Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

2017/18: An Exceptional Year for Ethiopian Airlines

Ethiopian Airlines, Africa’s largest Airline Group, is happy to announce that it has registered record success in the just ended 2017/18 fiscal year. In line with its 15 year strategic road map, Vision 2025, the airline registered historical success in financial, commercial, operational and customer service areas. During the 2017/18 fiscal year: Ethiopian introduced additional +14 new […] […]

Ethiopian and DHL Global Forwarding Partner to Build the Leading Cargo Logistics Provider JV Company in Africa

DHL Global Forwarding, the leading international provider of air, sea and road freight services, and Ethiopian Airlines, the largest aviation group in Africa, today signed a new agreement to form a joint venture company – DHL-Ethiopian Airlines Logistics Services Ltd., to build the Leading Cargo Logistics provider JV company in Africa; the company will be based in Ethiopia and do business in the entire continent of Africa, enhancing Ethiopia’s logistics infrastructure and connections.

[…]

የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ወደብ አጠቃቀም የሚያጠና ቡድን አቋቋመ

Massawa

ዋዜማ ራዲዮ- በቀድሞ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራ ቡድን ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች የምትጠቀምበትን ሁኔታ ማጥናት እንደጀመረ ከኢትዮጵያ የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሁለት ሳምንታት በፊት በሀገሪቱ ካሉ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ባደረጉት ቆይታ ሀገሪቱ አሁን ላይ የምጽዋ ወደብን በተቻለ ፍጥነት ወደመጠቀም እንደምትገባም ተናግረው ነበር ።
አሁን ላይም ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች የምትጠቀምበትን ሁኔታ አስመልክቶ ጥናት የሚያደርግ የተለያዩ ዘርፍ ባለሙያዎችን የያዘ የጥናት ቡድንን የቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አምባሳደር ግርማ ብሩ እየመሩት ነው ።
በጥናቱ ውጤት ላይም ኢትዮጵያ ምጽዋና አሰብን ስትጠቀም ምን አይነት ስትራቴጂ ይኖራታል ? ሁለቱ ሀገራትስ ከወደብ አንጻር ምን አይነት ግንኙነት ነው የሚኖራቸው ? የሚለው ጉዳይ ግልጽ ተደርጎ እንደሚቀመጥም ምንጮቻችን ነግረውናል ።

ይህም ብቻ ሳይሆን ወደቦቹን መጠቀም ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸውስ ምን ይመስላል ? የሚለው ጉዳይም እየተፈተሸ እንደሆነ ምንጮቼ ነግረውኛል ።
የጥናቱን ሂደት ከሚያውቁ ባለሙያዎች እንደሰማነው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የአሰብንና ምጽዋ ወደብን መጠቀም መጀመሯ በጅቡቲ ላይ ብቻ ከተንጠለጠለው አካሄዷ አንጻር እንደ አማራጭ መቀመጡ መልካም መሆኑ ቢነሳም ፤ ወደቦቹ አሁን ካሉበት ሁኔታ አንጻር ግን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸው በተወሰኑ ምክንያቶች ሳቢያ ብዙም እንዳልሆነ ነግረውኛል ።

ከምክንያቶቹ አንዱ የኤርትራ ወደቦች አሁን ላይ ያላቸው አቋምና ኢትዮጵያ ከጦርነቱ በፊት ስትጠቀምበት ታስገባ የነበረቻቸው እቃዎች አንጻር አሁን ላይ ልዩነታቸው እየሰፋ መምጣቱ ነው ።
ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት እጅግ እያደገ ከመጣው የገቢና ወጪ ንግድ አንፃር የመርከቦቿ የጭነት አቅምም ከጊዜ ወደጊዜ በእጅጉ ጨምሯል ።

ጅቡቲም በወደብ ላይ ብዙ ኢንቨስት ያደረገችው ከኢትዮጵያ የምታገኘውን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ መሆኑ ይታወቃል። ።
ኢትዮጵያም ከዲፒ ወርልድ(DP World) ጋር በርበራ ድርሻ ወስዳ በአመት 1.3 ሚሊዮን ኮንቴነር የሚያስተናግድ ወደብ ለማልማት የተዘጋጀችውም ለዚሁ ነው ።
የኤርትራ ሁለቱ ወደቦች ደግሞ የኢትዮጵያን ግዙፍ የገቢ እቃ ድርሻ ከመያዝ አንጻር አሁን ላይ ብዙ እንደሚቀራቸው የሚሰራውን ጥናት በቅርበት የሚያውቁ ምንጮቻችን ያስረዳሉ ።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ካሏት 11 መርከቦች ዘጠኙ በእለት ከእለት ስራ ውስጥ ናቸው ።
የሀገሪቱ ህዝብ ፤ የግንባታው እና የኢንዱስትሪው ዘርፍ የገቢ እቃዎች ፍላጎት መጨመሩን ተከትሎ የመርከቦች የመሸከም አቅምም ጨምሯል ።
የመርከቦች የመሸከም አቅም ሲጨምር ደግሞ በወደቦች ዳርቻ ያለው የማንሳፈፊያ ውሃማ ቦታ መርከቡን እንዲያንሳፍፍ ዝቅ ብሎ እንዲለማ ማድረግ ያስፈልጋል ፤ ካልሆነ መርከቡ ከመሬት ጋር የሚጋጭ ይሆናል ።
ጅቡቲ በቻይናውም ሆነ በዲፒ ወርልድ ያለማቻቸው የወደቦች ዳርቻ ጭነታቸው የከበዱ መርከቦችን ማንሳፈፍ በሚያስችል ሁኔታ ጥልቀት እንዲኖራቸው ሆነው ተሰርተዋል ።
አሰብና ምጽዋ ግን የድሮ የኢትዮጵያን መርከቦች የመሸከም አቅምን ከግንዛቤ ያስገቡ ናቸው ።
በሌላ በኩል የወደቦች ዳርቻ በአንዴ የሚያራግፉ መርከቦችን የመያዝ አቅማቸውም ዝቅተኛ ነው።
የጅቡቲ ወደብ በአንዴ 14 መርከቦችን እንዲያራግፉ የሚያስችሉ በርዞች (መቆሚያና ዕቃ ማራገፊያ) አሉት ።
የኤርትራው የአሰብ ወደብ ግን የመርከቦች ክብደት ውስንነቱ እንዳለም ሆኖ ሰባት መርከቦች በአንዴ የሚያራግፉበት ዳርቻ ነው ያለው።

እነዚህ ሁሉ ጉድለቶች ቢኖሩም ኤርትራ ምጽዋ ወደብን ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዝግጁ ለማድረግ አሰናድታዋለች ።
ኢትዮጵያም ወደቡን ለመጠቀም ዝግጁ ናት መባሉ የተጀመረው ዲፕሎማሲ ላይ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠርና መጠነኛ አማራጭ ለማምጣት ያለመ እንጂ ከዚያ የሚያልፍ ጥቅም የሚያመጣ አይደለም ይላሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ።
አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመሩትና ከማሪታይም ጉዳዮች ባለሰልጣንና ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የተውጣጡ ባለሙያዎችን ያካተተው የጥናት ቡድንም እነዚህን የወደቦቹን ጎድለቶች እንዴት ማሻሻል ይቻላል የሚሉ ጉዳዮችን ጨምረው እየተመለከቱ ነው።

ምናልባትም ኢትዮጵያ ከወደቦቹ ላይ ድርሻ በመውሰድ ልታለማ የምትችልበት አማራጭ አብሮ እንደሚታይ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች ስትጠቀም በክፍያ ይሁን አይሁን እስካሁን ባይገለጽም የጥናት ቡድኑ የወደብ ታሪፍ ጉዳይንም እንዲያጠና ታዟል ።
ሁለቱ ሀገራት በእንዲህ አይነት መሰረተ ልማቶች ሲተሳሰሩም የሚሰሩባቸው ህጎች አምባሳደር ግርማ ብሩ ከሚመሩት ቡድን የሚጠበቅ ነው ።

The post የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ወደብ አጠቃቀም የሚያጠና ቡድን አቋቋመ appeared first on Wazemaradio.

[…]

ከባህር ማዶ የተመለሱ የተቃዋሚ መሪዎችና ግለሰቦች የሆቴልና የመጓጓዣ ወጪ መንግስትን እየፈተነ ነው

Ethiopian

  • የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ከቀናት በኋላ አዲስ አበባ ይገባሉ

ዋዜማ ራዲዮ- ቀደም ሲል ወደ ሀገር ቤት የገቡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጉዳይ አስፈፃሚዎችን በዓየር ለማጓጓዝ ለሆቴልና ትራንስፖርት መንግስት ዳጎስ ያለ ወጪ ማውጣቱ ተሰምቷል።
ለግለሰቦቹ የየዕለት የሆቴል መስተንግዶና ሌሎች ወጪዎች ከዕለት ዕለት እየናረ መምጣቱን የሚናገሩት የመንግስት የሰራ ሀላፊዎች ወጪው ለሀገር ሰላምና ዕርቅ ሲባል የሚከፈል በመሆኑ ጉዳዩን መንግስት በሆደ ሰፊነት ሲመለከተው ቆይቷል።

አሁን ግን የወጪው መናር ያሳሰባቸው ሆቴሎች መንግስት ክፍያ እንዲፈፅም መጠየቃቸውንና እየቀረበ ያለው የገንዘብ መጠን አነጋጋሪ መሆኑን ለዋዜማ ቅርብ የሆኑ የአዲስ አበባ ምንጮች ነግረውናል።

የገንዘብ ወጪውንና ምን ያህን እንግዶች በመንግስት መስተንግዶ እየተደረገላቸው እንደሆነ የጠየቅናቸው ምንጫችን ሆቴሎች ሀገራዊ ፋይዳውን በመረዳት ቅናሽ ቢሰጡንም ተሰተናጋቾቹ በርካታ እንግዶች የሚጎበኟቸው በመሆኑና የቢሮ አገልግሎት የሚጠቀሙም ስላሉ ወጪውን ከፍ ማድረጉን ያስረዳሉ። የገንዘቡን መጠን መናገር ግን እንደማይደፍሩ ነግረውናል።

አሁን ቢያንስ ሀምሳ ሁለት ያህል እንግዶች በመንግስት እየተሰተናገዱ ሲሆን ከሶስት ወር እስከ አንድ ሳምንት የቆይታ ዕድሜ አላቸው። የገንዘቡን መጠን መናገር ግን እንደማይደፍሩ ነግረውናል።
አንዳንዶቹ ለጊዜው ከሆቴል ውጪ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ይቆዩና ተመልሰው እንደሚመጡ አንዳንዶቹ ደግሞ አዲስ አበባ ቤተሰብ ስለሌላቸው በቋሚነት የሆቴሉ እንግዶች ሆነው ቀጥለዋል። የፀጥታ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውም ሆቴል መሆኑን እንደሚመርጡ ተሰምቷል።

በተያያዘ ዜና ከሰሞኑ ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች መንግስት ለጉዞና ለሆቴል ወጪያቸውን ለመሸፈን ያቀረበላቸውን ግብዣ ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ስምተናል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር በአሜሪካ በነበረው ውይይት ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በአንድ አውሮፕላን መመለስ እንደሚችሉ የተነገራቸው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ማናቸውንም ወጪ ራሳቸው እንደሚችሉና ለመመለስ ዝግጅት እንደሚያሰፈልጋቸው ገልፀው የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ግብዣ ከምስጋና ጋር ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች በቀናት ጊዜ ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ያቀናሉ። ለአቀባበሉም ዝግጅት እየተደረገ ነው። አመራሮቹ ወደ ሀገር ቤት ሲጓዙ ለብቻቸው አይደለም፣ ከፍ ያለ ቁጥር ያለው የድርጅቱ ደጋፊና አባል ከባህር ማዶ አብሮ ይጓዛል። በመላዊ ኢትዮጵያ ያሉ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች አዲስ አበባን ያደምቋታል። በክልል ከተሞችም የአቀባበል ስነስርዓት ይካሄል።

ዝግጅቱ የሚካሄድበትን ቀንና ቦታ ድርጅቱ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

The post ከባህር ማዶ የተመለሱ የተቃዋሚ መሪዎችና ግለሰቦች የሆቴልና የመጓጓዣ ወጪ መንግስትን እየፈተነ ነው appeared first on Wazemaradio.

[…]

Awramba Times Presents Activist Jawar Mohammed (Video)

Activist Jawar Mohammed

Awramba Times Interviews Activist Jawar Mohammed on Current Ethiopian events and the way forward

[…]

የህወሃትና ኦብነግ የትግል አጋርነት – በንጹሃን ደም ሲታተም አየን!!

በሚያዚያ 1999 አቦሌ በሚባለው የነዳጅ ጉደጓድ መቆፈሪያ ካምፕ 200 የሚጠጉ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ታጣቂዎች በድንገት የፈጸሙት ጥቃት አስደንጋጭና አረመኔነት የተሞላበት ነበር። በወቅቱ ዘጠኝ ቻይናዎችን ጨምሮ በድምሩ ሰባ አራት ንጹሃን ህይወት አለፈ። በወቅቱ ጥቃቱ የተፈጸመው በሌሊት ሁሉም በተኙበት ሲሆን ግናብሩ ንጹሃንን ከጨፈጨፈ በኋላ ሰፊ መነጋገሪያ የነበረው ጉዳይ እንዴት ጥበቃው ላላ? እንዴት መከለከያና ደህንነት መረጃ አልባ […] […]

Ethiopian Tousism Organization gets new head

Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) has assigned Lensa Mekonnen as the new CEO of the Ethiopian Tourism Organization (ETO). She received the letter of appointment at the end of last week, filling the vacant position for the six months after the departure of Yohannes Tilahun, who was removed from his post following a dispute between […] […]

Bon Hotels’ Third Property Destined for Addis Ababa

The local property developer invested 300 million Br on a 115-room hotel. Bon Hotels, a South Africa-based hotel management company, has partnered with a local property developer to triple its presence in Addis Abeba. Ayal Tizaz, a local businessman, invested 300 million Br to construct the seven-storey hotel. The property, located close to German Square […] […]

Haile Hotels Extends to Debre Berhan

Haile & Alem International Plc, the operator of Haile Hotels & Resorts, is opening its ninth property in Debre Berhan, 130km northeast of of Addis Abeba, in Amhara Regional State. Owned by the celebrated long-distance runner Haile Gebrselassie and his wife Alem Tilahun, the new eight-storey, 100-room hotel is expected to cost 200 million Br […] […]

የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በቁጥጥር ስር ውለዋል

abdi liey

ዋዜማ ራዲዮ- የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በቁጥጥር ስር ውለዋል። የዋዜማ ምንጮች እንደነገሩን አብዲ ኢሌ በጅጅጋ ከነበሩበት ቤተ መንግስት ተይዘው ተወስደዋል። ፕሬዝዳንቱን ለመያዝ በተደረገው ጥረት ተኩስ መሰማቱን እማኞች ይናገራሉ።

ስራዊቱና የክልሉ ፖሊስ በጋራ በሰሞኑ ጥቃት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ሌሎች ባልስልጣናትንም ለመያዝ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ከክልሉ ምክር ቤት አባላት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ባለፉት ቀናት በፕሬዝዳንቱና በፌደራል መንግስቱ መካከል ድርድር ሲካሄድ ነበር። አብዲ ኢሌ የክልል ፕሬዝዳንትነቱን ስልጣን ለቀው የፓርቲያቸውን ሊቀመንበርነት እንደያዙ ለመቆየት ተስማምተው ነበር።

በስፍራው ያሉ ምንጮቻችን አብዲ ኢሌ በኀይል ተገደው እጅ መስጠታቸውን ይናገራሉ።
አሁን የመከላከያ ሰራዊቱ አብዲ ኢሌን ወዴት እንደወሰዳቸው አልታወቀም።

እስካሁን በተደረገ አሰሳ ከስልሳ የማያንሱ በግድያና ዝርፊያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተይዘዋል።

ባለፉት ቀናት በጅጅጋና ድሬዳዋ በደረሰው ዝግናኝ ስብዓዊ እልቂትና ውድመት የፌደራል መንግስቱ ፈጥኖ እርምጃ አልወሰደም በሚል ትችት እየቀረበበት ነው።

The post የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በቁጥጥር ስር ውለዋል appeared first on Wazemaradio.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.