Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ወደብ አጠቃቀም የሚያጠና ቡድን አቋቋመ

Massawa

ዋዜማ ራዲዮ- በቀድሞ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራ ቡድን ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች የምትጠቀምበትን ሁኔታ ማጥናት እንደጀመረ ከኢትዮጵያ የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሁለት ሳምንታት በፊት በሀገሪቱ ካሉ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ባደረጉት ቆይታ ሀገሪቱ አሁን ላይ የምጽዋ ወደብን በተቻለ ፍጥነት ወደመጠቀም እንደምትገባም ተናግረው ነበር ።
አሁን ላይም ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች የምትጠቀምበትን ሁኔታ አስመልክቶ ጥናት የሚያደርግ የተለያዩ ዘርፍ ባለሙያዎችን የያዘ የጥናት ቡድንን የቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አምባሳደር ግርማ ብሩ እየመሩት ነው ።
በጥናቱ ውጤት ላይም ኢትዮጵያ ምጽዋና አሰብን ስትጠቀም ምን አይነት ስትራቴጂ ይኖራታል ? ሁለቱ ሀገራትስ ከወደብ አንጻር ምን አይነት ግንኙነት ነው የሚኖራቸው ? የሚለው ጉዳይ ግልጽ ተደርጎ እንደሚቀመጥም ምንጮቻችን ነግረውናል ።

ይህም ብቻ ሳይሆን ወደቦቹን መጠቀም ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸውስ ምን ይመስላል ? የሚለው ጉዳይም እየተፈተሸ እንደሆነ ምንጮቼ ነግረውኛል ።
የጥናቱን ሂደት ከሚያውቁ ባለሙያዎች እንደሰማነው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የአሰብንና ምጽዋ ወደብን መጠቀም መጀመሯ በጅቡቲ ላይ ብቻ ከተንጠለጠለው አካሄዷ አንጻር እንደ አማራጭ መቀመጡ መልካም መሆኑ ቢነሳም ፤ ወደቦቹ አሁን ካሉበት ሁኔታ አንጻር ግን ኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸው በተወሰኑ ምክንያቶች ሳቢያ ብዙም እንዳልሆነ ነግረውኛል ።

ከምክንያቶቹ አንዱ የኤርትራ ወደቦች አሁን ላይ ያላቸው አቋምና ኢትዮጵያ ከጦርነቱ በፊት ስትጠቀምበት ታስገባ የነበረቻቸው እቃዎች አንጻር አሁን ላይ ልዩነታቸው እየሰፋ መምጣቱ ነው ።
ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት እጅግ እያደገ ከመጣው የገቢና ወጪ ንግድ አንፃር የመርከቦቿ የጭነት አቅምም ከጊዜ ወደጊዜ በእጅጉ ጨምሯል ።

ጅቡቲም በወደብ ላይ ብዙ ኢንቨስት ያደረገችው ከኢትዮጵያ የምታገኘውን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ መሆኑ ይታወቃል። ።
ኢትዮጵያም ከዲፒ ወርልድ(DP World) ጋር በርበራ ድርሻ ወስዳ በአመት 1.3 ሚሊዮን ኮንቴነር የሚያስተናግድ ወደብ ለማልማት የተዘጋጀችውም ለዚሁ ነው ።
የኤርትራ ሁለቱ ወደቦች ደግሞ የኢትዮጵያን ግዙፍ የገቢ እቃ ድርሻ ከመያዝ አንጻር አሁን ላይ ብዙ እንደሚቀራቸው የሚሰራውን ጥናት በቅርበት የሚያውቁ ምንጮቻችን ያስረዳሉ ።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ካሏት 11 መርከቦች ዘጠኙ በእለት ከእለት ስራ ውስጥ ናቸው ።
የሀገሪቱ ህዝብ ፤ የግንባታው እና የኢንዱስትሪው ዘርፍ የገቢ እቃዎች ፍላጎት መጨመሩን ተከትሎ የመርከቦች የመሸከም አቅምም ጨምሯል ።
የመርከቦች የመሸከም አቅም ሲጨምር ደግሞ በወደቦች ዳርቻ ያለው የማንሳፈፊያ ውሃማ ቦታ መርከቡን እንዲያንሳፍፍ ዝቅ ብሎ እንዲለማ ማድረግ ያስፈልጋል ፤ ካልሆነ መርከቡ ከመሬት ጋር የሚጋጭ ይሆናል ።
ጅቡቲ በቻይናውም ሆነ በዲፒ ወርልድ ያለማቻቸው የወደቦች ዳርቻ ጭነታቸው የከበዱ መርከቦችን ማንሳፈፍ በሚያስችል ሁኔታ ጥልቀት እንዲኖራቸው ሆነው ተሰርተዋል ።
አሰብና ምጽዋ ግን የድሮ የኢትዮጵያን መርከቦች የመሸከም አቅምን ከግንዛቤ ያስገቡ ናቸው ።
በሌላ በኩል የወደቦች ዳርቻ በአንዴ የሚያራግፉ መርከቦችን የመያዝ አቅማቸውም ዝቅተኛ ነው።
የጅቡቲ ወደብ በአንዴ 14 መርከቦችን እንዲያራግፉ የሚያስችሉ በርዞች (መቆሚያና ዕቃ ማራገፊያ) አሉት ።
የኤርትራው የአሰብ ወደብ ግን የመርከቦች ክብደት ውስንነቱ እንዳለም ሆኖ ሰባት መርከቦች በአንዴ የሚያራግፉበት ዳርቻ ነው ያለው።

እነዚህ ሁሉ ጉድለቶች ቢኖሩም ኤርትራ ምጽዋ ወደብን ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዝግጁ ለማድረግ አሰናድታዋለች ።
ኢትዮጵያም ወደቡን ለመጠቀም ዝግጁ ናት መባሉ የተጀመረው ዲፕሎማሲ ላይ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠርና መጠነኛ አማራጭ ለማምጣት ያለመ እንጂ ከዚያ የሚያልፍ ጥቅም የሚያመጣ አይደለም ይላሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ።
አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመሩትና ከማሪታይም ጉዳዮች ባለሰልጣንና ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የተውጣጡ ባለሙያዎችን ያካተተው የጥናት ቡድንም እነዚህን የወደቦቹን ጎድለቶች እንዴት ማሻሻል ይቻላል የሚሉ ጉዳዮችን ጨምረው እየተመለከቱ ነው።

ምናልባትም ኢትዮጵያ ከወደቦቹ ላይ ድርሻ በመውሰድ ልታለማ የምትችልበት አማራጭ አብሮ እንደሚታይ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች ስትጠቀም በክፍያ ይሁን አይሁን እስካሁን ባይገለጽም የጥናት ቡድኑ የወደብ ታሪፍ ጉዳይንም እንዲያጠና ታዟል ።
ሁለቱ ሀገራት በእንዲህ አይነት መሰረተ ልማቶች ሲተሳሰሩም የሚሰሩባቸው ህጎች አምባሳደር ግርማ ብሩ ከሚመሩት ቡድን የሚጠበቅ ነው ።

The post የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ወደብ አጠቃቀም የሚያጠና ቡድን አቋቋመ appeared first on Wazemaradio.

Source:: http://wazemaradio.com/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%89%B5%E1%88%AB%E1%8A%95-%E1%8B%88%E1%8B%B0%E1%89%A5-%E1%8A%A0/

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.