Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በቁጥጥር ስር ውለዋል

abdi liey

ዋዜማ ራዲዮ- የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በቁጥጥር ስር ውለዋል። የዋዜማ ምንጮች እንደነገሩን አብዲ ኢሌ በጅጅጋ ከነበሩበት ቤተ መንግስት ተይዘው ተወስደዋል። ፕሬዝዳንቱን ለመያዝ በተደረገው ጥረት ተኩስ መሰማቱን እማኞች ይናገራሉ።

ስራዊቱና የክልሉ ፖሊስ በጋራ በሰሞኑ ጥቃት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ሌሎች ባልስልጣናትንም ለመያዝ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ከክልሉ ምክር ቤት አባላት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ባለፉት ቀናት በፕሬዝዳንቱና በፌደራል መንግስቱ መካከል ድርድር ሲካሄድ ነበር። አብዲ ኢሌ የክልል ፕሬዝዳንትነቱን ስልጣን ለቀው የፓርቲያቸውን ሊቀመንበርነት እንደያዙ ለመቆየት ተስማምተው ነበር።

በስፍራው ያሉ ምንጮቻችን አብዲ ኢሌ በኀይል ተገደው እጅ መስጠታቸውን ይናገራሉ።
አሁን የመከላከያ ሰራዊቱ አብዲ ኢሌን ወዴት እንደወሰዳቸው አልታወቀም።

እስካሁን በተደረገ አሰሳ ከስልሳ የማያንሱ በግድያና ዝርፊያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተይዘዋል።

ባለፉት ቀናት በጅጅጋና ድሬዳዋ በደረሰው ዝግናኝ ስብዓዊ እልቂትና ውድመት የፌደራል መንግስቱ ፈጥኖ እርምጃ አልወሰደም በሚል ትችት እየቀረበበት ነው።

The post የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በቁጥጥር ስር ውለዋል appeared first on Wazemaradio.

Source:: http://wazemaradio.com/%E1%8B%A8%E1%88%B6%E1%88%9B%E1%88%8C-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8B%B5%E1%88%9E-%E1%8D%95%E1%88%AC%E1%8B%9D%E1%8B%B3%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A5%E1%8B%B2-%E1%88%98/