Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

ለውጥ

ለውጥ ከሩቅ አይመጣም ከቅርብ እንጂ፡፡ ለአንድ ግለሰብ መለወጥ ለውጥ ከውስጡ እንዲመጣ ያስፈልጋል፡፡ ለአንድ ቤተሰብ መለወጥ ደግሞ የቤተሰቡ አባላት መለወጥ የግድ ነው፡፡ ለአንድ ማዕበረሰብ ደግሞ እያንዳንዱ ቤተሰብ የሚያዋጡት ድምር ውጤት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ ስለዚህ ሀገር እንዲለወጥ እያንዳንዳችን መለወጥ ይኖርብናል፡፡

ይህንን ክታብ የከተብኩት ፕሬዝደንት ኦባማ ተመርጠው የለውጥ ዜና ትኩሳት ሳይበርድ ነው፡፡ ለውጥ!/Change!/ የሚለውን ሞቶ ይዘው የተነሱት ፕሬዝደንት ኦባማ ያሰቡትን ለማሳካት ከሁለት ዓመት በላይ የፈጀው የምረጡኝ ዘመቻው ብቻ ሳይሆን ለአሜሪካ ሕዝብ ገዝፎ የታየው ማንነታቸው ነው፡፡ ምንም እንኳን ዘረኝነት በአሜሪካ እጅግ የሳሳ ቢሆንም እነ ማርቲን ሉተር ኪንግ የጀመሩት ትግል ብዙ ትውልድ እንኳ ሳይተካ ጥቁር የአሜሪካ ፕሬዝደንት ይሆናል ብሎ ያሰበ የለም፡፡

ይህንን ታሪካዊ ክስተት ስናጣጥም እኔ መቼ ነው የምለወጠው? እኛ መቼ ነው የምንለወጠው? ኢትዮጵያ መቼ ነው የምትለወጠው? የሚል ጥያቄ አይምሮ ከመጠየቅ ወደ ኋላ አይልም፡፡ እንደኔ አመለካከት እያንዳንዳችን ከተለወጥን ፤ ሁለ ገብ የሆነ ለውጥ ላይ ከሠራን ጊዜ ሊወስድ ቢችልም ቀላል ነው ባይ ነኝ፡፡ ፕሬዝደንት ኦባማ ለውጥ ያሉለትን አላማ አንግበው ስኬትን ለማግኘት አስተዳደጋቸው ፤ በትምህርት ያላቸው ውጤት ፤ በበጉ አድራጎት ሥራ (Community Service) ያደረጉት አስተዋጽኦ ፤ በሥራው ዓለም የነበራቸው ስኬት ፤ በፓለቲካው ጅምራቸው የነበረው ውጤታማነት ሁሉ አስተዋጽኦ ነበረው፡፡

በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ ለሀገር እድገት እና ለውጥ በፓለቲካው መድረክ ከመሳተፍ ያለፈ ድርሻ ያለ አይመስልም፡፡ ተምሮ በተማረበት ዘርፍ ስኬታማ መሆን፤ ነግዶ በንግዱ ዓለም እጅግ ስኬታማ የሆነ ሚሊኒየር መሆን ፤ በበጎ አድራጎት ሥራዎች ትውልድን የሚቀርጽ ሥራዎችን በመሥራት ተተኪ ትውልድ ማፍራት ለኢትዮጵያ መለወጥ ቦታ የሊላቸው እስኪመስሉ ድረስ አስታዋሽ የላቸውም፡፡ ነገር ግን ለሀገሪቱ መለወጥ ይህንን መሠል አገልግሎቶች መስፋፋት ፤ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ አቅም በማጎልበት ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሰማራበት ዘርፍ የላቀ ስኬታማ ማድገግ ይገባል፡፡

በተለይ በዲያስፓራ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ከውጪው ዓለም የምናገኘውን ዕድል ቅድሚያ እራሳችን ስኬታማ ሆነን ለራሳችን እና ለቤተሰቦቻችን እንድንተርፍ ፤ ከዚያም አልፈን ከሌሎቹ ልቀን በመገኘት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነትን ማግኘት ለሀገራችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የምንፈልገው ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ እንችላለን፡፡ ለዚህ የጁውሾችን ተሞክሮ መውሰድ ይቻላል፡፡ ለእስራኤል ባለችበት መቆየት እያንዳንዳቸው ባሉበት ሀገር ስኬታማ በመሆን ኢኮኖሚውን እና ፓለቲካውን ፤ ማሕበረሰቡን እና ሚዲያውን በመቆጣጠር ለሀገራቸው የሚያስፈልጋት ሁሉ በቀላሉ እንዲደረግላት ማድረግ ችለዋል፡፡

በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ የአንድ ወይም የሌላ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ካልሆናችሁ ፤  አንዱን ወይም ሌላኛውን የፓለቲካ ፓርቲ ካልተቃወማችሁ ለሀገር የማታስቡ፤ ግድ የለሾች አርገው የሚቆጥሩ ሰዎች ያጋጥሙኛል፡፡ ሁሉም ሰው ፓለቲከኛ መሆን አለበት የሚል አመለካከት ጤናማ አይደለም፡፡ በሕክምና ፤ በምሕንድስና ፤ በመምህርነት ፤ በሳይንስ እና ምርምር ፤ በማሕበረሰብ ሳይንስ ወዘተ የሚሳተፈው ሰው ሁሉ ባለበት ሙያ ስኬታማ ሆኖ ሀገር የምታድግበትን ማሰብ ከቻለ በቂ ነው፡፡ በፓለቲካ ዘርፉ የሚሳተፍም እንዲሁ፡፡ በዲያስፖር ለምንኖር ኢትዮጵያዊያን ፓለቲካ ወይም ሃይማኖት ካልሆነ በስተቀር ማኅበረሰባዊ የሆኑ አጀንዳዎችን የሚያንሸርሽር ፤ ማኅበራ ችግሮችን የሚፈታ ፤ የአኗኗር ዘይቤን የሚረዳ ማስ ሚዲያም ሆነ ድረ ገጾችን ወይም ብሎግ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ሀበሻ 360 (habesha360.com) ይህንን ክፍተት ለመሙላት በመመስረትዋ እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡

እርስ በእርሳችን ስለ ባህላችን ፤ ሥርዓታችን ፤ ታሪካችን ልንማማር ያስፈልጋል፡፡ ስለ ትዳር ፤ ልጅ አስተዳደግ ፤ እጮኝነት እና ጋብቻ ፤ ስለ ትምህርት እና የተሻለ ኑሮ ስለመምራት ፤ ስለ ጥሩ ስነ-ምግባር እና ኢትዮጵያዊነት እኛው ለእኛ ካልጻፍን ማን ይጽፍልናል፡፡ ለውጥ ያለዕውቀት አይመጣምና ለመለወጥ መማር የግድ ነው፡፡ ለመማር ደግሞ አስተማሪ ያስፈልጋል፡፡ አስተማሪ ደግሞ ሁል ጊዜ ተማሪ ነው፡፡ ስለዚህ እያስተማርን ለመማር ልንነሳ ያስፈልጋል፡፡ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን የተሻሉ አድርገን በመቅረጽ ኢትዮጵያን እንለውጣት፡፡ ለውጥ ለኢትዮጵያ! Yes We Can!

ዘሀበሻ

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.