የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በግራ ዘመም እና መሠረተ-ጎሳ በሆኑ የአገራችን የፖለቲካ አስተሳሰቦች ዘንድ በጠላትነት እንደምትፈረጅ የአደባባይ ምሥጢር ነው። በዚህ ረገድ የሕወሐት የ40 ዓመት ፖለቲካ እና በኦነግ እና ከዚያም በኋላ በተነሡ የኦሮሞ ፖለቲካ አራማጆች ዘንድ ያለው አመለካከት ተጠቃሽ ነው። እነዚህ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ቤተ ክርስቲያኒቱን በጠላትነት የረጁበትን ዝርዝር ጉዳይ ለጊዜው ብናቆየው እና በኦሮሞ ልሒቃን አካባቢ የሚጠቀሰውን አንድ መጽሐፍ (ራእየ ማርያምን) ብቻ ብናነሣ፣ ጥላቻው መሠረት የሌለው ይልቁንም በግልሰቦች ስሕተት እና ተደጋጋሚ ስሕተት ላይ የሚያጠነጥን መሆኑን እንመለከታለን። ስለዚህም በዚህ ዙረያ የተደረገ አንድ የመነሻ ውይይት እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።