Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

በሙስና ተጠርጥዋል የተባሉ ግለሰቦችንና ባለስልጣናት የማሰር ዘመቻው ቀጥሏል- ተጨማሪ ከፍተኛ ነጋዴዎችና ባለስልጣናት እስሩን ይቀላቀላሉ

ትናንት ማምሻውን ቦሌ የባለሥልጣናት መንደር ግርግር ተፈጥሯል ደኅንነት መሥሪያ ቤት ባልደረቦች መሐል አለመግባባት እንዳለ እየተነገረ ነው፡፡ ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ትናንት ሊሰጠው የነበረውን መግለጫ ተሰርዟል ዛሬ ረፋድ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጌታቸው አምባዬ ከጋዜጠኞች ጋር ይገናኛሉ

ዋዜማ ራዲዮ- በከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው የሚታሰሩ የመንግሥት ኃላፊዎች ቁጥር ወደ 40 ማሻቀቡን ተከትሎ ትናንት ማምሻውን ቦሌ ኖቪስ ራማዳ ሆቴል ጀርባ በልዩ ኃይሎች ተከቦ ነበር፡፡ ዋዜማ የሰፈሩን ነዋሪዎች የአይን እማኝነት በመንተራስ ባገኘችው መረጃ ብርበራ ለማካሄድ በመጡ የልዩ አቃቤ ሕግ ባልደረቦችና በድኅነነት መሥሪያ ቤት ባልደረቦች መሐል መነሻው ያልታወቀ አለመግባባት ተፈጥሮ ቆይቷል፡፡ ፍጥጫው በግምት ለ45 ደቂቃቆች ከቆየ በኋላ መንገዱ ለተሸከርካሪዎች ክፍት ተደርጓል፡፡ ኾኖም ዋዜማ የየትኛውም ባለሥልጣን መኖርያ ቤት ሲበረበር ይህ ችግር ሊፈጠር እንደቻለ መረጃ ማግኘት አልቻለችም፡፡

በአካባቢው እስከ አትላስ በሚዘልቀው መንገድ ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ጨምሮ ከ12 የማያንሱ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግሥት ሹመኞች መኖርያ ቤት ይገኛል፡፡

ለደኅንነት መሥሪያ ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት ‹‹ቅድሚያ ማን ይታሰር፣ ማን ይቆይ›› በሚለው ጉዳይ ደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ዉስጥ ባሉ ኃላፊዎች ወጥ አቋም አይታይም፡፡ በአቃቤ ሕግና በደህንነቱ ኃይሎች መካከልም የእዝ ሰንሰለቱ ላይ መግባባቱ እምብዛምም ነው፡፡

ይህ በእንዲህ ሳለ ትናንት አርብ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በቀናት ልዩነት አዲስ መግለጫ ለመስጠት ጋዜጠኞችን ጠርተው የነበሩት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ጋዜጠኞች ቦታው ከደረሱ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት መግለጫውን ሰርዘውታል፡፡ ጋዜጠኞች ከተበተኑ በኋላም የልዩ አቃቤ ሕግ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አምባዬና ባልደረቦቻቸው በተጠርጣሪዎች ጉዳይ ሰፋ ያለ መግለጫ እንደሚሰጡ ተነግሮ ጋዜጠኞች ለዛሬ ቅዳሜ አራት ሰዓት ተመልሰው እንዲመጡ ተነግሯቸዋል፡፡

ዋዜማ ባገኘቸው ሌላ ተጨማሪ መረጃ በሳምንታት ዉስጥ ከ50 የማያንሱ የነጋዴው ማኅበረሰብ አባላት የእስር ዘመቻውን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ በፋይናንስ ደህንነት መሥሪያ ቤት፣ በገቢዎችና ጉምሩክ፣ በዋናው ኦዲተር እንዲሁም ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ባልደረቦች የተውጣጣ ኮሚቴ ከ120 በላይ ነጋዴዎችን በተጠርጣሪነት በጥቁር መዝገቡ አስፍሯል፡፡ ለወራት ያህልም የሂሳብ ባለሞያዎቻቸውን በመጥራት፣ ስልካቸውን በመጥለፍ፣ ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ መረጃ ሲያሰባስብ እንደነበር ተነግሯል፡፡ ከነዚህ መሐል በመጀመርያ ዙር የእስር ማዘዣ ይወጣባቸዋል ተብለው የሚገመቱት 18 የሚሆኑ ከፍተኛ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ የብዙዎቹ ክስ ከታክስ ስወራ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡

The post በሙስና ተጠርጥዋል የተባሉ ግለሰቦችንና ባለስልጣናት የማሰር ዘመቻው ቀጥሏል- ተጨማሪ ከፍተኛ ነጋዴዎችና ባለስልጣናት እስሩን ይቀላቀላሉ appeared first on Wazemaradio.

[…]

አዲሱ የአሜሪካ ምክርቤት ረቂቅ ሕግ በህወሓት ባለሥልጣናትና ቤተሰቦች ላይ ጭንቀት ፈጥሯል

ትላንት በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ የፀደቀው ረቂቅ ሕግ በህወሓት ባልሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ሥጋት፥ ፍርሃትና ጭንቀት መፍጠሩ ተሰማ። ረቂቅ ሕጉን ገና ከአወጣጡ ጀምሮ ሲከታተሉና ግብዓት ሲሰጡ የቆዩ ወገኖች እንደሚሉት ይህ ያሁኑ ረቂቅ ሕግ የህወሓት ሰዎች አንገት ላይ ገመዱን ያስገባ ነው። ኢትዮጵያውያንን በመግደል፥ በማሰቃየትና በማንኛውም መልኩ የሰብዓዊ መብቶቻቸውን በመርገጥ ስማቸው የሚገኝ የህወሓት […] […]

Ethiopia Made 3.3 Billion USD from Tourism

In the just ended fiscal year, Ethiopia generated 3.3 billion USD from tourists that came to visit the country. This was disclosed by the Ministry of Culture and Tourism.

[…]

ኦነግን በመቀላቀል ስልጠና ለመውሰድ አስበው ነበር የተባሉ ወጣቶች ተከሰሱ • ከተከሳሾቹ መካከል የ16 አመት ታዳጊ ይገኝበታል

ኦነግን በመቀላቀል ስልጠና ለመውሰድ አስበው ነበር የተባሉ ወጣቶች ተከሰሱ

• ከተከሳሾቹ መካከል የ16 አመት ታዳጊ ይገኝበታል

(በጌታቸው ሺፈራው)

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኦነግን በመቀላቀል ወታደራዊና ፖሊቲካዊ ስልጠና ሊወስዱ አስበው ነበር በሚል በ5 ወጣቶች ላይ የሽብር ክስ መስርቷል፡፡ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ …

[…]

የመቐለ ከነማ ደጋፊዎች እየታሰሩ ነው !

የመቐለ ከነማ ደጋፊዎች እየታሰሩ ነው !
÷÷÷÷÷÷÷ Amdom G/Slassie…. Arena ….

የመቐለ ቡድን ደጋፊዎች በድህንነት እየታደኑ እየታሰሩ ነው። እስካሁን 61 ዋናዋና ደጋፊዎች ናቸው የተባሉ ወጣቶች ታስረዋል።

የእስራቸው ምክንያት መቐለ ስቴድዮም ቡዱናቸው ለመቀበል በተዘጋጀው ስነስርዓት ላይ ኣባይ ወልዱ፣ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ …

[…]

አቶ ዳንኤል ሺበሺ ይግባኝ በተጠየቀበት የሽብርተኝነት ክስ ነፃ ተባለ !

አቶ ዳንኤል ሺበሺ ይግባኝ በተጠየቀበት የሽብርተኝነት ክስ ነፃ ተባለ !


[ 3ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃ ደስታ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤቱ ጥሪ ቢያቀርብለትም፣ ታስሮ እንዲቀርብ ትእዛዝ ቢሰጥም ተከሳሽ መቅረብ ባለመቻሉ ክስ እንዲቋረጥ በማለት ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል ]

በእነ ዘላለም …

[…]

ዋናዎቹ “መዥገሮች” ትንንሾቹን ነቀሉ!

ህወሓት/ኢህአዴግ በራሱ ጉባዔ (ፓርላማ)፣ በራሱ ባለሥልጣናት፣ በራሱ ፈቃድ፣ በራሱ በሚተዳደረው ሚዲያ፣ ፈቅዶም ሆነ ሳይፈቅድ በሚገዛለት ሕዝብ ፊት ይፋ ያደረገው የስኳር ፕሮጀክት ዝርፊያ በራሱ አስፈላጊ ርምጃ ለመውሰድ በቂ ሆኖ ሳለ ሙስናን በመታገል ስም እስካሁን መቆየቱ በራሱ አነጋጋሪ ነው፡፡ ምክንቱም አፈቀላጤ ነገሪ ሌንጮ እንዳለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ደሙን የሚጠጡት የበላይ ኃላፊዎች እነማን እንደሆኑ ፍንትው አድርጎ […] […]

የህወሃት/ኢህአዴግ ሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ከሒዝቦላና ሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ጋር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አገኘ

የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት አልፏል። ከውሳኔው በላይ የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሕዝብን ለመከራና ስቃይ ሲዳርግ የኖረው የኢህአዴግ አገዛዝ በአሻባሪነቱ ከሚወገዘው ሒዝቦላ እና ከሰሜን ኮሪያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ጋር በእኩል ቀርቦ መታየቱ “የአሜሪካና ኢህአዴግ ወዳጅነት ወዴት?” አስብሏል፡፡ በዕለቱ ዘጠን አጀንዳዎች ለውሳኔ […] […]

የፋሽስት ወያኔ ስም ከሒዝቦላ ጋር መነሳቱ ይበዛበታል! ( አቻምየለህ ታምሩ )

የፋሽስት ወያኔ ስም ከሒዝቦላ ጋር መነሳቱ ይበዛበታል!

( አቻምየለህ ታምሩ )

በዛሬው እለት በተካሄደው የአሜሪካ የሕግ መመሪያ የውጭ ጉዳይ ኮምቴ ጉባኤ የወያኔዋ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ የአገዛዙ ባህሪ ተገምግሞ የፋሽስት ወያኔ ስም አሜሪካ በአሸባሪነት ከፈረጀችው ከሊባኖሱ የሺዓ ቡድን ከሒዝቦላ …

[…]

Ethiopia to Issue National ID to Rastafarian Community and Ethiopian Jews

Meles Alem, spokesperson of the ministry of foreign affairs

Awramba Times (Addis Ababa) – The Foreign Affairs Ministry of Ethiopia, in collaboration with the National Intelligence and Security Service of Ethiopia will issue national identity cards for the Rastafarian Community who long have been seen as stateless in the Ethiopia, the Associated Press reported.

The decision means they can enter without visas and live without residence permits. The move also affects Ethiopian Jews and foreign nationals who have made positive contributions to the country.

“These individuals have long been unable to enter and leave the country easily,” Foreign Ministry spokesman Meles Alem was quoted as saying by the Associated Press. “In the case of Rastafarians, we have three generations of people residing here that have blended well with our citizens. But sadly they were neither Caribbean nor Ethiopians so were somehow stateless. This national ID will address this problem.”

Close to one thousand Rastafarians live in Ethiopia, especially in the capital, Addis Ababa, and a southern town called Shashamane. Ethiopia’s last emperor, Haile Selassie, granted land for the Shashamane settlement for black people who helped fight off Fascist Italian forces in the 1930s.

Rastafarianism, which began after the emperor came to power, has followers who believe he is god.

“We are overjoyed,” Ras King, a prominent member of the Rastafarian community who first came to Ethiopia in 1982 told AP. “We are extremely happy because this has fulfilled our confidence in our forefathers’ vision for a united Africa and black people from the West. As usual, Ethiopia has led the way and set the example for the rest of the continent in recognizing the Rastafarian movement.”

Ethiopian Jews, also known as Beta Israel, have a significant presence both in Ethiopia and in Israel.

The foreign ministry said the thousands of people who will be issued the new identity cards still cannot take part in elections or engage in the country’s security and defence sectors.

Members of the Rastafarian community in the town of Shashamane in Southern Ethiopia

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.