the people’s protection.They’re just there to protect an investment That’s why people get arrested” – Immortal Techniques Author: Angasu Areri Oromia is considered one of the richest region of the […] […]

Hiber Radio Daily Ethiopian News April 30, 2018

Hiber Radio Daily Ethiopian News April 30, 2018 […]

Ethiopia: Dr Negede Gobeze & Dr Aregawi Berhe on Dr Abiy Ahmed

Ethiopia: Dr Negede Gobeze & Dr Aregawi Berhe on Dr Abiy Ahmed […]

ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግልጽ ውይይትና ድርድር ሊደረግ ይገባል!

ዶ/ር አብይ የኦህዴድ ጽ/ቤት አላፊ በነበሩበት ወቅት ኦህዴድ ሁሉንም ሰላም ወዳድ ዜጋን ያስደሰተ ጥሪ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ላሉ ተቃዋሚዎች አቅርቦ ነበር። ይህ ጥሪ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የቀረበ በመሆኑ አንዳንድ በኦሮሞ ስም የሚታገሉ በውጪም በውስጥም ያሉ ተቃዋሚዎች በደስታ የተቀበሉት ነበር። ነገር ግን ይህ የኦህዴድ ጥሪ ምንም ያህል ለሀገሪቱ ሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ቢሆንም ያለ […] […]

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከራሳቸው ማዳን!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተስፋን-በጥንቃቄ (cautious optimism) ካነገቡት ሰዎች አንዱ ነኝ። የተስፋዬ መሠረቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን የመጡበት መንገድ፣ የገቧቸው ቃልኪዳኖች እና አሁን የታየው መረጋጋት ናቸው። አሁን የታየው መረጋጋት ስል የቄሮዎች የአደባባይ ተቃውሞ መቆሙን ማለቴ አይደለም። ተቃዋሚዎችን እያሳደዱ መከታተል፣ ማዋከብ እና ማሰር ርቀን ሳንሔድ አምና ከነበረው አንፃር እንኳ ልዩነቱ የትየለሌ ነው። ለዚህ የራሴን ስሜት እና ተሞክሮ […] […]

BBN Daily Ethiopian News April 27, 2018

BBN Daily Ethiopian News April 27, 2018 […]

አብይ ሲለካ.. የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አንድ ወር !

Abiy at parliament

[ዋዜማ ራዲዮ] አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ስልጣን ከተረከቡ አንድ ወር ሊደፍኑ ቀናት ይቀራሉ። መሪው ወደስልጣን የመጡበት ድባብ የተለየ ከመሆኑ ባሻገር በአስታራቂና አማላይ ንግግሮቻቸውም ቀላል የማይባል ደጋፊ አበጅተዋል። ዋዜማ ራዲዮ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ስልጣን ከተረከቡ የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ያደረጉትን ንግግር በተለይ መንግስታቸው ያከናውነዋል ያሉትን ቁልፍ ቃል ኪዳኖች ነቅሰን አውጥተናል።
እስካሁን ቃል ለገቡት ተግባር ማስፈፀሚያ የሚሆን ፍኖተ ካርታ ይፋ ባያደርጉም በንግግሮቻቸው ቁልፍ የፖሊሲ ጉዳዮችን አንስተዋል። ለክትትል እንዲመቻችሁ በዘርፍ በዘርፍ አሰናድተነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉትን ቃል በቃል ጠቅሰን፣ በቅንፍ ውስጥ ደግሞ መቼና የት እንደተናገሩት እናስቀምጣለን። [ይህን ዘገባ በድምፅ ለማግኘት ይህን ማስፈንጠሪያ ይከተሉ- Click Here]

ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር

“…ኢትዮጵያ እያደገች ያለች ሀገር ስለሆነች፣ ሁልጊዜ ለረዥም ጊዜ ጥቂት ሰዎችን ወንበር ላይ ማቆየት አትችልም የሚል ሀሳብ ስላለ ትምሕርት እንዲሆን… ኢሕአዴግ እንደ ድርጅት የወሰነው ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ያልገባ ስለሆነ፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የምናስገባው… ማንም የኢትዮጵያ መሪ ከአሁን በኋላ ከሁለት ተርም በላይ [በሕገ መንግሥት ጭምር] ማሰሪያ የሚደረግለት… የዕድሜ ልክ ሥልጣን ኢትዮጵያ ውስጥ ያበቃ መሆኑን፣ አሁን ላለነው፣ ለሚመጡት ለማስተማር ጭምር መሆኑን ግንዛቤ ቢወሰድ ጥሩ ነው” (ሀዋሳ፣ ሚያዚያ 18 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር፡ ይህ እንግዳ ሀሳብ ሲሆን ህገ መንግስታዊ ማሻሻያም ይፈልጋል። እቅዱ የተነገረው በዚህ ሳምንት በመሆኑ ተጨማሪ ወራትን መጠበቅ ግድ ሳይል አይቀርም

“…ለሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲ ሥርዓት መረጋገጥ ወሳኝ የሆኑ የዲሞክራሲ ተቋማት ተጠናክረው፣ ከወገንተኝነት ጸድተው፣ ሕዝባዊ ተዓማኒነታቸው እንዲጎለብት… መወሰድ ያለባቸውን ቁልፍ እርምጃዎች በጥናት ላይ ተመስርተን የምንወስድ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር፡ የተጀመረ አልያም የተገለፀ አዲስ እቅድ የለም

“…በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ውስጥ፣ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም መርህ፣ በመደማመጥ የሃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ መሆን አለበት፡፡ ኢትዮጵያ የጋራችን፣ የኛ የሁላችን መሆኗን ተገንዝበን የሁሉም ድምፅ የሚሰማበት፣ ሁላችንንም የሚያሳትፍ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመገንባቱን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ዴሞክራሲ ሲገነባ መንግሥት የዜጎችን ሃሳብ በነፃነት የመግለፅ መብት ማክበር አለበት፡፡ ዴሞክራሲን ከዜጎች ሠላማዊ እንቅስቃሴና ከመንግሥት መሪነት፣ ደጋፊነትና ሆደ ሰፊነት ውጪ ማዳበር አይቻልም። በመሆኑም መንግሥት የዜጎች ሠላማዊ እንቅስቃሴ እንዳይስተጓገል በፅናት ይሰራል” (ፓርላማ ፣መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር፡ ሀገሪቱ አሁንም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ናት

“ድርጅታችን ኢሕአዴግ በሀገራችን ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የተለያዩ ሥራዎች ቢሰራም ከሚጠበቀው አንጻር ሂደቱም ሆነ ውጤቱ ምሉዕ አልነበረም፤ አካሄዳችን ከመርሃችንና ከንግግራችን ሳይጣጣም ለዲሞክራሲ ሥርዓት መጎልበት መሄድ የሚገባንን ርቀት አለመሄዳችን ግልጽ ቢሆንም ይሕንን አሉታዊ ገጽታ ለመንደርደር እንደ መዘጋጃ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመን በሙሉ ኃይልና የአብሮነት መንፈስ ልንረባረብ ይገባል፡፡ ይሕንን መሰረታዊ ጉዳይ ዕውን ለማድረግም ኢሕአዴግ ራሱን ገምግሞ ችግሮቹን ከመለየት ባሻገር ከችግሩ ለመውጣት በሁሉም ደረጃ በሚገኙ አደረጃጀቶቹ የሪፎርምና የለውጥ ሥራዎች ማካሄድ ጀምሯል…” (ቤተመንግስት፣ ሚያዝያ 3 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር፡ የሚንስትሮች ሹም ሽርና ሽግሽግ ተደርጓል፣ መሰረታዊ የኣአደረጃጀትም ሆነ የአስተሳሰብ ለውጥ አልታየም

“…ሕግ ሁላችንንም እኩል የሚዳኝ መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ሲሆን ሕግ በተፈጥሮ ያለንን ሰብዓዊ ክብራችንን ያስጠብቅልናል፡፡ ይህን እውነታ በመረዳት በሀገራችን ዲሞክራሲ እንዲያብብ፣ ነፃነትና ፍትህ እንዲሰፍን፣ የሕግ የበላይነት ዕውን እንዲሆን አስፈላጊውን ማሻሻያ በማድረግ በዘርፉ ያለውን ክፍተት እንሞላለን” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን የመፍታት ሂደቱ ቀጥሏል፣ነገር ግን አሁንም በየእሰር ቤቱ ፖለቲካዊ ይዝት ባላቸው ክሶች መነሾ የሚማቅቁ ሰለመኖራቸው የአደባባይ ሚሰጢር ነው፡፡ እንዲያውም በያዘነው ሳምንት ከቅሊንጦ እሳት ቃጠሎ ምክኒያት በግፍ ታሰረው የሚገኙ እሰረኞችን ፍቱ እያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እየሞገቱ ነበር፡፡ በተጨማሪ ምንም አይነት የፍትህ ስርዓት ማሻሻያ አልቀረበም

“…ታዳጊውን ዲሞክራሲያችንን ለማዳበር ተጨማሪ የሕይወትም ሆነ የአካል መስዋዕትነት አያስፈልገንም፡፡ ባለፉት ዓመታት እንደ መንግሥትም እንደ ዜጎችም ከዲሞክራሲ ባህላችን አለመዳበር ጋር ተያይዞ በታዩብን እጥረቶች በዜጎቻችን ህይወት እና በግልም በጋራም ንብረቶቻችን ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት ደርሷል። ይህንን ሁላችንም ማስቀረት እንችልና ይገባንም ነበር፡፡ በተለያየ ጊዜ፣ መስዋዕትነት ለከፈሉ የመብት ተከራካሪዎችና ፖለቲከኞች፤ በቅጡ ሳይቦርቁ ህይወታቸው ለተቀጠፈ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች፤ ለሥነ ልቦናዊና አካላዊ ቀውስ ለተዳረጉ ቤተሰቦችና ግለሰቦች ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡
“…እንዲሁም ሰላም ለማስከበርና ሕገመንግሥታዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሲንቀሳቀሱ ህይወታቸውን ላጡ የፀጥታ ኃይሎች አባላት ለከፈሉት መስዋዕትነት ያለኝን አድናቆትና አክብሮት ለመግለፅ እፈልጋለሁ፡፡ ለተፈጠሩ ችግሮች እልባት በማበጀት ህዝባችንን እንደምንክስም ጭምር በዚሁ አጋጣሚ ቃል እገባለሁ” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ በርካታ ሰዎች ታስረዋል። የፀጥታ ሀይሎች ቢያንስ በሶስት አካባቢዎች ግድያ ፈፅመዋል ፣ የስብዓዊ መብት ተሟጋቾች ደግሞ 18 ስዎች መገደላቸው መረጃ አለን ይላሉ

“…ውጤታማ ባልሆነ የተንዛዛ ስብሰባ የሚባክን ጊዜና ንብረትን በመቀነስ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለሕዝብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ለመዘርጋት ተገቢውን ምላሽ የማይሰጥ የመንግስት ሠራተኛንም ሆነ ተቋም ተጠያቂ ለማድረግ የሚቻልበት አካሄድ በመዘርጋትና በማጠናከር ችግሩ የሚቀረፍበት ሁኔታ ለመቀየስ እንቅስቃሴ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እንግልት እንዳይኖር የሚያስችል መንግስታዊ አሰራር እንዲፈጠር ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ እንደምንሰራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: ጠቅላይ ሚንስትሩ ራሳቸው በየክልሉ እየተዘዋወሩ ከህዝቡ ጋር መሰብሰባቸውን ይቀጥሉ እንጂ፣ በተቋም ደረጃ ስብሰባ ስለመቀነስ የተሰጠ መመሪያ አልያም የቀረበ እቅድ የለም።

“…የዲሞክራሲ እውነተኛ ጥንካሬ መለኪያና አመላካች ተደርገው ትልቅ ትኩረት ከሚሰጣቸው መካከል የፍትሕ ሥርዓቱ ተቋማዊና ሙያዊ ብቃት ቀዳሚነት እንደሚይዙ ይታወቃል፡፡ የሕዝባችን ብሶት ምንጭ የሆኑት የፍትሕ አካላት ነጻነታቸውንና ሙያዊ ሥነ ምግባራዊ ብቃታቸውን ባረጋገጠ መንገድ እንዲሰሩ፣ በሕገ መንግስቱ መሰረት ተጠያቂ እንዲሆኑና የፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ለውጥ እንዲመጣ የሚያስችሉ መፍትሔዎችን በመውሰድ አስፈላጊው ሁሉ ይደረጋል” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: በሀገሪቱ ባለፉት ሶስት ዓመታት በርካታ ግድያ እስርና እንግልት ያደረሱ አካላት ላይ እስካሁን ህጋዊ ተጠያቂነት ይፋ አልተደረገም። ይሁን እንጂ መንግሰት ባደረገላቸው ጥሪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዛይድ ራድ አልሁሴን ኢትዮጲያን ጎበኝተዋል፡፡ ከተለያዩ የሰበዓዊ መብት ተሟጋቾችም ጋር ንግግር እንዲያደርጉ መንግስታቸው ፈቅዷል፡፡

“…በሕግና መመሪያ ተከልሎ የሚደረግ አድሎና በደል በማቆም፣ በፍትሕ ሥርዓቱ ሕዝቡ እውነተኛ ዳኝነት የሚያገኝበት፣ የሕግ የበላይነት የሚረጋገጥበት፣ ሠብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩበት፣ ከፖለቲካ ወገንተኝነት፣ ከጉቦ የጸዳ አገልግሎት የሚሰጥበት እንዲሆን አበክረን እንሰራለን” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: በፍትህ ዘርፍ ምንም አይነት ማሻሻያ ይፋ አልተደረገም

“…የመብት ጥሰት ብሶት ያስከተሉ፣ ለኢ ፍትሐዊ ምክንያት የሆኑ ሕጎችን ከሕዝብ በሚገኝ ግብዓት በመፈተሽ አስፈላጊው ማሻሻያ ይደረጋል” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: አፋኝ የተባሉት የፀረ ሽብር ህግ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከተው ህግ እና የሚዲያ ነፃነት ህግ አሁንም በስራ ላይ ናቸው።
የፖለቲካ ምህዳር ማስፋትና ተቃዋሚዎችን ማሳተፍ

“…ከኢህአዴግ ውጪ ያሉ ፓርቲዎችን የምናይበት መነፅር እንደ ተቃዋሚ ሳይሆን እንደ ተፎካካሪ፣ እንደ ጠላት ሳይሆን እንደ ወንድም፣ አማራጭ ሃሳብ አለኝ ብሎ እንደመጣ አገሩን እንደሚወድ የዜጋ ስብስብ ነው። ስለዚህ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ የተመቻቸና ፍትሃዊ የመወዳደሪያ ሜዳ እንዲኖር በመንግሥት በኩል ጽኑ ፍላጎት ያለ በመሆኑ ስለ ሠላምና ፍትህ በልዩ ልዩ መንገድ የምትታገሉ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች፣ አብሮነታችንንና ሠላማችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ፤ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንንም አሳልፈው የሚሰጡ የአስተሳሰብ መስመሮችን በአርቆ አስተዋይነትና ሀገራዊ ፍቅር፤ በሰጥቶ መቀበል መርህ የተሻለ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት እንድታግዙ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: የተወሰኑ የተቃዋሚ መሪዎች በጠቅላይ ሚንስትሩ የእራት ግብዣ ላይ ከመታደማቸው ውጪ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ምቹ ሁኔታ በድርጅታቸው ኢሕአዴግ የተወሰደ እርምጃ የለም

“…ትርጉም ያለው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲጎለብት ኢሕአዴግ ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎችም መጠናከር ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ተዓማኒነት ያለው፣ ፍትሐዊ በሆነ የመወዳደሪያ ሜዳ ላይ የሚከናወን፣ እውነተኛ ፉክክርና የሀሳብ ፍጭት የሚታይበት እንዲሆን ለማድረግ ከወዲሁ በቅንጅት እንደምንሰራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: ይሁን እንጂ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ ይካሄድ የነበረውን ስድስተኛ ዙር አዲስ አበባና ድሬዳዋ ጨምሮ የሚካሄደውን የአካባቢ የማሟያ ምርጫን ቀን አራዝሟል፡፡

“[ከተቀዋሚ ፓርቲዎች ጋ] ለፉክክር የሚመች ሜዳና ነጻነት እንዲኖር በማድረግ ለሀገራችን፣ ለሕዝባችንና ለድርጅታችንም የሚበጅ ፖለቲካዊ ዐውድ ለመፍጠር እተጋለን፤ ሌት ተቀን እንሰራለን …”(ቤተመንግስት፣ ሚያዝያ 3 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: የምርጫ ህግ የማሻሻል ጉዳይ ገና አልተሞከረም::

የኢኮኖሚ ቀውስን መፍታትና ሙስናን ማስቆም

“አሁን በጀመርነው አዲስ ምዕራፍ፣ ዘረፋን፣ የሀብት ብክነትን እና የተደራጀ ሙስናን፣ መላው ህዝባችንን በሚያሳትፍ እርምጃ ለመመከት ሌት ተቀን እንተጋለን” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር: የመከላከያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽ ሜቴክ ይዟቸው የነበሩ ብክነት የታየባቸው የተወሰኑ ከፍተኛ የመንግስት ፕሮጀክቶች እንዲነጠቁ መመሪያ መተላለፉ ተሰምቷል። መሰረተ ስፊና ተቋማዊ ሙስናን የመቀልበስ እርምጃ ይፋ አልተደረገም።

“…በግብርናው ዘርፍ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት፣ በረሃዎቻችንን ወደ ገነት ለመቀየር የመስኖ ልማት ሥራዎችን በስፋትና በተቀናጀ መልኩ በመተግበር፣ የአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎችን፣ የታዳጊ ክልሎች ላይ ሠፊ ኢንቨስትመንት በማካሄድ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ተገቢውን ትኩረት ሠጥተን እንሰራለን” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : በሀገሪቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ የምግብና ሌሎች ስብዓዊ ድጋፎችን የሚፈልጉ ዜጎች አሉ። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚመሩት ኣኢህ ኣአዴግ ከዚህ ቀደም ብዙ ተግዳሮቶች የታዩበትን ግብርና ላይ ተመርኩዞ ወደ ኣኢንደስትሪ የመሸጋገር ፖሊሲውን እንደሚገፋበት ከመግለፅ ውጪ ማሻሻያም ሆነ ለውጥ ስለመኖሩ አልተነገረም።

“…ጉቦና የጥቅም ሽርክና፣ ዝምድናና አድሏዊ አሰራር ጎጂ ባሕል መሆኑን አውቆ፣ ሙያውን አክብሮ፣ ለኃላፊነቱ ክብር ሠጥቶ የሚያገለግል የመንግስት ሠራተኛና አመራር እንዲፈጠር ከመንግስት በኩል ጽኑ ፍላጎት ያለ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ ይሕን ለማሳካትም ከሚወሰዱ እርምጃዎች መካከል በዋናነት በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚደረግ ምደባ በዕውቀት፣ ክሕሎትና ችሎታ… ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛ ቦታ እንዲሰማራ በማድረግ የመንግስትን የማስፈጸም ብቃት እናሻሽላለን” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ባለስልጣናት ምደባ የብሄር ተዋፃኦና የፓርቲ ታማኝነትን ታሳቢ አድርጎ እንደሚከናወን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ይፋ ያደረጉት የአዲሱ ካቢኔ ስብጥር ያሳብቃል። ከዚህ በኋላ በመካከለኛ ደረጃ ያሉ ሀላፊዎች በዕውቀታቸው ይመደቡ ይሆን? ጊዜ ወስደን የምናየው ይሆናል። ለአሁኑ ግን የተቀየረ ነገር የለም።

“…ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የውጪ ምንዛሪ እጥረት የንግድ እንቅስቃሴ እንዲዳከም፣ መዋዕለ ነዋይ በሚያፈሱ ባለሀብቶች መካከል መተማመን እንዲቀንስ፣ የዋጋ ንረት እንዲያሻቅብ ምክንያት ሆኗል፤ በአሁኑ ወቅት በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ በስፋት እንደ መሰማራታችን መጠን የውጪ ምንዛሪ እጥረት ማጋጠሙ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ችግሩ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይወጣና ከሥር መሰረቱ እንዲቀረፍ አስተማማኝ የሆነ የገቢና ውጪ ንግድ ሥርዓት እንዲሰፍን የግብርናና ማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን በጥራትና በብዛት ወደ ውጪ ለመላክ በትጋት የምንሰራ ይሆናል” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : የገቢና የወጪ ንግዱ እንደማናቸውም ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ችግሮች ያሉበት ቢሆንም ከሁሉ በላይ በስልጣን ላይ ካለው ፓርቲ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ከፍተኛ ምዝበራና ወንጀል የሚፈፀምበት ዘርፍ ነው። ምንዛሪ ከማሸሽ እስከ ግብርና ቀረጥ ማጭበርበር በስፋት ይታያል። ለዚህ የተያዘ መፍትሄ ይኖር ይሆን ከዶር አብይ መንግስት መፍትሄውን እየጠበቅን ነው።

“…እኛ የትውስት አመራሮች ስለሆንን ባለሀብት መፍጠር፣ ሀገር መቀየርና መልቀቅ ነው፤ ምናልባት ከእኛ መካከል [ከመንግስት ሹማምንት] “የሀብታሞች ኑሮ ያማለላችሁ ካላችሁና ሀብታም መሆን የምትፈልጉ ካላችሁ ይቻላል፤ ግን ለቃችሁ በዚያኛው ወገን ተሰለፉ” ተባብለናል (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : የጠቅላይ ሚንስትር አብይ መንግስት ይህን ችግር ለመዋጋት የነደፈውን እቅድ አላቀረበም። ለእስከዛሬው ጥፋትም የተጠየቀና ህግ ፊት የቀረበ አልሰማንም።

“በእኛ በኩል የምናስተካክላቸው በጣም በርካታ ነገሮች አሉ፤ የብላክ ማርኬት መናኸሪያ እዚህ ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ መሆኑን እያወቅን ዝም ብለን ያየንበት መንገድ ይቀየራል፡፡ የኮንትሮባንድ ማከማቻዎች ጉዳይም ይቀየራል” (ሸራተን ሆቴል ፣ሚያዚያ 8 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : እስከ ሚያዚያ 18 ቀን ሐሞስ ድረስ የጥቁር ገበያ ምንዛሪ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች እንደቀጠለ ነው።

“…አሁን የውጪ ምንዛሪ ችግር አለ ብቻ ሳይሆን ብዙዎቻችሁን መጠየቅ የምፈልገው ዱባይና ቻይና ያስቀመጣችሁትን እንድትመልሱ ነው፤ እንደ መንግሥት ሳይሆን እንደ አገር ችግር አለብን፤ ውጪ ምንዛሪን በተመለከተ ሀገር ችግር ላይ ነው ያለችው፤ እናንተ ግን ከዘመድም ከአዝማድም፣ ከተቀመጠውም በከፍተኛ ደረጃ እንድትመልሱ እጠይቃለሁ፤ እንድትመልሱ ስል ያው ይገባችኋል፤ ችግር ውስጥ ነው ያለነው አግዙን፤ ብሩን ስጡን ሳይሆን መልሱት፤ አሁን ካገዛችሁን ያኔ አግዘን ነበር ብላችሁ ደግሞ አንድ ቀን ትጠይቃላችሁ፤ እናንተ ችግር ሲሆን ጠይቃችሁ፣ እኛ ስንቸገር አለን የማትሉን ከሆነ ይኼ መልካም ጉርብትናም ዝምድናም አይደለም፡፡ አንዱ አንዱ ላይ አድቫንቴጅ እየመታ ስለሚሄድ እኛንም ችግሩን ለመፍታት አያነቃቃንም፤… የኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ ችግር ተረባርበን ካልፈታነው አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ የምናደርገውን ከተሰራ በኋላ ብናገር ይሻላል”
(ሸራተን ሆቴል ፣ሚያዚያ 8 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : እስከ አሁን የተወሰደ እርምጃ የለም
የተፈናቀሉትን መልሶ ማቋቋምና ብሄር ተኮር ጥቃትን ማቆም

“…የዳበረ የዴሞክራሲ ባህል አለመኖር ፣ ሥር የሰደደ ድህነት ፣ የተደራጀ የሙስና እና ብልሹ አሰራር መስፋፋት፣ የመልካም አስተዳደር እጦት ተደማምረው ሰፊና ውስብስብ ፈተና ደቅነውብናል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ ወገኖቻችን ከመኖሪያ ቀዬአቸው ለመፈናቀል፣ ለህይወት እና ንብረት መጥፋት ተዳርገው እንደነበር ይታወሳል። ዜጎች በአገራቸው ውስጥ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር እና ሃብት የማፍራት መብታቸው መከበር አለበት፡፡ በመሆኑም እንደዚህ አይነት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እንዲያበቃና ዳግም እንዳይፈጠር መሥራት ይኖርብናል” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : ጠቅላይ ሚንስትሩ በተለያዩ ንግ ግሮቻቸው ላይ እንድነትን የሚሰብኩ መልዕክቶችን በተዋቡ ቃላትና ምሳሌዎች ከማቅረብ በዘለለ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዜጎች በብሄራቸው ምክን ያት ዒላማ እንዳይሆኑ የሚያደርግ እቅድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

“…ከሁሉ በላይ ከዚህ የተፈናቀሉ… ከዚያ የተፈናቀሉ ሰዎች ለሁላችን ቁስል፣ ለሁላችን አሳዛኝ… ድጋሚ መስማት የማንፈልገው ክስተት መሆኑን አምነን ባለን አቅም ሁሉ ተረባርበን ወደነበሩበበት እንዲመለሱ፣ ከሕዝባቸው ጋር እንዲታረቁ፣ የትናንትናውን ታሪክ በፍቅርና በአዳዲስ ድል እንዲቀይሩ የፌደራል መንግስት ከሁለቱ ክልሎች ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ በዚህ አጋጣሚ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ” (ጅግጅጋ፣ መጋቢት 28 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ ደም በተቃቡት በሶማሌና በኦሮምያም ሆነ በተለያዩ ጊዜያት በብሄር ማንነታቸው ዒላማ የተደረጉትን ማስታረቅም ሆነ ተቋማዊ በሆነ አሰራር ማቋቋም አልተጀመረም።

ወታደራዊና የደህንነት ክፍሉን በህግ ጥላ ስር ማዋል

“…የጸጥታና የደሕንነት ተቋማት ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዱ፣ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን እና የሀገር ሉዓላዊነት የሚያስብጠቁ፣ የሀገር ኩራትና መመኪያ ሆነው እንዲቀጥሉ በቅርበት እንሰራለን”
የውጪ ግንኙነት (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : በዚህ ጉዳይ ላይ አንድም የተሞከረም ይሁን የታሰበ ነገር ስለመኖሩ አልተገለፀም። በርካታ ወገኖችም የአብይ መንግስት ደህንነቱና ወታደሩን ክፍል መበወዝና ለህግ ተገዥ እንዲሆን ማድረግ ካልቻለ፣ ሌሎች ለውጦችም ስኬታማነታቸው አጠራጣሪ ነው የሚል አስተያየት አላቸው።

“… ከኤርትራ መንግሥት ጋር ለዓመታት ሰፍኖ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃም ከልብ እንፈልጋለን። የበኩላችንንም እንወጣለን፡፡ በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ ሀገር ህዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል ልዩነቶቻችንን በውይይት ለመፍታት ያለንን ዝግጁነት እየገለፅኩ የኤርትራ መንግሥትም ተመሳሳይ አቋም እንዲወስድ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : ይህ አዲስ ፖሊሲ ወይም አቋም አይደለም። የኤርትራ መንግስት በፍርድ ቤት የተሰጠኝን ግዛት ሳልረከብ አልደራደርም በሚል አቋሙ እንደፀና ነው። ጠሚር አብይ አንድም አዲስ አማራጭ ማቅረብ ወይም የኤርትራን መንግስት አሳምነው ወደ ድርድር ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ትምህርት፣ ስራ አጥነትና ሴቶች

“…የትምህርት መስፋፋት ይበል የሚያሰኝ የመንግሥታችን ስኬት ቢሆንም ይህ የትምህርት ሽፋን ዕድገት በጥራት እስካልተደገፈ ድረስ ልፋት ጥረታችን ሁሉ የምንተጋለትን ውጤት ሊያመጣልን አይችልም። በመሆኑም ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉትን የእውቀት አለሞቻችንን በጥራት ላይ አትኩረው እንዲሰሩ መንግሥት በፍጹም ቁርጠኝነት ይረባረባል”(ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : እስካሁን የቀረበ እቅድ የለም።

“…ኢትዮጵያ ለወጣቶቿ ተስፋ የምትሰጥ እንጂ፣ ተስፋ የምታስቆርጥ አገር እንዳትሆን የምንችለውን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባለሁ፡፡ በሚቀጥሉት ጊዜያት ለወጣቱ የሥራ ዕድል መፍጠር ብቻ ሳይሆን ወጣት ባለሀብቶች በብዛት እንዲፈጠሩ እንሰራለን፡፡ ለዚህ እንቅፋትና መሰናክል የሚሆኑ አመለካከቶችና የተንዛዙ አድሏዊ የሆኑ አሰራሮችን አስወግደን ፍትሃዊ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት እንዲኖረን መንግሥት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : እስካሁን የቀረበ እቅድ የለም።

“…መንግሥታችን ከዚህ ቀደም ከነበረው ፍጥነት እና የትግበራ ስኬት በላቀ መልኩ ለሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት ይሰራል።” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : በሚንስትር ደረጃ ከተቀመጡት ሴቶች በቀር የሴቶችን ተሳትፎ ዋስትና የሚሰጠው እቅድ ወደፊት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

“…ሥራ አጥነት ወጣቶቻችንን ለወንጀል፣ በሱስ ለመጠመድ እንዲሁም ለስደት ሲዳርግ ተስተውሏል፡፡ ይሕንን ሁኔታ ለመቀየር መንግስት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : እስካሁን የቀረበ እቅድ የለም።

“…ለሁላችንም የምትበቃ በዚያው ልክ ግን የሁላችንንም ተሳትፎ የምትፈልግ ሀገር አለችንና ዕውቀታችሁንና ልምዳችሁን ይዛችሁ ወደሀገራችሁ መመለስና ሀገራችሁን አልምታችሁ መልማት ለምትሹ ሁሉ እጃችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን፡፡ በውጪ ሀገራት ኑሯችሁን ላደረጋችሁትም ቢሆን በማንኛውም መልኩ በሀገራችሁ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑና ሀገራችንን በሁሉም መልክ ለመቀየር ለምታደርጉት አስተዋጽኦ መንግሥት ያልተቆጠበ ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል” (ፓርላማ መጋቢት 24 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : ይህ በሀገራዊ እርቅና ሽምግልና መደገፍ ያለበት ቃል ኪዳን ይመስላል። እስካሁን በባህር ማዶ ያሉና የፖለቲካ ልዩነት ያላቸውን ወገኖች ዋስትና የሚሰጥ ድባብ አልተፈጠረም። ይህ ጊዜ ሊወስድ የሚችል ዕቅድ ነው።

“…መንግስት የሕዝባችንን ሁሉን አቀፍ ጥንካሬ መሰረት በማድረግና የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ሀገራዊ አንድነታችንን ይበልጥ ለማጎልበት በጽናት እንደሚሰራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ” (ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ሚያዝያ 7 ቀን)

ባለፈው አንድ ወር : ጠሚር አብይ እስካሁን ያደረጓቸው ንግግሮች ከበቂ በላይ አንድነትን የሚያጎለብቱና ቅን ናቸው። ይህን ቅን ሀሳብ ከስሜት በዘለለ በየደረጃው ለማስፈፀም የሚረዳ ስትራቴጂና ግብ አልተቀመጠም። ከገዥው ፓርቲ ርዕዮተ አለም ጋርስ እንዴት እንደሚጣጣም መፈተሽ አለበት። [ዋዜማ ራዲዮ] -ይህን ዘገባ በድምፅ ለማግኘት ይህን ማስፈንጠሪያ ይከተሉ- Click

The post አብይ ሲለካ.. የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አንድ ወር ! appeared first on Wazemaradio.

[…]

U.N. Rights Chief Urges New Leadership in Ethiopia to Improve Human rights

UN Human Rights chief, Zeid Ra’ad Al Hussein (L), discussing with Ethiopia’s newly elected PM Abiy Ahmed

By Dawit Kebede

Awramba Times (Addis Ababa) – UN High Commissioner for Human Rights, Zeid Ra’ad Al Hussein, who was in Ethiopia following the nation’s historic transition of power, arged the new leadership of PM Abiy Ahmed to take the initiatives of improving human rights situations in the horn Africa nation.

During his official visit in Ethiopia from April 14 – 17, 2018, the High Commissioner held talks with the newly elected Prime Minister of Ethiopia Abiy Ahmed, Foreign Minister Workneh Gebeyehu, newly appointed Speaker of the House Muferihat Kamil, Ethiopian Human Rights Commissioner, Officials from Oromia Regional State, Addis Ababa University community and different parts of the society in and outside the capital Addis Ababa.

“We all want to see an Ethiopia with continuous economic development where all people benefit, and where people express their views on public policies, unafraid,” said UN Human Rights chief Zeid Ra’ad Al Hussein at the end of his official visit.

Ethiopia has been riven by human rights violations and oppression on protests in Oromia and Amhara regions by those demanding equality in the last three years.

“Moments of transition are rarely ever smooth. Ethiopia has struggled with a heavy history, but it has the wisdom of a tolerant, vibrant, youthful population to harness,” said Mr. Zeid, encouraging the authorities to keep the positive momentum going and to keep translating the inspiring words in the Prime Minister’s inaugural address into action.

The High Commissioner added that, following the inaugural speech of the Premier, he was “deeply impressed” by the renewed interest, hope and commitment all Ethiopians have demonstrated. This renewed feeling of the People would give further impetus to Government’s ongoing efforts to bring about social justice in the country, he underlined in his his exclusive interview with the state run, Ethiopian television, at the end of his visit.

The High commissioner added, he has reitaterated that he has taken pleasure with the idea that the speech by Prime Minister Abiy fully embraced the basic Declaration of Human Rights.

While discussing with PM Abiy, Zeid Al Hussien noted he has visited several regions of the country and has been able to witness a new chapter unfolding in the development of human rights and democracy in Ethiopia.

Expressing his contentment for being able to visit areas outside Addis without any restrictions, High Commissioner Zeid noted his talks particularly with Aba Gaddas and Officials of Bishoftu confirmed the longstanding Ethiopian culture of democracy that has transcended millennia.

The High Commissioner pledged to support the Government of Ethiopia in its commitment to fulfill the high demands of the wider public for a fast-paced transformation, giving due emphasis to technical and institutional capacity building of the Government, particularly in the field of human rights protection.

The United Nations Human Rights Council has signed a Memorandum of Understanding (MoU) to open a Regional Office in Addis that covers 17 Eastern and South African countries. The agreement was signed by Foreign Minister Workneh Gebeyehu and the High Commissioner.

While noting the deep-seated interest to further enhance relations between the African Union and the U.N. Prince Zeid has underscored that Comments and Reports on Africa should fully consider the full dignity of the continent. Zeid said this during the 1st African Union (AU) and the United Nations (UN) High Level Dialogue on Human Rights held this week at the AUC Hall.

“In this 70th anniversary year of the Universal Declaration of Human Rights, when too many leaders risk reversing hard-won human rights gains, we look to Ethiopia to continue to give cause for optimism and hope,” Mr. Zeid said.

[…]

Uber driver, 46, who asked a lesbian passenger how she had sex with her girlfriend is fined $300

Umar Subi Gammeda made an inappropriate remark to a Brisbane passenger The Ethiopian national had been giving a lift to Fortitude Valley in August 2017 His female passenger, 25, had told him she was gay during chat about marriage The Uber driver, 46, told her homosexuality wasn’t condoned in his home nation By Australian Associated Press […] […]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.