Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

Historic home is both preserved and modernized

Everyone is looking to lose weight these days, but most people miss the one key to just how easy it really is: eating more fiber! While you need protein, healthy fats, and many vitamins and minerals for overall health, the one food that can help you stay fuller longer and keep your weight down is fiber-rich foods. […]

7 Little Known Facts About the Costumes on UnReal

Everyone is looking to lose weight these days, but most people miss the one key to just how easy it really is: eating more fiber! While you need protein, healthy fats, and many vitamins and minerals for overall health, the one food that can help you stay fuller longer and keep your weight down is fiber-rich foods. […]

መረጃ ሙሉ ያደርጋል: የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ዜናዎች እንዲሁም መጣጥፎች ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር

News #Ethiopia Wetatoch Dimts
መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ::

[…]

የቱርክ መንግስት በትግራይ የነጃሺ የመቃብር ስፍራንና መስጂድ እድሳት እያጠናቀቀ ነው

nejashi

ዋዜማ ራዲዮ-የቱርክ መንግስት በትግራይ ነጋሽ የሚገኘውን የንጉስ አርማህ ወይም ነጃሺ የመቃብር ስፍራ እድሳት እያጠናቀቀ መኾኑን አስታውቋል።

እድሳቱን እያከናወነ የሚገኘው የቱርክ የትብብርና ቅንጅት ኤጀንሲ (Turkish Coopration and Coordination Agency) በመባል የሚታወቀው የቱርክ የተራድዖ ድርጅት ነው። በእድሳቱ በእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች ዘንድ ነጃሺ በሚል ስም የሚታወቁት የአክሱም ንጉስ መቃብር እና በአካባቢው የሚገኘው የ አልነጃሺ መስጊድ ዳግመኛ ከመታደሳቸው በተጨማሪ ስፍራውን ለሚጎበኙ ተሳላሚዎች የሚያገለግል የምግብ እልፍኝ (food court) እና 500 ሰዎችን በአንድ ጊዜ ሊይዝ የሚችል የመሰብሰብያ አዳራሽም እንደሚገነባለት ታውቋል። የመቃብር ስፍራው የሚገኝባትን የ ነጋሽ ከተማ ያለባትን የውኃ ችግር የሚቀርፍም የውኃ ማጠራቀሚያ እንደሚገነባ ኤጀንሲው አስታውቋል።

የነጃሺ መቃብር ለዓለም ዓቀፍ ሙስሊሞች ትልቅ ክብር ከሚሰጣቸው የሐይማኖታዊ ጉዞ መዳረሻዎች አንዱ እንደመኾኑ መጠን የቱርክ መንግስት ይህን ታሪካዊ ስፍራ ለማደስ ያደረገው ድጋፍ ሐይማኖታዊ ተልእኮ ተደርጎ የሚታሰብ ነው። የንጉስ አርማህን ባለውለታነት በዓለም አቀፍ ሙስሊሞች ዘንድ እንዲታሰብ ያደረገውም የእስልምና ሐይማኖት በተጀመረበት በሰባተኛው መቶ ክፍለዘመን የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች በአገራቸው በደረሰባቸው ስደት ምክንያት መጠጊያ ሲሹ እጃቸውን ዘርግተው የተቀበሏቸው ብቸኛ የዓለም መሪ ስለነበሩም እንኾነ የእስልምና የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዘንድ የንጉስ አርማህ ታሪክ በተለየ ሁኔታ መወሳት ም ጀምሯል። ንጉስ አርማህ ለብዙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ንጉስ ተደርገው በመወሰድ የኩራት ምንጭ እንደኾኑም ይነገርላቸዋል።

ምንም እንኳን የንጉስ አርማህም ኾነ የሌሎች የዚያ ዘመን የአክሱም ነገስታት ታሪክ ከመረጃ መጥፋት ምክንያት ብዙ የማይታወቅ ቢኾንም ንጉስ አርማህ ግን እንደ እስልምና እምነት ባለውለታነታቸው በእስልምና ድርሳናት ውስጥ በተሰጣቸው ስፍራ ምክንያት እስካሁን ድረስ ስማቸው ለመጠራት የበቁ አክሱማዊ ንጉስ ኾነዋል። ምናልባትም በእስልምና እምነት ውስጥ ትልቅ ስፍራ ከተሰጣቸው ቀደምት ኢትዮጵያውያን መካከል ከእስልምናው ነቢይ ሙሐመድ ጋር የቀረበ ትውውቅ ከነበራቸው ኢትዮጵያዊቱ የነብዩ አሳዳጊና የጸሎት ማንቂያ የኾነውንና አዛን በመባል የሚታወቀውን ጥሪ የጀመሩት ሌላው ኢትዮጵያዊ ቢላል ጋር ተጨምሮ በነቢዩ ሙሐመድ ዘንድ ስለኢትዮጵያ መልካም ዝናን ሳያተርፉላት እንዳልቀሩም ይገመታል።

በእስልምና የታሪክ መዛግብት ስለንጉስ አርማህ የተጻፈውን ትውፊት በመመልከት ብቻ እንኳን ንጉሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያስመሰግናቸው የሚያስችላቸው ብዙ ጉዳይ አለ። በሐይማኖታቸው ምክንያት በግፍ ተሰደው የነበሩትን ሰዎች ተቀብለው ጥበቃ በመስጠታቸውና በሐይማኖታቸው ምክንያት ተጽእኖ ሳይደርስባቸው እንዲኖሩ በመፍቀዳቸው ዓለም ከብዙ ዘመን በኋላ ተስማምቶ የደረሰበትን የስደተኞችን የሰበአዊ መብት የማስጠበቅ ተግባር ፈጽመዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የዘለቀውንም በሁለቱ ሐይማኖቶች መካከል ያለውን ወንድማማችነት ፈር ቀዳጅ ኾነውም አኩሪ ተግባር ፈጽመዋል። በዚህ ሁሉ ሐይማኖታዊም ሐይማኖታዊ ያልኾነም ተግባር ምክንያት የንጉሱ ታሪክ የበለጠ ገናናነት የሚገባው ኾኖ ሳለ እንደ ብዙዎቹ የአገሪቱ መልካም መለያዎች ሁሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገባውን ያህል የታወቀ አይደለም።

የቱርክ መንግስት ይህን ታሪካዊ ቦታ በማሳደስ ለጎብኚዎች የሚስማማ እንዲኾን ያደረገው ከዚህ ሐይማኖታዊ ተልእኮ በመነሳት ብቻ አለመኾኑንም መገመት ይቻላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቱርክ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ከበፊቱ በተለየ እያጠናከረ የሚገኝበትም ፖለቲካዊ ምክንያት እንዳለውም ግልጽ ነው።

የቱርኩ የሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን መንግስት በቅርቡ ከተሞከረበት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በብርቱ ትግል ከተረፈ በኋላ ተቃዋሚዎቹን እና የነጻውን ፕሬስ በመጨፍለቅ ዳግመኛ ጉዳት እንዳይደርስብስት የሚያደርገው መከላከል በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ እያስወቀሰው ይገኛል። የቱርክ መንግስት ከመፈንቅለ መንግስት ሙከራው በኋላ ከወሰዳቸው ርምጃዎች አንዱ የጉለን እንቅስቃሴ በመባል የሚታወቀውን ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ ከመሰረቱት ከሙሐመድ ፈትሁላህ ጉለን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጥሩ ቱርካውያንን ማሳደድ መጀመራቸው ነው። ኤርዶጋን ጉለንን የስልጣናቸው ተቀናቃኝ አድርገው በማየታቸው ምክንያት በስደት ከሚኖሩበት ከአሜሪካም ተላልፈው እንዲሰጧት እየጠየቀች ነው።

ጉለንን ከማሳደድ በተጨማሪም የኤርዶጋን መንግስት በኚሁ ግለሰብ የተመሰረቱና በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ በቁጥር 1,000 የሚገመቱ የቱርክ የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤቶችንና ልዩ ልዩ የእርዳታ ተቋማትን እንዲዘጉለት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረገም ይገኛል። ከመፈንቅለ መንግስት ሙከራውም በፊት ቢኾን የቱርክ መንግስት በፖለቲካ ተቀናቃኛቸው በጉለን የተያዙ የንግድና የትምህርት ተቋማት እንዲዘጉ ለማድረግ ትልቅ ጥረት ማድረግ ጀምሮ ብዙዎቹን የእንቅስቃሴው ማዕከላት የሚገኙባቸውን የአፍሪካ አገራት ደጅ ሲጠና ቆይቷል። ለብዙዎቹ የአፍሪካ መንግስታት ለረጅም ጊዜ የቱርክን ሕዝብ ወክሎ የበጎ አድራጎትና የኢንቨስትመንት ስራ ሲሰራ የኖረውን የጉለናውያኑን እንቅስቃሴ ማስቀየም ፍላጎት የላቸውም። ሶማልያንና ኢትዮጵያን ከመሰሉ ጥቂት አገራት በቀር የ ኤርዶጋን ጥያቄ ተቀባይነት ያገኘም አይመስልም።

የኢትዮጵያም መንግስት ለዚህ የኤርዶጋን ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት በኢትዮጵያ የሚገኘውን የጉለንን ትምህርት ቤት አሳልፎ ለቱርክ መንግስት ሰጥቷል። በዚህም ምክንያት በሁለቱ መንግስታት መካከል በአዲስ መልክ የተጀመረው ወዳጅነት የሰመረ መስሏል። የኢትዮጵያው ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ በቱርክ የተደረገላቸውም ደማቅ አቀባበል ይህን በሁለቱ መንግስታት መካከል የተጀመረ አዲስ ፍቅር የሚያሳይ ነው። ግንኝነቱንም በንግድና በኢንቨስትመንት ለማጠናከርም መሪዎቹ ቃል ሲገቡም ተስተውሏል።

የነጃሺ መቃብር እና የአልነጃሺ መስጊድ እድሳትም ላይ ድጋፍ ለማድረግ የቱርክ መንግስት ቃል የገባው ኤርዶጋን ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ነበር። ኤርዶጋን በፍሪካ ያላቸውን የፖለቲካ ተሰሚነት ከፍ ለማድረግ ጥረት በሚያደርጉበት ጊዜ ብዙዎቹን የአፍሪካ አገራት ሲጎበኙ ቆይተዋል። በኢትዮጵያ የነበራቸውም ጉብኝት የዚሁ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አንዱ አካል ነበር።

የጉለን እንቅስቃሴ ሰላማዊነትንና የትምህርትን አስፈላጊነት የሚሰብክ፥ የሐይማኖቶች ወንድማማችነት ለዓለም ሰላም ያለውን አስፈላጊነት ከፍ ባለ ድምጽ የሚያሰማ እስላማዊ እንቅስቃሴ መኾኑ ይነገርለታል። ገዢዎቿ ፍትሕ ያውቃሉ የሚል ምስክርነት በነቢዩ መሐመድ የተሰጣት የነጃሺዋ ኢትዮጵያ ግን ዛሬ የስደተኛውን የጉለንን ድምጽ የሚሰማ ገዢ ያላት አትመስልም። የጉለን አሳዳጅ ኤርዶጋን የስደተኛ ጠበቃ የነበሩትን የነጃሺን መታሰቢያ ለማሰራት ያደረጉትም ጥረት ስላቁ ከፍ ብሎ የሚታየውም ለዚሁ ነው።

The post የቱርክ መንግስት በትግራይ የነጃሺ የመቃብር ስፍራንና መስጂድ እድሳት እያጠናቀቀ ነው appeared first on Wazemaradio.

[…]

የደከመን መርገጥ ሳይሆን የደከመን ማገዝ ነው ትክክል – (ምላሽ ለአቶ ይገረም አለሙ)- ግርማ ካሳ

ይገረም አለሙ የተባሉ ጸሃፊ “ድርድሩ” በሚል ያቀረቡትን ጽሁፍ ዘሃበሻ ላይ አነበብኩ። እኝህ ሰው ከሚጦምሩትና ከሚጽፉት ዉጭ ማን እንደሆኑ፣ አገር ቤት ይኑሩ፣ ዉጭ አገር፣ በእዉነተኛ ስማቸው ይጻፉ፣ በብእር ስም ብዙ የማውቀው ነገር የለም። ሆኖም ባቀረቡት ሐሳብ ዙሪያ እኔም የተሰማኝን አንዳንድ ምላሾሽ፣ …

[…]

ሰማያዊ ፓርቲ መሰንጠቅ አልገጠመኝም አለ

yilkal

Yilkal Getnet, ousted Blue Party leader

ዋዜማ ራዲዮ- በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ያገኘው አዲሱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር በፓርቲ ውስጥ መስንጠቅ አለመከሰቱን ይልቁንም ፓርቲው በዲስፕሊንና በምዝበራ ጥፋተኛ ያላቸው የአመራር አባላት ላይ እርምጃ የወሰደበት እንደነበረ አስታወቀ።
ለፓርቲውና ለቀድሞ አመራሮች ክብር ሲባል ጉዳዩን በዝምታ ይዞት መቆየቱን የገለፀው አዲሲ የፓርቲው አመራር ችግሩን በፓርቲው ውስጥ ለመፍታት የተደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ጉዳዩ ወደ አደባባይ መውጣቱንና በአሁኑ ወቅት ፓርቲው በአብላጫው የቀድሞ አመራር አባላትን ይዞ ስራ መቀጠሉን ገልጿል። ዝርዝር ዘገባው የሚከተለው ነው።

የካቲት 8/2009 በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተቸረው የሰማያዊ ፓርቲ አዲሱ ሥራ አስፈፃሚ በዛሬው ዕለት (የካቲት 19/2009) በጽ/ቤቱ በሰጠው የፓርቲው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ፣ የፓርቲው የቀድሞ የፓርቲ መሥራችና የሥራ አስፈፃሚ አባላት የነበሩ፣ እንዲሁም አሁን የብሔራዊ ምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ጌታነህ ባልቻ “ተከስቶ የነበረው ችግር መከፋፈል ሊባል አይችልም” በማለት አስተባብለዋል። “ጥቂት ሰዎች በዲሲፕሊን እና በንብረት ምዝበራ ቢሰናበቱም፣ አሁንም 37 ቋሚ እና 13 ጊዜያዊ አባላት ያሉት ብሔራዊ ምክር ቤት አለ። ሥራ አስፈፃሚውም የጠቅላላውን ጉባዔ እና የምርጫ ቦርድን ዕውቅና አግኝቷል” ብለዋል። በአዲሱ የፓርቲው ሊቀ መንበር አጭር የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው የማብራሪያ መድረክ፣ የተለያዩ ሰነዶችን በማቅረብ በቀድሞው ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል እና ደጋፊዎቻቸው፣ እንዲሁም በአቶ የሺዋስ አሰፋ የሚመራው አዲሱ ሥራ አስፈፃሚ መካከል የነበረው ችግር በቀድሞው ሥራ አስፈፃሚ ድክመት የተፈጠረ እና አሁን ግን እልባት ያገኘ መሆኑን ለማስረዳት ሞክሯል። አቶ የሺዋስ በመክፈቻ ንግግራቸው “እስካሁን ዝም ያልነው፣ አንደኛ የሰውን ክብር ላለመንካት እና ሁለተኛ የመታረቅ ትንሽ ዕድል ካለ ብለን ነበር።” ብለዋል። አቶ ጌታነህም የቀድሞው ሊቀመንበር እና ሌሎች የተባረሩ አባላቱ ለሠላማዊ ትግሉ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ግምት ውስጥ በማስገባት ፓርቲው ጉዳዩን ይፋ ከማድረግ መቆጠቡን ገልጸዋል።

Yeshiwas Assafa, new leader of Blue Party

አቶ ጌታነህ ባልቻ “የችግሩ መነሻ የፓርቲው የቀድሞ ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት እና ሌሎቹም የድርጅቱን ንብረት መመዝበራቸው ነው” ብለዋል። “የንብረት መመዝበሩ ጥያቄ እንደተፈጠረ የሥነ ስርዓት አጣሪ ኮሚቴ ተዋቅሮ ጉዳዩን በመመርመር ያረጋገጠ ሲሆን፣ በዚሁ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ ነባሩን ሊቀመንበር በማውረድ አዲስ ምርጫ በማካሔድ አቶ የሺዋስ የሊቀ መንበርነቱን ቦታ በውስጠ ደንቡ መሠረት ወስደዋል” ብለዋል። አቶ የሺዋስም በመግቢያ ንግግራቸው ከሊቀ መንበር በስተቀር ቀሪው የሥራ አስፈፃሚው ኃላፊዎች ባሉበት መቀጠላቸውን አስረድተዋል።

ከፓርቲው አስራ አምስት መስራች አባላት መካከል አንዱ ብቻ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የቀድሞውን ሊቀመንበር ጨምሮ ሁለት ተጨማሪ መሥራች አባላት በሥነ ስርዓት ጉድለት በመታገዳቸው መሥራች ዐሥራ አንድ አባላት የፓርቲውን ሥራዎች ለማከናወን በሚጥሩበት ሰዓት ፓርቲው እንደተሰነጠቀ መነገሩ ትክክል አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል። የድርጅቱን ንብረት መዝብረዋል የተባሉት 5 ሰዎች በድርጅቱ ደንብ መሠረት ክስ የቀረበባቸው እና በደንቡ መሠረት የተከራከሩ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ጥፋተኛ መሆናቸው ሲበየን፣ አቶ ይልቃልን ጨምሮ በይቅርታና በቅጣት ለመታለፍ ያልፈቀዱት አራቱ ከአባልነት ሲሰናበቱ አቶ ጌታነህ ባልቻ ግን በቅጣት ታልፈው የአዲሱ የሥራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ቀጥለዋል። የአጣሪው ኮሚቴ ገለልተኝነት፣ የተመዘበረው ንብረት ግምት፣ የጠቅላላ ጉባዔው ምልዓትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባላት ሲመልሱ የሥነ ስርዓት አጣሪ ኮሚቴው ሦስት አባላት በምክር ቤቱ የፀደቁ በመሆናቸው ገለልተኛ ናቸው ብለዋል። ተመዘበረ የተባለውን ገንዘብ ትክክለኛ መጠን ለመግለጽ በተደጋጋሚ ያመነቱት አቶ ጌታነህ፣ በመጨረሻ “ከመጀመሪያ ጀምሮ ከተደረጉት 3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪዎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ በሰነድ ሳይወራረድ የቀረ ነው” ብለዋል። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር አስቸጋሪ ገጽታ ምክንያት ለቅስቀሳ የሚታተሙ በራሪዎች እና ተመሳሳይ ወጪዎች የሦስተኛ ወገንን ደኅንነት ከመጠበቅ አንፃር ያለ ደረሰኝ ሊሠሩ እንደሚችሉ እና ችግሩ በዚህ ሳቢያ ተፈጥሮ እንደሆነ እና የአሠራር ክፍተት ካለ የተጠየቁት አቶ ጌታነህ፣ “እንደዚህ ዓይነት ወጪዎች በልዩ ቃለ ጉባኤ የሚፈፀምበት አሠራር አለን” በማለት የአሠራር ክፍተት ለምዝበራ እንዳላጋለጣቸው አስረድተዋል። የጠቅላላ ጉባዔውን ምልዓት በተመለከተ በመተዳደሪያ ደንቡ የተወሰነ ቁጥር ባይኖርም ሰማያዊ ፓርቲ መዋቅሮቹን በዘጋባቸው ወረዳዎች ቁጥር ልክ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት እንደሚኖረውና በ2007 አቶ ይልቃል ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ በፀደቀው እና ከዚያ ጀምሮ ለ3 ዓመታት በሚያገለግለው 226 አባላት ያሉት ጠቅላላ ጉባዔ ዳግም ጥሪ ተደርጎ፣ 129 አባላት ተገኝተው ኮረም በመሙላቱ በተደረገው ምርጫ አቶ ይልቃል ወርደው አቶ የሺዋስ በምትካቸው ተመርጠዋል። በአቶ ይልቃል እና ደጋፊዎቻቸው ከተነሱ ቅሬታዎች መካከል፣ የፓርቲው አባላት ያልሆኑ ሰዎች መገኘታቸው አግባብ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ አቶ የሺዋስ “ታዛቢ እንዲኖር በማለት ከቀድሞው አንድነት ፓርቲ፣ ከመኢአድ እንዲሁም ከምርጫ ቦርድ ታዛቢ ጋብዘናል። እነዚህ ግን በደምፅ ቆጠራው አልተሳተፉም። የአቶ ይልቃል ደጋፊ የነበሩ 13 ሰዎች ከ129ኙ በተጨማሪ ቢገኙም ጉባዔውን ለማስተጓጎል እንጂ ለመሳተፍ ፊርማቸውን ለማኖር ስላልፈቀዱ በጠቅላላው ጉባዔ ውሳኔ እንዲወጡ ተደርገዋል” በማለት ተሳታፊዎቹ የፈረሙበትን ሰነድ አሳይተዋል። ጠቅላላ ጉባዔው የተካሔደው ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ ነው በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የተራገበውን ዜና ሲያስተባብሉም፣ አቶ ጌታነህ ሁለት ደብዳቤዎችን አቅርበዋል። የመጀመሪያው ከፓርቲው ለሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ሰጪ ጉባዔውን ለማካሔድ የተጠየቀበት ደብዳቤ ሲሆን፣ ሁለተኛው የሰሜን አሜሪካው ድጋፍ ሰጪ ድጋፍ ማድረጉን የገለጸበት እና ለአቶ ይልቃል ጌትነትም ግልባጭ የተወበት የኢሜይል መልዕክት ነው። ከቀድሞው ሊቀ መንበር እና ደጋፊዎቻቸው ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት፣ በወቅቱ ከሁለት ዓመት እስር በኋላ በነጻ የተፈቱት አቶ የሺዋስ አሰፋ በግንቦት ወር 2008 ልዩነቱን በእርቅ ለመፍታት ንግግር ላይ የነበሩ መሆናቸውን አስታውሰው፣ በዚህ ውይይት መሐል ሊቀ መንበሩ አቶ ይልቃል ወደካናዳ መሔዳቸውን የውይይቱ አካላት እንደማንኛውም ሰው ከሚዲያ መስማታቸውን ተናግረዋል። የቀድሞውም፣ የአሁኑም ሥራ አስፈፃሚ ውስጥ በውጭ ጉዳይ ኃላፊነት የሚያገለግሉት አቶ አበበ አካሉም “እኔ እንኳን አቶ ይልቃል በፓርቲው ሥም ሊሔዱ ስለመሆናቸው ምንም መረጃ አልነበረኝም። ፓርቲው የግለሰብ ንብረት የሆነ ያክል ነበር። እኔ የማገለግለው የኢትዮጵያ ሕዝብን እንጂ የፓርቲውን ሊቀመንበር አይደለም” በማለት በምሬት ተናግረዋል። የገንዘብ ምዝበራው አሁንም እንደቀጠለ የተናገሩት አቶ ጌታነህ፣ “በቅርቡ ከሰሜን አሜሪካ ደጋፊዎቻችን የተላከልን 7,600 ዶላር ድጋፍ አቶ ይልቃል እጅ ከገባ በኋላ ወደ ፓርቲው ገቢ አልተደረገም። ደጋፊዎቹም እውነቱን ሲያውቁ ለማስመለስ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካላቸውም” ብለዋል። “ከዚህም ውጪ ሌሎች ምዝበራዎች አሉ” ያሉት አቶ ጌታነህ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊወስዱት እንደሚችሉም ጠቁመዋል። የቀድሞ የፓርቲ መሪ ይልቃል ጌትነት ግን የአዲሲ አመራር እርምጃ ፓርቲውን ለማፍረስ የተቀነባበረና ባልታወቁ ሀይሎች የተቀነባበረ ሴራ ነው ሲሉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እያለ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ላይ 12 የቀድሞ የፓርቲ አባላትን የያዘ ሁለት ኮሚቴ መመሥረቱ ተነግሯል። የአቶ ይልቃል ደጋፊዎች የምርጫ ቦርዱን ውሳኔ በፍርድ ቤት ሊሞግቱት ይችላሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የኮሚቴው አባል እና ከሦስት ወራት የማዕከላዊ እስር በኋላ በቅርቡ የተፈቱት፣ የሕግ ባለሙያው አቶ አዲሱ ጌታነህ በትላንትናው ዕለት አመሻሹ ላይ ባልታወቁ ሰዎች በጩቤ ተወግተው ሆስፒታል መግባታቸው ተነግሯል።

The post ሰማያዊ ፓርቲ መሰንጠቅ አልገጠመኝም አለ appeared first on Wazemaradio.

[…]

ዞን ዘጠኞችና ጋዜጠኞች በተገኙበት የሰማያዊ ፓርቲ መሰረታዊ መልሶችን ሰጠ – የሚሊዮኖች ድምጽ

“መሰረታዊ መልሶች!” በሚል የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢና የሕግ ባለሞያው አቶ ይድነቃቸው ከበደ ዛሬ የካቲቲ 19 ቀን ፓርቲው በውስጣዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጽ/ቤቱ ስላደረገ ገለጻ ማብራሪይ ሰጥተዋል።

የቀድሞ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል የፓርቲው የበላይ አካል የሆነውን የጠቅላላ ጉባዬ ውሳኔ አልቀበልም …

[…]

የአለቃ ጸጋየ በርሄና የህላዊ ዮሴፍ ወጎች፤ ከሹመት እስከ ሽረት፤

የህወሓት-እስራኤል ቀጣይ የፖለቲካ ቁማር! አሁን ባለዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ለህወሓት/ኢህአዴግ ቁልፍ የስጋት ምንጩ የዲያስፖራዉ የተቃዉሞ ጎራ ነዉ፡፡ የድህረ-ምርጫ 97 ዉርስ ዕዳ የሆነዉ የዲያስፖራዉ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እንደ ሀገር ቤቱ ሁሉ በዘዉግ ፖለቲካ የሚታመስ ቢሆንም በጋራ ጠላት (ህወሓት/ኢህአዴግ) መዉደቅ ላይ ያለ አንዳች የልዩነት መስመር ይስማማል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ሀገር ቤት ያሉት የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከሚያሰሙት ጩኅት በላይ […] […]

ማጭበርበር የማይሰለቸው ወያኔ የውጪ ሀገር ስደተኞችን ለማቋቋም እየሰራሁ ነው አለ

ማጭበርበር የማይሰለቸው ወያኔ የውጪ ሀገር ስደተኞችን ለማቋቋም እየሰራሁ ነው አለ. የራሱን ዜጎች እያባረረ የሌላ አገር ስደተኞችን የሚያቋቁም ደነዝ አገዛዝ እድሜው አጭር ነው።

– የአውሮፓ ህብረትና ኔዘርላንድ ለስደተኞች ማቋቋሚያ የ720 ሚ. ብር ድጋፍ አድርገዋል
– ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች በየጊዜው እየጨመሩ …

[…]

የቀድሞው የጋምቢያ ፕሬዚዳንት የዘረፉት ገንዘብ 1 ቢ. ዶላር ደርሷል

በምርጫ ቢሸነፉም ስልጣኔን አልለቅም ብለው ለሳምንታት ካንገራገሩ በኋላ በተደረገባቸው ጫና አገራቸውን ጥለው የተሰደዱት የቀድሞው የጋምቢያ ፕሬዚዳንት ያያ ጃሜህ ከአገሪቱ ካዘና ያለአግባብ የዘረፉት ገንዘብ 1 ቢሊዮን ዶላር ያህል መድረሱን አዲሱ የአገሪቱ መንግስት አስታወቀ፡፡
አዲሱ የአዳማ ባሮው መንግስት ሚኒስትሮች ያወጡትም መረጃ ጠቅሶ …

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.