Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ የግል ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አገደ

ዋዜማ- ከወራት ማመንታት በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ የግል አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ እገዳ መጣሉን መኪና አስመጪ ድርጅቶችና ተሽከርካሪ ለማስገባት የሞከሩ ግለሰቦች ለዋዜማ ተናግረዋል።

ምንጮቻችን እንደነገሩን ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ከአውሮፓና ደቡብ አፍሪቃ ያጓጓዟቸውን በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ማስገባት እንደማይችሉ ከሶስት ሳምንት በፊት ተነግሯቸዋል። በእገዳው ሳቢያ ከፍተኛ መጉላላትና ኪሳራ እንደደረሰባቸው ባለጉዳዮቹ ነግረውናል።

ከሳምንታት በፊት የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማገዱን ለፓርላማ አባላት ሲያስታውቅ የገንዘብ ሚኒስቴር በበኩሉ እገዳው ተገባራዊ እንደማይደረግና በዕቅድ ደረጃ ያለ መሆኑን ተናግሮ ነበር።

ይሁንና ባለፉት ቀናት የተለየ ፍላጎት ላላቸው የልማት ፕሮጀክቶችና ለህዝብ ትራንስፖርት የሚውሉ ካልሆኑ በቀር በነዳጅ የሚሰሩ የግል ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር አይገቡም።

“እንዲህ አይነቱ አሰራር ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ ዝግጅት እንድናደርግና ከውጪ ተጭነው በመንገድ ላይ ያሉና የውጪ ምንዛሪ የወጣባቸውን ተሽከርካሪዎች እንድናስረክብ ዕድል መሰጠት ነበረበት” ይላሉ በከተማዋ በአስመጪነት ስራ የተሰማሩ ባለሀብት።በመጪው ሳምንት ከትራስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ጋር ለመነጋገር ማቀዳቸውንም ነግረውናል።

በውጪ ሀገር ከሀያ ዓመታት በላይ የቆየ ሌላ ግለሰብ ደግሞ አቅሜ የሚፈቅደውን አይነት ለግል መገልገያ ተሽከርካሪ ገዝቼ አስፈላጊውን የጎምሩክ መስፈርት ባሟላም፣ መኪናውን ማስገባት እንደማልችልና ወደመጣበት እንደመልሰው ተነግሮኛል ይላል።

መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ የግል ተሽከርካሪዎችን ያገደው የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና የነዳጅ ወጪውን ለመቀነስ መሆኑን ገልጿል።

ከሰሞኑ ለዋልታ መግለጫ የሰጡት የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚንስትሩ አለሙ ስሜ የነዳጅ መኪና ክልከላው ተግባራዊ መደረግ መጀመሩንና መንግስት የኤሌክትሪክ መኪና ላይ ከፍተኛ የቀረጥ ማበረታቻ ማድረጉን አረጋግጠዋል።

መንግስት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የባትሪ መኪናዎችን እንደሚያበረታታና እንደሚያስፋፋም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

ሚንስትሩ አክለውም ህብረተሰቡ በነዳጅ የማይሰሩ የትራንስፖርት አማራጮችንና የጋማ ከብትና ብስክሌት እንዲጠቁም ብሎም በግሩ መጓጓዝን ልማድ እንዲያደርግ መክረዋል።

ሚኒስቴሩ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚውሉና የተለየ ምክንያት ላላቸው የግል ላልሆኑ ተቋማት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እንዳማይከለክል አለሙ ስሜ ጠቁመዋል።

ይህ አሰራር የሀገሪቱ የአረንጓዴ ልማት አንድ አካል መሆኑንና “በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት” በካቢኔ ውይይት ተደርጎበት ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረም ሚንስትሩ አመልክተዋል።

በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ መኪናዎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን ተከትሎ በሀገር ውስጥ ስላሉት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ምን ዕቅድ እንዳለው መንግስት አላሳወቀም። [ዋዜማ]

The post መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ የግል ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አገደ first appeared on Wazemaradio.

The post መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ የግል ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አገደ appeared first on Wazemaradio.

Source:: https://wazemaradio.com/%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%8A%90%E1%8B%B3%E1%8C%85-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%B0%E1%88%A9-%E1%8B%A8%E1%8C%8D%E1%88%8D-%E1%89%B0%E1%88%BD%E1%8A%A8%E1%88%AD%E1%8A%AB/?utm_source=rss&utm_medium=rss&utm_campaign=%25e1%2588%2598%25e1%258a%2595%25e1%258c%258d%25e1%2588%25b5%25e1%2589%25b5-%25e1%2589%25a0%25e1%258a%2590%25e1%258b%25b3%25e1%258c%2585-%25e1%258b%25a8%25e1%2588%259a%25e1%2588%25b0%25e1%2588%25a9-%25e1%258b%25a8%25e1%258c%258d%25e1%2588%258d-%25e1%2589%25b0%25e1%2588%25bd%25e1%258a%25a8%25e1%2588%25ad%25e1%258a%25ab

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.