Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

ስፓርትና ፓለቲካ?

ሰሞኑን ሁሉ የዜና ማሰራጫዎች ያቶከሩበት አንድ ነገር ቢኖር ለንደን ኦሎምፒክ ነው። በየአራት ዓመቱ አንዴ የሚደረገው የኦሎምፒክ ወድድር በዓለም ሕዝቦች ዘንድ ትልቅ አትኩሮት ካላቸው የስፓርት ውድድሮች ዋነኛው ነው። ስፓርት ለሰላም ለፍቅር ለወዳጅነት እያልን እዳደግን ሁሉ በየአህጉሩ ያሉ ሀገሮች በአንድ ላይ ተሰብስበው ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለወዳጅነት የሚቆሙበት ነው። የኦሎምፒክ አዘጋጅ የሆነችውም ሀገር ለናሙና ከየሀገሩ የተወሰዱባት ትንሻ ዓለም ነው የምትሆነው ብለን ብንናገር ማጋነን አይሆንም። ውድድሩን ለማሸነፍ የሚታደሉት ጥቂቶች ቢሆኑም ከየሀገሩ ለመሳተፍ የሚመጡት ስፓርተኞች ስፍር ቁጥር የላቸውም። በለንደኑ ኦሎምፒክ ከ14፣000 በላይ ስፖርተኞች ከ205 ሀገራት ተሳታፊ ሆነዋል።

 

ኢትዮጵያ በዓለም ስማ አዘውትሮ ከሚነሳበት አራት ነገሮች አንድ አትሌትክስ ነው። በእነ አበበ ቢቂላ ስማ በአትሌቲክስ መነሳት የጀመረው ኢትዮጵያ እነ ምሩጽ ፤ ኃይሌ ፤ ቀነኒሳ ፤ ደራርቱ ፣ ፋጡማ ፣ መሠረት ፤ ጥሩነሽ … ስማቸውን ጠቅሼ የማልጨርሰው አትሌቶች ስሟን በወርቅ ጽፈው አልፈዋል። የተቀሩት ሦስቱ የትኞቹ ናቸው ብላችሁ ሆዳችሁን እንዳይበላቹ ማብራራት ባያስፈልግም ጠቅሼ አልፋቸዋለው። ሁሌም አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንሔድ የሚያደርገን ጥንታዊ ታሪካችን እና ሀይማኖታችን ሁለቱ ሲሆኑ ሦስተኛው አንገት የሚያስዳፋን ድህነታችን ናቸው። እንዴት እንደነጮቹ ኢትዮጵያን በድህነት አንተም ታነሳታለህ እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ብዙዎቻችንን ከሀገር ያሰደደን የተበላሸ ፓለቲካችን እና ድህነታችንም አይደል።

 

በዚህ በሰሞኑ የለንደን ኦሎምፒክ ሁለት ወርቅ በ ጥሩነሽ ዲባባ እና ገላና ቲኪ እንዲሁም መዳብ በታሪኩ በቀለ አግንተን ይህ ጽሑፍ እስከምጽፍበት ሰዓት ድረስ በዓለም ሰንጠረዝ 19ነኛ ፤ በአፍሪካ ሁለተኛ ፤ በአትሌቲክስ እንዲሁ ሁለተኛ ሆነን ስማችን ገኖ እየተነሳ ነው። ብዙዎች በቀነኒሳ የአስር ሺህ ሜትር ርቀት ውድድር ወርቅ አለማግኘታችን ቢያበሳጭም የሁል ጊዜ ኩራታችን ቀነኒሳ ሁሌም የሚነሳ ጀግና እንደሆነ ልንዘነጋ አይገባም። ሰው በመሆኑ እንደሰው ይደክማል ነገ ደግሞ ይበረታል እና ሰው መሆኑን መዘንጋት አይገባም። እስካሁን ባለው ድል እንኳን ደስ ያለን። ገና ከአትሌቶቻችን ብዙ እንጠብቃለን።

 

ይህን ጽሑፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ የአትሌቶቻችን ድል ሳይሆን እርሱን ተመልክቶ የሰማሆት አስቀያሚ ፓለቲካ ስለኮረኮረኝ ነው። የጥሩነሽን ድል አስመልክቶ ደስታ ለመግለጽ እና አስተያየት ለመስጠት በአንዱ የዲሲ ሬዲዮ ከታደሙ አንዱ ጋዜጠኛ ድሉን ከሚያራምደው የፓለቲካ ፓርቲ ድል ጋር ሲቀላቅለው ውሃና ዘይት ቢሆንብኝ። የአትሌቶቻችንን ድል ሃገሪቱን የሚመራው ፓለቲካ ድል ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝቦች ድል ነው። የዓለም ሕዝቦችም ድል ሁሉ። ከላይ በመግቢያዮ ላይ እንደጀመርኩት በጦርነት ያሉ ሀገሮች እንኳን በፍቅር የሚወዳደሩበት የአትሌቲክስ ድል ፤ በስደትም ሆነ በሀገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ድል ነው እነጂ “ጋዜጠኛ” ተብዮው እንዳሉት የሚወገን ፓለቲካ አይደልም። አንዳንዴ የማይቀላቀል ለመቀላቀል መሞከር መሃይምነት ካልሆነ ምን ይባላል። ገና ለገና ድሉ የእገሌ ፓለቲካ ድል ነው ብሎ ሕዝቡ አትሌቱን እና ሀገሩን እንዲጠላ ለማድረግ ከሚሞክር ወንጀል ውጪ ምን እንለዋለን።

 

ብዙ ጊዜ ፓለቲካ እጅግ እንደማይስማማኝ ከሰዎች ጋር ስወያይ “ሁሉም ነገር ፓለቲካ አለው” ፓለቲካን መሸሽ አትችልም የሚሉ ሰዎች ይበዛሉ። ሁሉም ነገር የራሱ ፓለቲካ እንዳለው አውቃለሁ። እኔ ግን የፓለቲካን ፓለቲካ እንዳልኩ እንዲያሰምሩልኝ ግድ እላቸዋለሁ። ፓለቲካ አይስማማኝም ማለት ፓለቲካ ወይም የፓለቲካ ፓርቲ አያሰፈልግም ማለት አይደለም። ሁሉም የራሱ ጸጋ እንዳለው ሁሉ ለኔ ጸጋዮ አይደለም ለማለት እንጂ። የስፓርት ጋዜጠኛው – የፓለቲካ ተንታኝ ልሁን ቢል መልካም አይሆንም። ሀገራችን ብዙ ማደግ ያለባት ዘርፎች አሏት ስለ ታሪክ ፣ ሃይማኖት ፣ ባህል ፣ የሕብረተሰብ አኗኗር ፣ ስፓርት ወዘተ የሚተነትኑ ባለሙያዎች – የሚያደንቁ ደጋፊዎች ያስፈልጉናል የፓለቲካ ብቻ አይደለም። ስለዚህ የማይቀላቀለውን ሳንቀላቅል ሀገራችንን እና ማሕበረሰባችንን እናሳድግ።

 

 

ዘሚካኤል

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.