Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

የትግራይና የአማራ ክልል የሚወዛገቡባቸውን አካባቢዎች በተመለከተ በሚቀጥሉት ቀናት የሚከተሉት እርምጃዎች ይወስዳሉ

ዋዜማ- የወሰን ይገባኛል የሚነሳባቸውን አካባቢዎች (የራያ ፣ ጠለምት እና ወልቃይት) በተመለከተ የትግራይና የአማራ ክልል አመራሮች የፕሪቶሪያውን የሰላም ውል ተንተርሰው በደረሱት የመተግበሪያ ስምምነት መሰረት ታጣቂዎችን ማስወጣት ተፈናቃዮችን መመለስና አዲስ የአስተዳደር መዋቅር መዘርጋትን ጨምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ለማድረግ መታቀዱን ዋዜማ ስለጉዳይ ከሚያውቁ መንግስታዊ ምንጮች ያገኘችው የሰነድ መረጃ ያመለክታል።

የወሰን ውዝግቡን ለመፍታት የተሰየመው ብሄራዊ ኮሚቴ በቅርቡ ባደረገው ምክክር በደረሰው ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስት መከላከያ ፀጥታውንና ሂደቱን የማስተባበር ኃላፊነት ይረከባል።

ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ መኖሪያቸው ያለቅድመ ሁኔታ መመለስ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ያሰመረበት መርሀግብሩ የትግራይ ክልል የተፈናቃዮችን ቁጥርና ዝርዝር አሰናድቶ ለመከላከያ እንዲያቀርብ፣ ከተመላሾች መካከል በወንጀል የሚጠረጠሩ ወደ መኖሪያቸው መመለስ እንደማይከለከሉና የተጠረጠሩበት ወንጀል ካለ በተናጠል የሚታይ እንደሆነ ያትታል።

ማናቸውንም የወንጀል ድርጊት ክስ የፌደራል መንግስቱ በሂደት የሚመለከተው ይሆናል።

የቀደመ መኖሪያቸው በአወዛጋቢዎቹ አካባቢዎች የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ታጣቂዎች እና ሚሊሻ እንደታጣቂ ሳይሆን እንደተፈናቃይ ወደ ቦታቸው መመለስ እንደሚችሉም ከስምምነት ተደርሷል።

የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች በአማራ ክልል የተመሰረቱ የአስተዳደር እና የፀጥታ መዋቅሮች ይፈርሳሉ።

ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከአካባቢው የሚወጡ ሲሆን የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት ደግሞ እንደታጣቂ ሳይሆን እንደ ነዋሪ መቆየት እንዲችሉ በብሄራዊ ኮሚቴው ስምምነት ተደርሷል።

ከጦርነቱ ተከትሎ የተፈጠሩ የአስተዳደር መዋቅሮች ሲፈርሱ የንብረትና የሰነድ መጥፋት እንዳይኖር መከላከያ ሰራዊት ጉዳዩን ተረክቦ አዲስ ለሚቋቋመው አስተዳደር እንዲያስረክብ ሀለፊነት ተሰጥቶታል።

በዕቅዱ መሰረት ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው ከተመለሱ በኃላ ሁሉን ያካተተ የቀበሌ አመራር ምርጫ ይደረጋል። የቀበሌ አመራሮች የወረዳ አመራሮቻቸውን ይመርጣሉ።

የአካባቢው አስተዳደር በምርጫ ከተሰየመ በኃላ የፌደራል መንግስት በጀት እንደሚመድብላቸው ስምምነቱ ያብራራል።

ይህ ከተፈፀመ በኋላ በአመቺ ጊዜና ነባራዊ ሁኔታው ተገምግሞ በአካባቢው ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ታቅዷል።

የራያ እና ጠለምት አካባቢዎች ጉዳይን በቅድሚያ በመፍታት የወልቃይት ጉዳይ ይህንን ተከትሎ በተመሳሳይ እንዲፈታ ለማድረግ አስፈፃሚ ቡድን ተቋቁሞ ስራውን እንደሚያከናውን ብሄራዊ ኮሚቴው ከስምምነት ደርሷል።

ከሁለቱ ክልልሎች የተውጣጣ ግብረ ሀይል በአፈፃፀሙ ላይ በታዛቢነት የሚሳተፍ ሲሆን ጉድለቶችንና የማሻሻያ ሀሳቦችን በግብረመልስ የሚያቀርብ ይሆናል።

ይህ ስምምነት በተደረስ በቀናት ውስጥ በራያ፡ አላማጣ በኩል የትግራይ ኀይሎች ከአማራ ክልል ሚሊሻ ጋር የተጋጩ ሲሆን ሁለቱ ክልሎች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ሰንብተዋል።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለዋዜማ እንደነገሩት፣ ይህን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት መፈፀም ይጀምራሉ። [ዋዜማ]

The post የትግራይና የአማራ ክልል የሚወዛገቡባቸውን አካባቢዎች በተመለከተ በሚቀጥሉት ቀናት የሚከተሉት እርምጃዎች ይወስዳሉ first appeared on Wazemaradio.

The post የትግራይና የአማራ ክልል የሚወዛገቡባቸውን አካባቢዎች በተመለከተ በሚቀጥሉት ቀናት የሚከተሉት እርምጃዎች ይወስዳሉ appeared first on Wazemaradio.

[…]

ጠቅላይ ሚንስትሩ የተቃዋሚ  ፓርቲ አባላትን ለውይይት ጋበዙ፣ ፓርቲዎቹ ስልጠናም ይወስዳሉ ተብሏል

ዋዜማ- የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ መያዛቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሁሉንም አገር አቀፍ እና ክልል አቀፍ ፖለተካ ፓርቲዎችን ለማወያየት ወደ አዲስ አበባ አስጠርተዋል።

ለአገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ጸሐፊ ወይም የጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና ሦስት የሥራ አስፈፃሚ አባላት በድምሩ ስድስት ተወካዮች እንዲሳተፉ እድል ተሰጥቷቸዋል።

ከክልላዊ ፓርቲዎች ደግሞ ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ጸሐፊ ወይም የጽሕፈት ቤት ኃላፊ በድምሩ ሦስት ሰዎች ተጋብዘዋል፡፡

ዐቢይ ለውይይት የጠሯቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች የሦስት ቀን ፕሮግራም እንደተያዘላቸው ዋዜማ ለፓርቲዎች ከደረሰው ፕሮግራም ተመልክታለች።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመወያየት የሚገኙ የፓርቲ መሪዎች በቅድሚያ፣ ነገ ⁠እሁድ መጋቢት 22/2016 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዋና ዋና የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ።

ከጉብኝቱ በኋላ የፊታችን ⁠ሰኞ መጋቢት 23/2016 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ውይይት ያደርጋሉ። በሦስተኛው ቀን ፕሮግራም ማክሰኞ መጋቢት 24/2016 ዓ.ም ስልጠና ይወስዳሉ።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሚደረገው ውይይት ላይ እንዲሳተፉ የቀረበላቸውን ግብዣ ውድቅ ያደረጉ ፓርቲዎች መኖራቸውን ዋዜማ ሰምታለች።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በማካሄደውን ውይይት አንሳተፍም ካሉት መካከል፣ አብዛኛዎቹ “የፖለቲካ ፓርቲዎች ኮከስ” የተሰኘው የተፎካካሪ ፓርቲዎች ስብስብ አባላት ናቸው።

በአሁኑ ወቅት 13 አባላት ያሉት ስብስቡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሚደረገው ውይይት ተሳትፎ ላይ የጋራ አቋም መያዙን የኮከሱ አባላት ለዋዜማ አረጋግጠዋል።

የኮከሱ አባል ፓርቲዎች በውይይቱ ላይ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን፣ የኦከሱ አባል የሆነው የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ ለዋዜማ ተናግረዋል። የስብስቡ አባል ፓርቲዎች በጉዳዩ ላይ ተሰብስበው የመከሩ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይ የተገኙት ዘጠኝ ፓርቲዎች የውይይት ተሳትፎውን ውድቅ አድርገዋል ተብሏል።

ምንም እንኳን የኮከሱ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ለማድረግ የቀረበውን ግብዣ ውድቅ ቢያደርጉም፣ ልዩ የፓርቲ ጉዳይ ያላቸው አባላት መሳተፍ እንዲችሉ ስምምነት ላይ መደረሱን ግርማ ጠቁመዋል።

ፓርቲዎቹ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመወያየት ፈቃደኛ ያልሆኑት፣ “መንግሥት ለይስሙላ አወያየሁ ከማለት የዘለለ” የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ሀሳብ የመቀበል ፍላጎት የለውም በማለት መሆኑን ገልጸዋል።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ሦስት የፓርቲ መሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የሚደረገው ውይይት፣ “የተለየ ነገር አይፈጥርም” የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል። ለዚህም እንደ ምክንያት ያቀረቡት ከዚህ ቀደም በተለይ በሰላም ጉዳይ ተደጋጋሚ የመፍትሔ ሀሳብ አቅርበው፣ በመንግሥት በኩል እንደ አማራጭ ከመቀበል ይልቅ በተደጋጋሚ ገፍቶናል የሚል ነው።

በፕ/ር መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ ሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ ሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ፣ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲ ግንባር (ዎሕደግ)፣ አገው ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲና ሌሎችም የኮከሱ አባላት ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት የክልሎች ተወካዮችን፣ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶችን፣ ባለ ሀብቶችንና ሴቶችን በየተራ አወያይተዋል። [ዋዜማ]

The post ጠቅላይ ሚንስትሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ለውይይት ጋበዙ፣ ፓርቲዎቹ ስልጠናም ይወስዳሉ ተብሏል first appeared on Wazemaradio.

The post ጠቅላይ ሚንስትሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ለውይይት ጋበዙ፣ ፓርቲዎቹ ስልጠናም ይወስዳሉ ተብሏል appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopia: No Hotels Achieve 5-Star Rating in Latest Evaluations

Ministry of Tourism Logo 11

Ethiopia’s Ministry of Tourism recently announced the results of hotel evaluations. Disappointingly, none of the 64 establishments assessed achieved the coveted 5-star rating. This follows a similar trend in 2022 and 2023, where evaluations of the same number of hotels yielded no 5-star designations.

[…]

Ethiopia: Four Companies Awarded Mining Licenses

Ministry of Mines Logo

Ministry of Mines announced the awarding of mining licenses to four companies. The signing ceremony was attended by Minister of Mines Habtamu Tegegn and company executives.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data – 28 March 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 28 March 2024.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data – 27 March 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 27 March 2024.

[…]

Ethiopia: National Bank Unveils Plans for New Bank Law and Granting Fintech Licenses

NBE Logo

Ethiopia’s National Bank Governor, Mamo Mehretu, highlighted the transformative potential of digital financial services during a recent panel discussion on the Digital Ethiopia 2025 strategy review. His focus was on the upcoming changes driven by new regulations and increased competition.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data – 26 March 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 26 March 2024.

[…]

Ethiopia, Pan African Federation of Accounting Team Up to Strengthen Accounting Practices

AABE Logo

The Accounting and Auditing Board of Ethiopia (AABE) joined forces with the Pan African Federation of Accounting (PAFA) to host a “Quality Assurance Review Workshop.” This initiative aims to elevate accounting and auditing standards across Africa.

[…]

Ethiopia: Djibouti Restricts NVOCCs as Multimodal Operators

Multimodal Djibouti

Djibouti threw a curveball at Ethiopia’s plan to expand multimodal transport options. Djibouti banned non-vessel operators (NVOCCs) from acting as multimodal operators, despite Ethiopia approving three new companies for the role. Djibouti worries NVOCCs cannot guarantee logistics costs or ensure cargo safety.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.