Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

የተዘቀዘቀ መስቀል?!

“አርቲስት ቴዲ አፍሮ የጥምቀት በዓልን ወደ አደባባይ ወጥቶ ማክበሩን የሚያሳይ ፎቶ ተለቋል” ሲሉ ነው በርካቶች ባሰራጩት አስተያየት “ነገሩ ምንድን ነው?” ሲሉ ግራ በመጋባት ማብራሪያ የጠየቁ ቢበዙም፣ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመው የነበሩ አካላት ላይ ውግዘት መድረሱን ያስታወሱም አልታጡም። የሚያደርገውን በማወቅ፣ ጊዜና ሰዓት በማስላት በሚያከናውናቸው ተግባሮቹ ስኬት የለኩት “ቴዲ ሳያውቅ ይህን ለበሰ ለማለት ያስቸግራል” ሲሉም ተድምጠዋል። የዲዛይን […] […]

ፑንትላንድ ለኢትዮጵያ ወደብ በነጻ እሰጣለሁ አለች

የሶማሊላንድና አሜሪካ የጦር ሰፈር ስምምነት ያደርጋሉ ከሶማሊያ ራሷን ለይታ በራስ ገዝነት የምትተዳደረዋ ፑንትላንድ “ኢትዮጵያ የባህር ዳርቻዎቼን አልምታ መጠቀም ትችላለች፤ እኛ በየትኛውም ኢትዮጵያ ወጪ ገቢ ላይ ምንም ዓይነት ቀረጥ አንጥልም” ስትል በባለስልጣኗ አማካይነት መናገሯ ጫጫታ አስነሳ። የሶማሊላንድ መሪ ወደ አረብ ኢምሬትስና አሜሪካ አቅንተው ከፍተኛ የተባለ የጦር ሰፈር ግንባታ ውል እንደሚፈራረሙ ታውቋል። ፑንትላንድ በምታሳያቸው እንቅስቃሴ ክፉኛ ያናደዳቸው […] […]

የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ ለማምከን በሶማሊያ የተዘጋጀ ስትራቴጂክ ሰነድ

ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ በወታደራዊ፣ በዲፕሎማሲ እና በሌሎችም ዘመቻዎች የምትከተለውን ስትራቴጂ የተመለከተው ሰነድ ሚስጥራዊ ማስታወሻ ለ፡ ሐሰን ሼክ ሞሃሙ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት A confidential Memorandum To: HE. Hassan Sheikh Mohamoud President of the Somali Federal Republic ከ፡ ሙክታር አይናሼ፣ የሶማሊያ መንግሰት የፀጥታ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝና አማካሪ፣ የሶማሊያ ዜጋ –ግልባጭ፡ -ሃምዛ ባሬ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ […] […]

የኦሮምያና የአማራ ክልል አማፅያንን ከመንግስት ጋር ለማደራደር አዲስ ሙከራዎች እየተደረጉ ነው

ዋዜማ – በታንዛንያ በሁለት ዙር ተካሂዶ ባለቀ ሰዓት የተሰተጓጎለውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትንና የመንግስትን ድርድር ለሶስተኛ ዙር ለማስቀጠል እንዲሁም የአማራ ክልል ፋኖ ታጣቂዎችን ወደ ድርድር ለማምጣት በአሜሪካ እና በአውሮፓ ህብረት በኩል የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ዋዜማ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች ሰምታለች።

የፌደራሉ መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ድርድር በስልጣን ድልድልና በአሸባሪነት ፍረጃ እንዲሁም ጉልህ ባልሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በተነሱ አለመግባባቶች ከሁለት ወራት በፊት ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል። ድርድሩ ለምን እንዳልተሳካና የድርድሩ ዋና ዋና ነጥቦችን እዚህ ማስፈንጠሪያ ላይ ያገኙታል።

የአሜሪካ መንግስት ዋና አደራዳሪ ማይክ ሀመር ከኢጋድና የአፍሪቃ ህብረት ጋር በመሆን ድርድሩን ለማስቀጠል የሚያስችል ውይይት ከመንግስት ጋር ለማድረግ እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት አተገባበር ለመገምገም ባለፉት ቀናት ወደ አዲስ አበባ አቅንተው ነበር። በቆይታቸውም ድርድሩን ማስቀጠል የሚያስችሉ ዝርዝር ጉዳዮችን ከሚመለከታቸው ጋር መወያየታቸውን ምንጮች ነግረውናል።

ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በተጨማሪ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች ጋር ድርድር ማድረግ የሚቻልበት ጉዳይ ላይ ባለፉት ሁለት ወራት በአሜሪካ መንግስትና በአውሮፓ ህብረት እንዲሁም በእንግሊዝ መንግስት በኩል ጥረቶች ሲደረጉ ሰንብተዋል።

ከአማራ ክልል ሀይሎች ጋር ድርድር ለማድረግ እጅግ ፈታኝ የሆነው በተበታተነ መልኩ ያለው አደረጃጀት ታጣቂዎቹንም ሆነ ያሏቸውን ጥያቄዎች ይዞ በአንድ ድምፅ ሊቀርብ የሚችል ሀይል አለመኖሩ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ያስረዳሉ።

በሀገርቤትም ሆነ በውጪ ያሉ የፋኖ አደረጃጀቶች የተለያዩ መሆናቸው ቅድመ ድርድር ለመጀመር የሚያስችል ውይይት ለማድረግ እንኳ ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል። ከታጣቂዎቹ ወገን ወደ ድርድር መምጣት ላይ ተቃውሞ ያላቸውና ጥያቄያቸውን በመሳሪያ ሀይል እንፈታለን ብለው የሚያምኑ እንዳሉም ምንጮች አልሸሸጉም። ይህን የተጠሪነት ችግር ለመፍታት ድርድሩ በቅድሚያ በሀገር ቤት በአቀራራቢ ሽማግሌዎች በኩል እንዲጀመርና ሁሉን ያማከሉ ተደራዳሪዎች እንዲለዩ ሀሳብ ያቀረቡም መኖራቸውን ስምተናል።

በሌላ ወገን ድርድሩ በአማራ ክልል መንግስትና በታጣቂዎች መካከል እንዲደረግ የሚያስችል ሀሳብ ያላቸው የአውሮፓ ዲፕሎማቶች የክልሉን ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደን በሁለት ዙር ማወያየታቸው ታውቋል።

የፌደራሉ መንግስት ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ድርድር ለማድረ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸው ላይ ጥርጣሬ እንዳለው ገልፆ፣ ለሚደረጉ ማናቸውም ድርድሮች በሩ ክፍት መሆኑን ነግሮናል ብለዋል ዲፕሎማቶቹ።

እነዚህ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ የሰላም ጥረቶች በእንጥልጥል ባሉበት ሰዓት በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት እንዲሁም የሱዳኑ ጦርነት መባባስ ምዕራባውያኑን የበለጠ እንዳሳሰባቸው እየገለፁ ነው። [ዋዜማ]

To reach Wazema Editors, Please write wazemaradio@gmail.com

The post የኦሮምያና የአማራ ክልል አማፅያንን ከመንግስት ጋር ለማደራደር አዲስ ሙከራዎች እየተደረጉ ነው first appeared on Wazemaradio.

The post የኦሮምያና የአማራ ክልል አማፅያንን ከመንግስት ጋር ለማደራደር አዲስ ሙከራዎች እየተደረጉ ነው appeared first on Wazemaradio.

[…]

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ለምን አልተስማሙም?

ዋዜማ- የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (አልያም በፌደራሉ መንግሥቱ አጠራር ኦነግ-ሸኔ) እና የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ባደረጓቸው ኹለት ዙር ድርድሮች ወደ ስምምነት ለመድረሰ ተቃርበው ነበር። በኹለተኛው ዙር ድርድር የመጨረሻ ሰዓት ላይ በተፈጠረ አለመግባባት፣ ተስፋ የተጣለበት ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁም ሲነገር ሰንብቷል። ያ ድርድር ስለምን ከሸፈ? ተደራዳሪዎቹስ ሊስማሙባቸው ያልቻሏቸው አጀንዳዎች ምንድን ነበሩ? እነዚኽን እና መሰል ጥያቄዎችን አስመልክቶ፣ ዋዜማ ያሰባሰበቻቸውን መረጃዎች እንደሚከተለው አሰናድተነዋል።

የታንዛኒያው ጠረጴዛ

ዕለተ ማክሰኞ ሚያዝያ 17 2015 ዓ.ም.፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ተደራዳሪዎች ዛንዚባር ላይ መገናኘታቸው ሲረጋገጥ፣ የአገሪቷ የሰላም ቆሌ ይራዳቸዋል ብለው ተስፋ ያደረጉ ብዙዎች ነበሩ። በፕሪቶሪያ ከሕወሓት ጋራ የተፈፀመው የሰላም ስምምነት የፈጠረው መነቃቃት፣ ለመንግሥትም ሆነ ለኦነሠ ብርታት ሳይፈጥርላቸው አልቀረም ነበር። ተደራዳሪዎቹ የሄዱባት ታንዛኒያ፣ ነጻነቷን ካገኘችበት እ.ኤ.አ. ከኅዳር 1954 ወዲህ፣ ከአጎራባቾቿ ጋራ ስትነፃፀር የጎላ የእርስ በእርስ ጦርነት ያላገጠማት ሰላማዊ አገር ነች። እንዲያውም የጎረቤት አገር ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ደቡብ ሱዳንን ውስጣዊ ሰላም ያሰፍናሉ የተባሉ በርካታ የሰላም ድርድሮች እና ስምምነቶች የተከወኑባትም አገር ነች። ቢያንስ ከዚኽ አኳያም፣ የኢትዮጵያም ሰዎች አንዳች ስምምነት ላይ ይደርሳሉ የሚል ተስፋ አርብቦ ነበር።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ተደራዳሪዎቹ ወደ ዛንዚባር እና ዳሬ ሰላም ሲሄዱም ሆነ ሲመለሱ፣ እንዲስማሙ ሊያደርጓቸው የሚችሉ ውጫዊ እና ውስጣዊ ኹኔታዎች አልነበሩም። ከታንዛኒያው ጠረጴዛ ቀደም ብሎም፣ የኢትዮጵያን መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ለማቀራረብ አገር ቤት የተደረጉ በርካታ ሙከራዎች በተደጋጋሚ ከሽፈዋል። የዛንዚባሩ ድርድር እንደሚካሄድ ማረጋገጫው የተሰማውም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ሚያዝያ 15 2015 ዓ.ም. የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እንዲያበቃ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ለተባሉት የተለያዩ አካላት በተዘጋጀው የዕውቅና ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው፣ መንግሥታቸው ከኦነሠ ተወካዮች ጋራ በዛንዚባር ደሴት ለድርድር እንደሚቀመጥ ሲያስታውቁ ነበር።

“ከኦነግ-ሸኔ ጋራ ከነገ ወዲያ ታንዛኒያ ውስጥ ድርድር ይጀመራል” ሲሉ አስታወቁ። ኦነሠ በበኩሉ፣ በማግስቱ ባወጣው መግለጫ የድርድር ቀጠሮ መኖሩን አረጋገጠ። በዚኽ መግለጫው ግን፣ “ሸኔ” እየተባለ መጠራቱን አጥብቆ አወገዘ። “በስሜ ጥሩኝ” ሲል ያሳሰበው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ከዚህ ውጭ ባለ ስም መጠራቱ “የተሳሳተ፣ ማንነቴንና አላማዬን አዛብቶ ለማቅረብ የሚደረግ ሙከራ ነው” ሲልም መንግሥት ከዚኽ ተግባሩ እንዲታቀብ አሳሰቦ አለፈ።

የዛንዚባሩ ድርድር መተማመን ለመፍጠር እና በቀጣይ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ድርድር አካሄዶች ላይ ለመስማማት የታቀደ ነበር። የኦነሠ ቃል አቀባይ ድርድሩ በኖርዌይ እና በኬንያ አደራዳሪነት እንደሚከናወን፣ በቀጣይ ግን አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ኢጋድ በሂደቱ እንደሚሳተፉ ለ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃል አረጋግጠው ነበር። ኬንያ እና ኖርዌይ በጋራ በመሩት የዛንዚባሩ የመጀመሪያ የዝግጅት ድርድርም፣ ኹለት ስኬቶች ተመዝግበዋል። የዋዜማ ምንጮች እንደሚሉት፣ ኦነሠ ወደ ድርድሩ ከመግባቱ በፊትም ሆነ ዛንዚባር ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ ያቀረበው ቁልፍ ጥያቄ፣ ድርድሩ በሦስተኛ ወገኖች አደራዳሪነት እንዲካሄድ እና ስምምነቱም በዋስትና ሰጪዎች አማካይነት እንዲደመደም ነበር። አሜሪካ፣ ኖርዌይ እና የአውሮፓ ኅብረት ዋስትና ሰጪዎች እንዲሆኑ የኦነሠ ጥብቅ ፍላጎት ነበር። የሦስተኛ ወገኖችን አደራዳሪነት ሲገፋ የሰነበተው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በኦነሠ በኩል የቀረበውን ይኽንን የአደራዳሪዎችን እና የዋስትና ሰጪዎችን ጥያቄ ሲቀበል፣ ኹሉም ወገኖች ተስፋ አድሮባቸው ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ተደራዳሪዎቹን ወደ ታንዛኒያ ሲልክም፣ በዚኽ ቅድመ ኹኔታ መስማማቱን ማመላከቱ አልቀረም። በዳሬ ሰላሙ ድርድር እንደታየው፣ በአደራዳሪነት እና በዋስትና ሰጪነት የተገኙት የአሜሪካ እና የኖርዌይ መንግሥታት፣ እንዲኹም የኢጋድ ተወካዮች ነበሩ።

በሦስት ቀናት ይጠናቀቃል የተባለው የዛንዚባሩ ድርድር፣ ለዘጠኝ ቀናት ተራዝሞ ሚያዝያ 25 ተጠናቀቀ። ንግግሩ ሲገባደድም፣ በቀጣይ ይካሄዳል ተብሎ ተስፋ በተደረገበት የድርድሩ ቴክኒካዊ አካሄዶች፣ በሦስተኛ ወገን አደራዳሪዎች እና ዋስትና ሰጪዎች መኖር ላይ ከመስማማታቸው ባለፈ፣ ዳግም ለመገናኘትም ቃል ገብተው መለያየታቸው፣ ለተጠባቂው ሰላም ቀብድ ተደርጎ ተቆጠረ።

ዳር ኤስ ሳላም (የሰላም ስፍራ)

በዛንዚባሩ የመጀመሪያ ዙር ድርድር ገርበብ ተደርጎ የተተወው የሰላም በር፣ ኹለተኛውን ዙር ድርድር በተስፋ እንዲጠበቅ አድርጎታል። ኹለተኛውን ድርድር የተሳካ እንዲያደርጉት ከቀረቡት ጥያቄዎች አንዱ፣ አገር ቤት የሚገኙት የኦነሠ መሪዎች በድርድሩ በአካል የሚሳተፉበት ኹኔታ እንዲመቻች እንደነበር የዋዜማ ምንጮች ይናገራሉ። በዚኽ መሰረትም፣ በአሜሪካ አመቻችነት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊቱ መሪ ኩምሳ ድሪባ (በጫካ የትግል ስሙ ጃል መሮ) ፤ እንዲሁም ምክትሉ እና የጉጂው የጦር ክንፍ መሪ ገመቹ ረጋሳ ወደ ዳሬ ሰላም እንዲጓዙ ተፈቅዶ በድርድሩ ተሳትፈዋል። ሆኖም የኦነሠ መሪዎች እና ተስፋ የተጣለባቸው አደራዳሪዎች መገኘት ድርድሩን ውጤታማ አላደረገውም። በዳሬ ሰላሙ ድርድር የአሜሪካ፣ የኖርዌይ፣ እና የኢጋድ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የዳሬ ሰላሙ ድርድር በተጠናቀቀ በሰዓታት ውስጥ፣ ተደራዳሪዎቹ ወገኖች ለድርድሩ መክሸፍ አንዱ ሌላውን አውግዘዋል። በአደራዳሪነትም፣ በታዛቢነትም የተገኙት የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር በቅርቡ ስለድርድሩ ያሉት ግን፣ ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ድርድር የመመለስ ጉዳይ አይቀሬ መሆኑን የሚያመላክት ሆኖ ተቆጥሯል። ከሁለት ወር ገደማ በፊት፣ “ኢትዮጵያ-ተስፋ ወይስ የበረታ ስጋት” በሚል ርዕስ ስር፣ በሴኔቱ የውጪ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ማብራሪያ የሰጡት ሐመር፣ “በአጭር ጊዜ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት ይቻላል ብሎ መናገር ከባድ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። ከዚያ ባለፈም፣ “ኹለቱም ወገኖች ለማመቻመች መዘጋጀት አለባቸው”ም ብለው ነበር። ከወዲኽ በኩል የተሰማው የኢጋድ መግለጫም፣ ኹለቱም ወገኖች ዳግም ወደ ድርድር እንዲመጡ የሚያሳስብ ነበር። ይህን ተስፋ እና ጥሪ በቅጡ ለመረዳትም፣ ተደራዳሪዎቹ ታንዛኒያ ላይ ለምን እንደተፋረሱ፣ ከዚያም አልፎ መሬት ያለውን የቡድኖቹ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ሚዛን መከታተልን ይጠይቃል።

ከድርድሩ ጀርባ

በዳሬ ሰላሙ ድርድር ውይይት ስለተደረገባቸው ጉዳዮች አደራዳሪዎቹም ሆኑ ታዛቢዎቹ እስከ አኹን በይፋ ያሉት ነገር የለም። ተደራዳሪዎቹ ግን፣ አንዱ ሌላውን “ከስምምነት የመድረስ ዓላማ አልነበረውም” ሲል አንዱ ሌላውን ይወቅሳል። ለድርድሩ ቅርብ የሆኑ አንድ ምንጭ፣ ኹለት ሳምንት በፈጀው የዳሬ ሰላሙ ድርድር “የጅል ጥያቄ” የሚባሉ ጉዳዮች እንደመደራደሪያ መቅረባቸውን ለዋዜማ አንስተውላታል።

ኹለት ከፍተኛ የኦነሠ መሪዎች እና ሌሎች የዲያስፖራ ተወካዮች በአካል በተገኙበት ቀረቡ ከተባሉት ጥያቄዎች አንዱ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ ኦሮሚያ)ን ግማሽ መቀመጫ ያለውድድር እንዲሰጠው የሚጠይቅ ነበር። ዲፕሎማቱ እንደሚሉት፣ ይኽ ጥያቄ የቀረበው መንግሥት የኦነሠ ለሚያቀርባቸው አባላቱ፣ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክልል ካቢኔ ባሉ ቦታዎች ሹመት ለመስጠት እንደሚችል ባቀረበው ሃሳብ ላይ ተጨማሪ ተደርጎ ነው። የኦነሠ ተደራዳሪዎች፣ ተዋጊዎቻቸው ወደ ክልሉ የፖሊስ ኅይል እና የፌደራል መንግሥቱ ጦር ውስጥ እንዲካተቱ ያቀረቡት ጥያቄ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ የኦነሠ የተዋጊዎቹን እና የጦር መሣሪያውን ብዛት በታዛቢዎች ፊት የመግለጥን ጉዳይ መቃወሙ፣ ተደራዳሪዎቹን ካላግባቡ ጉዳዮች አንዱ እንደነበር ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል።

በኦነሠ በኩል፣ ታጣቂዎቹ ወደ ፖሊስ እና መከላከያ ሲካተቱ የጦር መሣሪያቸውን ሳይፈቱ እንዲገቡ፣ ከፈቱም መሣሪያቸውን ለፌደራሉ መንግሥት ሳይሆን ለሦስተኛ ወገኖች ለማስረከብ የቀረበው መደራደሪያ፣ እጅግ ያልተጠበቀ ቢሆንም በአደራዳሪዎች ግፊት ታጣቂው ኅይል ጥያቄውን ማንሳቱንም ዋዜማ ሰምታለች።

ኦነሠ፣ በሕዝብ እንደራሴዎቹ ምክር ቤት የተጣለበት የሽብርተኝነት ስያሜ፣ ስምምነት በተፈረመበት ቀን እንዲነሳለት መጠየቁም፣ በዚያ የነበሩት የመንግሥት ተደራዳሪዎች ሊስማሙበት የሚቻላቸው ርዕሰ-ጉዳይ እንዳልነበር ነገሩን በቅርበት የተከታተሉ ምንጭ ለዋዜማ ገልፀዋል።

በኹለተኛው የታንዛኒያው ንግግር ዋዜማ ላይ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ልዑካን ቡድን፣ በአማጺው ቡድን ወታደራዊ አዛዥ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) እና በምክትላቸው ገመቹ ረጋሳ መሪነት ለንግግሩ ከታንዛኒያዋ ዳሬ ሰላም መግባቱን ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር። ቡድኑ በዚኹ መግለጫው፣ ራሱን “የኦሮሞ ነጻነት ግንባር – የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” በማለት ነበር የገለጠው። በንግግሩ ዙሪያም አስቀድሞ ለሕዝቡ መረጃ ያልሰጠው፣ የጦር አዛዦቹ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የውጊያ ቀጠናዎች ወደ ታንዛኒያ በሰላም እስኪደርሱ እንደነበርም በመግለጫው ተመላክቶ ነበር። ለጦርነቱ “ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄ” ለማፈላለግ ዝግጁነቱን የገለጠው ቡድኑ፣ የዳሬ ሰላሙ ንግግር ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መረጃ እንደሚሰጥም ተናግሮ ነበር።

ንግግሩ ከተጠናቀቀ በኋላም፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ኹለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ያለ ውጤት ለመበተኑ መንግሥትን ተጠያቂ የሚያደርግ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። ቡድኑ፣ መንግሥት መሠረታዊ ችግሮችን ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ፣ ብቸኛ ፍላጎቱ አመራሮቼን መመልመል ነበር ሲልም መንግሥትን ወቅሷል። በዛንዚባር እና ዳሬ ሰላም ንግግሮች፣ በኦሮሚያ ክልል መንግስታዊ አወቃቀር ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ አካታች ሃሳቦችን አቅርቦ እንደነበር የገለጠው ቡድኑ፣ ኾኖም በመንግሥት ግትርነት ሳቢያ ታሪካዊው አጋጣሚ ተበላሽቷል በማለት መግለጡ ይታወሳል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በድርድሩ ጉዳይ ላይ ላነሳናቸው ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎች ነልስ እንዲሰጠን ለአንድ ወር ያህል ሙከራ ብናደርግም የተለያዩ ምክንያቶች በመደርደር ተገቢ ምላሽ አልሰጠንም። [ዋዜማ]

The post የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ለምን አልተስማሙም? first appeared on Wazemaradio.

The post የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ለምን አልተስማሙም? appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data – 19 January 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 19 January 2024.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - 17 January 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 17 January 2024.

[…]

Nirvana to Start Agro-Processing in Ethiopia

Bahir Dar Industrial Park

Nirvana Processing, an Indian Company, is set to commence agro-food processing in Ethiopia’s Bahir Dar Industrial Park with a 5 million USD investment.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - 16 January 2023

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 16 January 2023.

[…]

Ethiopian Securities Exchange Welcomes Its First Private Investor

ESX Logo

Zemen Bank has become the first private entity to secure an agreement with the Ethiopian Securities Exchange (ESX) by investing Birr 47.5 million to acquire a 5% ownership share. This fulfills the minimum requirement set by ESX for investors as of January 11, 2024.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.