Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 15 January 2024.
[…]
|
|||||||
Ethiopia has formulated a logistics master plan to enhance and strengthen its logistics system. A validation workshop for the first phase of the plan took place, where the State Minister of Transport and Logistics, Denge Boru, emphasized the importance of regular review and improvement of the logistics sector. […] ዋዜማ- የጠሚር ዐቢይ መንግስት ከ4 ዓመት በፊት “ሀገር በቀል” ነው ያለውን የኢኮኖሚ ዕቅድ ይፋ አድርጎ ነበር። ይህ ዕቅድ በእርግጥ “ሀገር በቀል” ስለመሆኑ፣ ብሎም አሁን ከገባንበት የኢኮኖሚ ፈተና ያወጣናል ወይ? ኢትዮጵያ የብድር ወለድ ዕዳ አለመክፈሏ የሀገሪቱን የመበደር ተስፋና ባለሀብቶችን የመሳብ ዕድሏን አኮስሶታል። ለመሆኑ ሀገሪቱ 33 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል እንዴት ተሳናት? በጉዳዩ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገናል። ሶስት አጠር ያሉ ክፍሎች ያሉት ውይይት ከታች የያይዟል። ተመልክታችሁ የናንተን አስተያየት አድርሱን። The post ሀገር በቀል ወይስ ዋሽንግተን መር የኢኮኖሚ ዕቅድ? first appeared on Wazemaradio. The post ሀገር በቀል ወይስ ዋሽንግተን መር የኢኮኖሚ ዕቅድ? appeared first on Wazemaradio. […] ዋዜማ- የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ መሪዎች ኢትዮጵያን ለ50 ዓመታት የባህር ጠረፍ ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ሰነድ ከፈረሙ በኋላ በቀጠናው አዲስ የጆኦ ፖለቲካ ድንግርግር ተፈጥሯል። አሜሪካና ቻይና በሶማሊላንድ ጉዳይ የተለያየ አቋም አላቸው። ይህ ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጥረት አጋዥም ፈታኝም እውነታ ነው። የአፍሪቃ ህብረት በተደጋጋሚ የቀረበለትን የሶማሊላንድ የዕውቅና ጥያቄ አልተቀበለም። የኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ ዕውቅና መስጠት በአፍሪቃ አህጉር አዲስ መስመር ሆኖ ይመዘገባል። ስምምነቱ በታቀደው መሰረት ከተጠናቀቀ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪቃ ቀንድ አዲስ የታሪክ እጥፋት እንደሚሆን በርከት ያሉ የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ። በሀገር ውስጥ በእርስ በርስ ግጭትና በበረታ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ ከፊቷ የሚጠብቃት ተግዳሮትን ለመወጣት ያለችበትን ቁመና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ አስተያየት ሰጪዎችም አሉ። የመግባቢያ ስምምነቱ 20ኪሜ በ90 ኪሜ የሚሆን የባህር ሀይል ሰፈርና የበርበራ ወደብን ለመጠቀም የ50 ዓመታት የሊዝ ኪራይ ስምምነት ነው። ሶማሊያ ስምምነቱን “ተቀባይነት የሌለውና ሉዐላዊነቴን የሚዳፈር ነው፣ ለዚህም አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ወደ ኋላ አልልም” ብላለች። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ አዲሱ ስምምነት አልሸባብ እንዲያንሰራራ በር ይከፍታል ሲሉም ለፓርላማቸው ተናግረዋል። አስከትለውም ለግብፅና ለኳታር መሪዎች ስልክ በመደወል የአጋርነት ድጋፍ ጠይቀዋል። የሶማሊያ መንግስት የአፍሪቃ ህብረት፣ የፀጥታው ምክር ቤትና የአረብ ሊግ እንዲሁም ኢጋድ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲያደርጉ የሚጠይቅ መግለጫ አውጥቷል። ሶማሊያ በአዲስ አበባ የነበሯትን አምባሳደርም ለምክክር ወደ ሀገር ቤት ጠርታለች። በሶማሊላንድ ሀርጌሳ የመግባቢያ ሰነዱ በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድና ሙሴ ባሂ አብዲ መፈረሙ ይፋ ከተደረገ ጀምሮ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍና የአደባባይ የደስታ መግለጫ እየተደረገ ነው። በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ለመስጠት መስማማቷን የሀገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህም ለሰላሳ አመታት ከሶማሊያ ተነጥላ ለቆየችው ሶማሊላንድ ትልቅ የታሪክ እጥፋት ተደርጎ ተወስዷል። በዝርዝር ጉዳዮች ላይ በአንድ ወር ውስጥ ስምምነት ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ በሶማሊላንድና ኢትዮጵያ ስምምነት ዙሪያ አስቀድሞ መረጃው የተነገራቸው ጥቂት ሀገራት መኖራቸውን ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች ስምታለች። ምናልባትም የተባበሩት አረብ ዔምሬትስ ለሶማሊላንድ ዕውቅና በመስጠት ኢትዮጵያን ልትቀላቀል እንደምትችል ይጠበቃል። ለኢትዮጵያ የባህር ሀይል በማሰልጠንና የጦር መሳሪያ በመሸጥ አጋር የሆነችው ፈረንሳይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም። የአውሮፓ ህብረት ግን የሶማሊያን ሉዐላዊነት የሚዳፈር ማናቸውንም ድርጊት እንደሚያወግዝ በቃል አቀባዩ በኩል አስታውቋል። ዩናይትድስቴትስ ከወራት በፊት ከሶማሊላንድ ጋር የተናጠል ወታደራዊና የፀጥታ ትብብር ማድረግ የሚያስችላትን ህግ በኮንግረስ በኩል አስፀድቃለች። ይህ የአሜሪካ እርምጃ አሁን ኢትዮጵያ ላደረገችው ስምምነት አጋዥ መከራከሪያ ሊሆን የሚችል ነው። ከስምምነቱ ጋር ተያይዞ ብርቱ ዲፕሎማሲያዊ ፈተና ከፊቷ የሚጠብቃት ኢትዮጵያ ጠንካራ የልዑካን አባላትን የያዘ የዲፕሎማሲ ቡድን ወደተለያዩ ሀገራት ለማሰማራትና በውጪ ያሉ ዲፕሎማቶችን ስለጉዳዩ እንዲያስረዱ ለማድረግ ማቀዷን ሰምተናል። ዋነኛ የኢኮኖሚ አጋር የሆነችው ቻይና ፣ ከታይዋን ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያን እርምጃ እንደማትደግፈው ከወዲሁ እየተነገረ ነው። እስካሁን ከቻይና በኩል የወጣ መግለጫ የለም። የአረብ ሊግና አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከሶማሊያ ጎን እንደሆኑ ከወዲሁ እየተናገሩ ነው። ግብፅ ከሶማሊያ ጋር ሁለገብ ትብብር ለማድረግና የሶማሊያን የግዛት አንድነት ለማስከበር ድጋፍ እንደምታደርግ ፕሬዝዳንት አልሲሲ ለሶማሊያ አቻቸው ለሀሰን ሼክ መሀሙድ ቃል ገብተዋል። ባለፉት ሶስት አመታት የሶማሊያ ወታደሮችን በማሰልጠን ስራ ተጠምዳ የሰነበተችው ኤርትራ እስካሁን ይፋዊ አስተያየት አልሰጠችም። ባለፉት ወራት ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን መግለጿን ተከትሎ ኤርትራን ልትወር ትችላለች በሚል ሰፊ መላ ምት በውጥረት የሰነበቱ ኤርትራውያን እፎይታ እንደተሰማቸው በማህበራዊ ሚዲያ ሲገልፁ አንብበናል። [ዋዜማ] The post የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት አዲስ የታሪክ እጥፋት? first appeared on Wazemaradio. The post የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት አዲስ የታሪክ እጥፋት? appeared first on Wazemaradio. […] |
News
Political Groups |