Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data – 19 March 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 19 March 2024.

[…]

Ethiopia: Government Tackles Challenges in Vertical Coffee Trading Platform

coffee-5278346 1280

The Ethiopian government is addressing concerns within the coffee industry, urging suppliers and exporters to uphold their obligations on the vertical trading platform. This platform, designed to connect farmers and suppliers directly with exporters, has faced issues impacting both farmers and national export targets.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data – 18 March 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 18 March 2024.

[…]

Ethiopia: Ethio Telecom's Telebirr Platform Sees Soaring Success in Ethiopia

Ethio Telecom

Ethio Telecom’s digital payment platform, Telebirr, has facilitated a staggering Birr 1.9 trillion in transactions, according to Ethio Telecom’s Executive Officer Firehiwot Tamiru.

[…]

Ethiopia: Tana Beles Sugar Factory Faces Hurdles on Road to Production

Tana Beles

The Tana Beles sugar factory, envisioned as a solution to Ethiopia’s sugar supply woes, has yet to launch operations this year due to unforeseen challenges.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data – 18 March 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 18 March 2024.

[…]

ንግድ ባንክ የተወሰደበትን ገንዘብ ለማስመለስ ዘመቻ ሊጀምር ነው

ዋዜማ- ቅዳሜ ዕለት በየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል መዋቅር ላይ የተከሰተውን ግድፈት ተጠቅመው ገንዘብ የወስዱ አካላትን ለማደን ግብረ ኀይል መቋቋሙን ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ሰምታለች።

ከብሔራዊ ባንክና ንግድ ባንክ ባለሙያዎች እንዲሁም የፀጥታ አካላት የተካተቱበት ይህ ግብረ ኀይል በስድስት ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ከባንኩ ያለ አግባብ ተወስዷል ያለውን ገንዘብ ለማመለስ ያለመ ነው። ባንኩ የተወሰደበትን የገንዘብ መጠን አላሳወቀም። ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ግን ከ66 ሺህ በላይ ደንበኞች አካውንት በችግሩ መታወኩን፣ ቅዳሜ ለስድስት ሰዓታት በቆየው መታወክ 25 ሺ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መደረጉን እንዲሁም ሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ተንቀሳቅሷል። ባንኩ መረጃውን ማረጋገጥ አልፈለገም።

አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ከወዲሁ ገንዘብ ከክፍያ ማሽኖች የወሰዱና በህገወጥ ዝውውሩ የተሳተፉ ተማሪዎች ገንዘቡን ለባንኩ እንዲመልሱና ራሳቸውን ከህግ ተጠየቂነት እንዲያተርፉ የሚያሳስብ ጥሪ አድርገዋል።

በባንኩ ላይ የደረሰው ችግር የሳይበር ጥቃት አለመሆኑንና ውስጣዊ ግድፈት መሆኑን ባንኩ አበክሮ ገልጿል።

የባንኩ የውስጥ ምንጮች ለዋዜማ እንደተናገሩት ግን ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተከናወነ አንድ መንግስታዊ የባንክ ክፍያ (ከአንድ መቶ ሚሊየን ብር ያላነሰ) ከአንድ በላይ የከፋይ ወገን በዲጂታል ፊርማ ሊያፀድቀው ሲገባ በአንድ ሰው ፈራሚነት ወደ ተከፋይ መተላለፉ የባንኩን ሀላፊዎች አስደንግጦ ነበር። አርብ ዕለት ችግሩን ለማወቅና ለመፍታት ሙከራ ሲደረግ መዋሉንና የቅዳሜ ሌሊቱ ቀውስ መከተሉን ሰምተናል።

ባንኩ የሳይበር ጥቃት አለመፈፀሙን ይናገር እንጂ ክስተቱ በባንኩ ዲጂታል መዋቅር ላይ በውስጥ አዋቂ የተፈፀመ ጥቃት ሊሆን እንደሚችል የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ባንኩ ከተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ ጋር በተያያዘ በርካታ ሰራተኞችን ከስራ ያሰናበተ መሆኑን ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል።

ብሄራዊ ባንክ፣ ቅዳሜ እለት በንግድ ባንክ ላይ ያጋጠመው የአገልግሎት መቋረጥ በባንኩ አገልግሎት መስጫ ሥርዓት ላይ ከተደረገ የደኅንነት ፍተሻና የማሻሻያ ሥራ ጋር የተያያዘ እንደኾነ ገልጧል።

ብሄራዊ ባንክ፣ ክስተቱ የባንኩን፣ የደንበኞቹንና አጠቃላይ የፋይናንስ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል አለመኾኑን አረጋግጫለኹ ብሏል። ባንኩ፣ ችግሩ ባስከተላቸው ጉዳቶች ላይ ምርመራ አድርጎ ውጤቱን ወደፊት እንደሚገልጥ አስታውቋል። ባኹኑ ወቅት የኹሉም የፋይናንስ ተቋማት የፋይናንስ ሥርዓቶች ደኅንነቸው የተጠበቀ መኾኑን ባንኩ ገልጦ፣ ኅብረተሰቡ ያለ ስጋት የፋይናንስ አገልግሎቶችን መጠቀም እንዲቀጥል አሳስቧል። [ዋዜማ]

The post ንግድ ባንክ የተወሰደበትን ገንዘብ ለማስመለስ ዘመቻ ሊጀምር ነው first appeared on Wazemaradio.

The post ንግድ ባንክ የተወሰደበትን ገንዘብ ለማስመለስ ዘመቻ ሊጀምር ነው appeared first on Wazemaradio.

[…]

የአዲስ አበባን ምልክቶች ማፍረስ? (VIDEO)

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከተማይቱን እንደስሟ “አዲስ አደርጋለሁ” ብሎ የተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክቶችን እያካሄደ ነው። የከተማዋን ነባር ሰፈሮች ብሎም የከተማዋን ታሪክ የሚያንፀባርቁ ቅርሶችን ሳይቀር እያፈረሰም ነው። “ይህ ፈረሳ በከተማዋ አዲስ ማንነትን ለማንበር የሚደረግ ዘመቻ ነው” ሲሉም የሚተቹት አሉ። በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው ጋር በዋዜማ ከስምንተኛ ወለል ተመልክተነዋል። ከታች ተያይዟል ተጋበዙልን

The post የአዲስ አበባን ምልክቶች ማፍረስ? (VIDEO) first appeared on Wazemaradio.

The post የአዲስ አበባን ምልክቶች ማፍረስ? (VIDEO) appeared first on Wazemaradio.

[…]

” የባንክ መረጃችን እየወጣ ለዘራፊ ተጋልጠናል ” ባለሀብቶች

  • በአዲስ አበባ ፣ አዳማና ባህርዳር ከፍያለ ገንዘብ ተጠይቀናል አሉ

ዋዜማ- በአዲስ አበባ በተለያየ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በማያውቁት ስልክ እየተደወለላቸው ገንዘብ እየተጠየቁ ፤ ገንዘቡን የማይሰጡ ከሆነም ለደህንነታቸው የሚያሰጋ ማስፈራርያ እየደረሰባቸው እንደሆነ ዋዜማ ካሰባሰበችው መረጃ ተረድታለች ።

አዳማና ባህርዳር ያሉ ባለሀብቶችም በታጣቂዎች ከአንድ ጊዜ በላይ ገንዘብ መጠየቃቸውን ነግረውናል።

እየደወሉ በማስፈራርያ ገንዘብ የሚጠይቁ ግለሰቦች ፤ ባለሀብት ነው ብለው ያሰቡትን ሰው ሙሉ አድራሻ ብቻ ሳይሆን ፤ በባንክ ውስጥ የሚያንቀሳቅሱትን ገንዘብ እና የባንክ መረጃቸውን የሚያውቁ መሆኑ ደግሞ በግለሰቦች ላይ ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ መሆኑን ተረድተናል ።

ለዚህ ዘገባ ሲባል ጉዳያቸውን የተከታተልነው እና ለደህንነታቸው ስማቸው እና የኩባንያቸው ስም እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ግለሰብ ፤ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ አሏቸው ሌሎች የንግድ ስራዎች ላይም ተሰማርተዋል ።

ሆኖም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በስልካቸው እየተደወለ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየተጠየቁ ፤ ይህን ማድረግ የማይችሉ ከሆነ ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል።የሚደውሉላቸው ሰዎች ግለሰባዊ ጉዳዮቻቸውን ሳይቀር የሚያውቁበት ደረጃ ስላሰጋቸውም መጀመርያ ይኖሩበት ከነበረበት ቦታ ሁለት ግዜ የመኖርያ ሰፈር እንደቀየሩም መረዳት ችለናል።ሁኔታውን በስራ እና ኑሯቸው ላይ ስጋት እንደፈጠረባቸውም ገልጸዋል ።

ሌላው ባለሀብት እንዲሁ በአዲስ አበባ በንግድ ላይ የተሰማሩ ሲሆን ፤ በተመሳሳይ በስልክ እየተደወላላቸው መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብን እየተጠየቁ እንደሆነ ያስረዳሉ። በዚሁ ሳቢያ የእጅ ስልካቸውን ለቤተሰብ አባላቸው ሰጥተው በሌላ ስልክ እንደሚጠቀሙ ይገልጻሉ ።ሆኖም ለቤተሰብም እንፈልጋቸዋለን እየተባለ እንደሚደወል ይናገራሉ ።

ለዚህ ዘገባ ጉዳያቸውን የተመለከትናችው ግለሰቦች ከሚደውሉላቸው ሰዎች ንግግር በመነሳት ገንዘብ ካላመጣችሁ ብለው የሚያስፈራሯቸው ግለሰቦችን ከንግግራቸው በመነሳት ፖሊቲካዊ አላማ ያላቸው እንደሆነ እንደሚገምቱ ይገልጻሉ ።

ከአርባ አንድ አመታት በላይ በአዳማ ከተማ ከትንሽ ስራ ተነስተው ስመጥር ባለሀብት ለመሆን የበቁና ስሞኑን ከሀገር መውጣት የቻሉ ባለሀብት እንደነገሩን ደግሞ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ያህል በአገዳጅ ሁኔታ የተጠየቁትን ስድስት ሚሊየን ብር በሚሰጥር ከፍለው የቤተሰባቸውን ደህንነት ለጊዜው ማረጋገጥ ቢችሉም በጥር ወር በድጋሚ አስር ሚሊየን ብር ካልከፈልክ የሚል ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው ይናገራሉ።

“ጉዳዩን ለመንግስት አካላት አስውቄ ለንብረቴ ጥበቃ እንዲደረግልኝ ተወስኖ ጠባቂዎቹ ስራ በጀመሩ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ የድርጅቴ አንድ ሚኒባስ መኪና ከግቢው ውስጥ ባልታወቀ ግለሰብ ተወስዶ ተሰወረ” ይላሉ።

ስድስት ቤተሰቦቻቸውን ከሀገር አስወጥተው ራሳቸው ለአጭር እረፍት በውጪ ሀገር የሚገኙት ባለሀብት የኦሮምያም ሆነ ፌደራል ፖሊስ በዚህ መሰል ጉዳይ ተደጋጋሚ ጥቆማ ቢደርሳቸውም ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት አቅምም ፍላጎትም ይጎድላቸዋ ሲሉ ያስረዳሉ።

የባንክ ብድር መክፈል ተስኗቸው ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት ሌላ የባህርዳር ባለሀብት ድግሞ ክልሉ በጦርነት ላይ በመሆኑ የተበደሩትን በወቅቱ ሰርተው መክፈል እንደተቸገሩ ያብራራሉ።

“ባለፈው አንድ አመት ሶስት ታጣቂ ቡድኖች ከፍያለ ገንዘብ እንድሰጣቸው በማግባባት ጠይቀውኝ ነበር። መንግስት ደግሞ ለታጣቂዎች ትረዳለህ ብሎ ለሶስት ወር ያህል ድርጅታቸውን ዘግቶት ቆይቷል”

ታጣቂዎቹ አቀራረባቸው የማስፈራራት ባይሆንም የጠየቁትን ድጋፍ እምቢ ማለት ከነሱ የሚያጣላ እንደሆነባቸውም አልሸሸጉም። ባለሀብቱ ለታጣቂዎቹ ገንዘቡን ይክፈሉ አይክፈሉ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆኑም።

በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ እንዲሰጠን የጠየቅነው የፌደራል ፖሊስ በማናቸውም የወንጀል ጉዳይ በወቅቱ መረጃ ከቀረበለት እርምጃ ለመውሰድና ምርመራም ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ነግሮናል። ስዎች ከወንጀለኞች ጋር ተሰማምተውና ገንዘብ ከፍለው ከጨረሱ በኋላ የሚመጣ አቤቱታ ላይ ፖሊስ ስራውን ለመስራት ይቸገራል ብሏል።

የኦሮምያ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት ትናንት ዓርብ ዕለት ቀጠሮ ቢሰጠንም አስቸኳይ ስራ ገጥሞናል በሚል በቀጠሮው ሳይገኙ ቀርተዋል።

በንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን የባንክ መረጃን እናውቃለን በማለት አስፈራርቶ ገንዘብ መጠየቅ በተለይ በኦሮምያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በመለመዱ ንብረታቸውን ጥለው ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ እንዳሉም ዋዜማ ሰምታለች። [ዋዜማ]

The post ” የባንክ መረጃችን እየወጣ ለዘራፊ ተጋልጠናል ” ባለሀብቶች first appeared on Wazemaradio.

The post ” የባንክ መረጃችን እየወጣ ለዘራፊ ተጋልጠናል ” ባለሀብቶች appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data – 13 March 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 13 March 2024.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.