Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

ለዛሬ ታቅዶ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኞች ምዘና ፈተና ተሰረዘ

Adanech-Abebe

ዋዜማ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራተኞቹ ዛሬ ሊሰጠው አቅዶ የነበረው አወዛጋቢው የመጀመሪያ ዙር የብቃት መመዘኛ ፈተና ባልታወቀ ምክንያት መሰረዙን ዋዜማ ሰምታለች።

ለፈተና የተመረጡት ሠራተኞቹ በአውቶቡስ ወደ ፈተና ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ሲጠባበቁ እንደነበር ለዋዜማ ተናግረዋል።

ዳግማዊ ሚኒልክ ት/ቤት የፈተና ጣቢያ ሊፈተኑ የነበሩ አንድ ሰራተኛ የተወሰኑ ሰራተኞች ስም ዝርዝር ብቻ በመፈተኛ ክፍሎች እንደተለጠፈ ለዋዜማ ገልጸዋል። ፈተናው ሊሰጥባቸው በነበሩ ሌሎች ሶስት ቦታዎችም መሰረዙን ከተፈታኞች ስምተናል።

በቦታው ፖሊሶች ብቻ ስለነበሩ ለምን እንደተሰረዘ የሚናገር አካል እንዳልነበርም ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ፣ የብቃት መመዘኛ ፈተናውን የሚሰጠው አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ ጥናት ባደረጉት የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች እንደሆነ ገልፆ ነበር። ስለምዘናው ዝርዝር መረጃ በዚህ ማስፈንጠሪያ ያገኛሉ

በትናትናው ዕለት ተቃዋሚው እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች ሊሰጠው ያቀደው ምዘና እንዲኹም በምዘናው የሚሰጠው የሠራተኞች ምደባ ባስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል።

ፓርቲው፣ ፈተናና ምዘናው መንግሥት የማይፈልጋቸውን ሠራተኞች በማስወገድ የሚፈልጋቸውን ለመተካት ኾን ብሎ ያዘጋጀው ስልት መኾኑን ለመገመት አያዳግትም ብሏል። ከፈተናው በፊት የፈተናው መልስ በየትምህርት ቤቶች አስቀድሞ ተለጥፎ መገኘቱን ከመረጃ ምንጮቹ መረዳቱን የጠቀሰው ፓርቲው፣ ይህን ተከትሎ ፈተናው ለጊዜው መቋረጡን እንደደረሰበት ገልጧል።

ፓርቲው፣ በአዲስ አበባ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እየሠሩ የሚገኙ ሠራተኞች የብሄር ማንነታቸውን እንዲሞሉ የሚያስገድደው ቅጽ ባስቸኳይ እንዲቆምም ፓርቲው ጠይቋል። በዚኹ መግለጫው፣ የከተማዋ አስተዳደር ሠራተኞች የፈተና አሰጣጡን፣ ምደባውንና “ብሄር” የሚጠይቀውን ቅጽ በሰላማዊ መንገድ እንዲቃወሙ ፓርቲው ጥሪ አድርጓል። [ዋዜማ]

To reach Wazema editors, you can write to wazemaradio@gmail.com

The post ለዛሬ ታቅዶ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኞች ምዘና ፈተና ተሰረዘ first appeared on Wazemaradio.

The post ለዛሬ ታቅዶ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የሰራተኞች ምዘና ፈተና ተሰረዘ appeared first on Wazemaradio.

Source:: https://wazemaradio.com/%E1%88%88%E1%8B%9B%E1%88%AC-%E1%89%B3%E1%89%85%E1%8B%B6-%E1%8B%A8%E1%8A%90%E1%89%A0%E1%88%A8%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B/?utm_source=rss&utm_medium=rss&utm_campaign=%25e1%2588%2588%25e1%258b%259b%25e1%2588%25ac-%25e1%2589%25b3%25e1%2589%2585%25e1%258b%25b6-%25e1%258b%25a8%25e1%258a%2590%25e1%2589%25a0%25e1%2588%25a8%25e1%258b%258d-%25e1%258b%25a8%25e1%258a%25a0%25e1%258b%25b2%25e1%2588%25b5-%25e1%258a%25a0%25e1%2589%25a0%25e1%2589%25a3-%25e1%258a%25a8%25e1%2589%25b0%25e1%2588%259b

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.