“ውይይት በአደባባይ» የተባለው ዝግጅት በ”አደባባይ የጡመራ መድረክ» እየተዘጋጀ የሚቀርብ ግልጽ የውይይት መድረካችን ነው። አሐዱ ብለን በምንጀምረው በዚህ የመጀመሪያ ዝግጅታችን የመርሐ ግብሩ አዘጋጅ ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ ከሁለት እንግዶች ጋር ይመካከራል። እንግዶቻችን ቀሲስ አሸናፊ ዹጋ እና ቀሲስ ንዋይ ካሳሁን ናቸው። የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሎጅ ምሩቃን የሆኑት ሁለቱ እንግዶች በተለያዩ እርከኖች ቤተ ክርስቲያናችንን ያገለገሉና በማገልገል ላይ የሚገኙ ናቸው። “የአገራችን ወቅታዊ ችግር እና የክርስቲያኖች ሚና» በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የተደረገው ውይይት እነሆ።