Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

የህዳሴው ግድብ ሶስተኛ ዙር ውሀ ሙሌት ተጠናቆ በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት ውሀው በግድቡ አናት ላይ ይፈሳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው

FILE

  • ሁለተኛው ተርባይንም ሀይል ለማመንጨት ዝግጁ ሆኗል

ዋዜማ ራዲዮ- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሀ ሙሌት ተጠናቆ ዛሬ ወይ ነገ በግድቡ አናት ላይ ውሀው ይፈሳል ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን ዋዜማ ራዲዮ ከግድቡ ግንባታ ከፍተኛ አመራሮች ሰምታለች።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመርያ ምዕራፍ የውሀ ሙሌቱን ላለፉት ተከታታይ ሁለት የክረምት ወቅቶች ያደረገ ሲሆን በ2012 አ.ም የክረምት ወራት 4.9 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ ይዟል።

ባለፈው ክረምት ማለትም በ2013 አ.ም 13.4 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀን በእቅዱ መሰረት መያዝ የነበረበት ቢሆንም በሀገሪቱ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተፈጠሩ ፖሊቲካዊ ቀውሶች የግንባታ እቃዎችን ወደ ስፍራው ማጓጓዝን ከባድ ስላደረጉት የተጠቀሰውን የውሀ መጠን ለመያዝ የግድቡ ቁመት መድረስ የነበረበት ከባህር ጠለል በላይ 595 ሜትር ላይ ባለመድረሱ እቅዱ አልተሳካም። ዋዜማ ራዲዮ ከታማኝ ምንጮቿ መስማት እንደቻለችውም ህዳሴ ግድብ ባለፈው አመት የክረምት ወራት 1.8 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ ነው መያዝ የቻለው።

በዚህኛው የክረምት ወቅት ግን የግድቡን ቁመት ከባህር ጠለል በላይ 600 ሜትር በማድረስ ተጨማሪ ከ14 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ በላይ በመያዝ በጥቅሉ ግድቡ ከ21 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ ውሀን የሚይዝ መሆኑንም ሰምተናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ የሀይል ማመንጫ ተርባይን ተከላ እና ሙከራ ተከናውኖ ሀይል ለማመንጨት ዝግጁ መሆኑ ተነግሯል።

ከአምስት ወራት በፊትም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጀመርያው የሀይል ማመንጫ ተርባይን ሀይል ማመንጨት መጀመሩ የሚታወስ ነው።እስካሁንም እንደሚያገኘው የውሀ መጠን የኤሌክትሪክ ሀይል እያመነጨ ነው።

ከዚህ የክረምት ወቅት ጀምሮ የሚከናወነው ሁለተኛው ምእራፍ ሶስተኛ ዙር የውሀ ሙሌት ለሶስት አመታት የሚከናወን ሲሆን የግድቡን ቁመት መሰረት በማድረግ ግድቡ በጥቅሉ 49 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ እስኪይዝ በየክረምት ወራቱ እንደሚሞላ የቀደሙ የእቅድ ሰነዶች ያሳያሉ።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ 11 አመታት አልፈውታል። [ዋዜማ ራዲዮ]

The post የህዳሴው ግድብ ሶስተኛ ዙር ውሀ ሙሌት ተጠናቆ በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት ውሀው በግድቡ አናት ላይ ይፈሳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው appeared first on Wazemaradio.

[…]

መንግሥት አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት በአደራዳሪነት የመሳተፋቸውን ሐሳብ አሁንም አልተቀበለውም

ዋዜማ ራዲዮ- የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ፣ ከሕወሃት ጋራ ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የሰላም ድርድር አስፈላጊ ነው ያለውን የመንግሥት አቋምና ፍላጎት የሚያብራራ “የሰላም ሐሳብ ይሁንታ” (ፕሮፖዛል) ማዘጋጀቱን ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 11 ቀን ዓ.ም አሳውቋል። ይህ ሰነድ ሰሞኑን ለአፍሪካ ህብረት እንደሚቀርብ የኮሚቴው አባላት በአዲስ አበባ ተቀማጭ ለሆኑ የተለያዩ ሀገራት ለዲፕሎማቶች በሰጡት ማብራሪያ አረጋግጠዋል።

አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት በአደራዳሪነት የመሳተፋቸውን ሐሳብ መንግስት አሁንም አለመቀበሉ በውይይቱ ተገልጧል። የኮሚቴው አባላት “ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ” በሕወሃት ላይ በቂ ጫና አላደረገም፣ ለጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት እያየ እንዳላየ ማለፍን መርጧል ሲሉ መተቻተውን ዋዜማ ሰምታለች።

የአፍሪካ ኅብረት በመንግስትና በሕወሃት መካከል የታሰበውን ድርድር በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ የማስጀመር እቅድ እንዳለው አስቀድሞ መዘገቡ ይታወሳል። ደመቀ መኮንን፣ ሬድዋን ሑሴን እና ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በጋራ ለዲፕሎማቶቹ እንደነገሩት፣ መንግሥት ድርድሩ ሁሉም አካላት የሚያከብሩት ዘላቂ የተኩስ አቁም የሚያቋቋም ስምምነት የሚደረስበት እንዲሆን ይፈልጋል።

የመንግስት ዋና ፍላጎት ወደ ሌላ ጦርነት እንዳይገባ ማድረግ ነው መባሉን ዋዜማ ሰምታለች። በውይይቱ የተሳተፉ ዲፕሎማት ለዋዜማ እንደገለጹት፣ መንግሥት ከህወሃት ጋር የሚደረገው ድርድርና የሰላም ስምምነት በሃገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ስራ ይካተታሉ ተብለው የሚጠበቁ ውስብስብ ፖለቲካዊና አገራዊ ጉዳዮችን ለመፍታት ያግዛል የሚል እምነት አንጸባርቋል።

በገለጻው ላይ የተገኙት ዲፕሎማቶች የተለያዩ ጥያቄዎች ማንሳታቸውን ዋዜማ ከዲፕሎማቲክ ምንጮች ተረድታለች። ከሌሎች ታጣቂ ቡድኖች በተለየም ከሸኔ ጋራ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ለቀረበ ጥያቄ በተሰጠ ማብራሪያ ታጣቂዎቹ በዋናነት የሚረዱት በሕወሃት በመሆኑ ከእርሱ የሚደርገው ድርድር ከተሳካ ሌሎቹ ታጣቂዎች ወደ ሰላም የሚመጡበት እድል እንደሚኖር መነገሩን ዲፕሎማቶቹ ጠቅሰዋል።

ዲፕሎማቶቹ፣ መንግሥት የአፍሪካ ኅብረት ዋና አደራዳሪ መሆን አለበት በሚል የያዘው አቋም ቅድመ ሁኔታ ይመስላል ብለው ጠይቀው ነበር። አደራዳሪነቱን በተመድ ወይም በሌላ አካል የመተካትን ሐሳብ አንድ የአውሮፓ ዲፕሎማት አንስተዋል።

የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴው አባላት የአፍሪካ ኅብረት ጉዳይ የመርህ እንጂ የቅድመ ሁኔታ ጉዳይ እንዳልሆነ አብራርተው፣ መንግሥታቸው በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይም ተመሳሳይ መርህ መከተሉን እንደጠቀሱ በስብሰባስ የተገኙ ምንጮች ነግረውናል።

አንድ የኮሚቴው አባል፣ በአፍሪካ ሕብረት ድርድሩን የመምራት አቅምና ፍላጎት ላይ መንግሥት እንደሚተማመን ተናግረዋል። ኅብረቱ ወይም የሚሰይማቸው መልእክተኖች አቅም እና ገለልተኝነት ይጎድላቸዋል በሚል በህወሃት በኩል ተደጋጋሚ ቅሬት መቅረቡ ይታወሳል።

የመንግሥት ተወካዮች ተመድም ሆነ አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት በአደራዳሪነት ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት አሁንም እንዳልተቀበሉት የገለጹት በተዘዋዋሪ ነው፣ ዋዜማ እንደሰማቸው። “ድርድሩን በቴክኒክና በገንዘብ ልታግዙ ትችላላችሁ” የሚል መልስ ተሰጥቷል።

በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸውን አወዛጋቢ አካባቢዎች በተመለከተ ዲፕሎማቶቹ ጠይቀዋል።

የመንግስት ተወካዮች፣ ዘላቂ ተኩስ አቁምና ስምምነት ሳይደረስ ሌሎች ጉዳዮችን መነጋገርም ሆነ መፍታት አይቻልም የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ሕወሃት ጦርነት ለመጀመር እየተዘጋጀ ነው ብለው የከሰሱት የኮሚቴው አባላት፣ ለሕወሃት መሳሪያ የሚያቀብሉት እነማን እንደሆኑ መንግስት እንደሚያውቅ ለዲፕሎማቶቹ በሰጡት ማብራሪያ ጠቅሰዋል። በውይይቱ ሕወሃት ጦርነት ሊጀምር ይችላል የሚል ግምትና ስጋት መንጸባረቁን የዋዜማ ምንጮች ጠቁመዋል።

የስልክ፣ ኤሌክትሪክ፣ ባንክ፣ ኢንተርኔትና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች ለማስጀመር የድርድሩን ውጤት ትጠብቃላችሁ ወይስ ከወዲሁ ለመልቀቅ ታሳባላችሁ የሚል ጥያቄም ቀርቦ ነበር። አገልግሎት ማስጀመር የድርድሩ አካል አይደለም፣ ሆኖም አገልግሎቶቹን ማስጀመር ራሱ ምክክርና ትብብር የሚፈልጉ ብዙ የዝግጅት ስራዎችን ይፈልጋል ሲሉ ነው መልሰዋል አንደኛው የመንግስት ተወካይ። አገልግሎች ሰጪ ተቋማት ውይይቱ እንደጀመረ ሥራቸውን ለመጀመር የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መታዘዛቸው በወቅቱ መነገሩን ዋዜማ አውቃለች።

መንግሥት ከሕወሃት ጋር እንዲደራደር በሰኔ ወር ያቋቋመውን የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ የሚመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ሲሆኑ፣ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር፣ ጌታቸው ጀምበር እና ሌ/ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ ደሞ በአባልነት ተካተውበታል። ሕወሃትም ተደራዳሪ ቡድን ማቋቋሙን ዘግየት ብሎ በሐምሌ አጋማሽ ገደማ ለውጭ ዜና ምንጮች ተናግሯል። የቡድኑን አባላት ማንነት እና ብዛት ግን ሕወሃት እስካሁን ይፋ አላደረገም። [ዋዜማ ራዲዮ]

The post መንግሥት አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት በአደራዳሪነት የመሳተፋቸውን ሐሳብ አሁንም አልተቀበለውም appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopian to Welcome Amman to its Extensive Network

Ethiopian Airlines, the largest network operator in Africa is pleased to announce that it has finalized all preparations to commence a passenger flight to Amman, Jordan as of September 19, 2022.

The thrice weekly flight will be operated as per the below schedule.

Flight Number

Frequency

Departure Airport

Departure time

Arrival Airport

Arrival Time

Sub Fleet

ET 428

Mon, Wed, Sat

ADD

22:30

AMM

02:05

737

ET 429

Tue, Thu, Sun

AMM

03:05

ADD

06:44

737

[…]

Ethiopia: Kacha to Expand Services by Joining Ethswitch

Ethswitch

Ethswitch and Kacha Digital Financial Service signed an agreement to work together. Kacha joined Ethswitch, a payment platform for commercial banks, to expand its services and deliver efficient service to its customers.

The company is expected to collaborate with banks, microfinance institutions, insurance companies, and credit savings institutions to provide digital transactions in Ethiopia.

[…]

Ethiopia Urges Int’l Pressure on Tigray Region to Accept Peace Talks

Khartoum – Mohammed Amin Yassin Ethiopian ambassador to Sudan, Yibeltal Aemero, accused on Monday many parties, he refused to name, of interfering and supporting the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) to fuel the conflict in …

Ethiopia Urges Int’l Pressure on Tigray Region to Accept Peace Talks Read More »

[…]

Some Quick Thoughts on Immediate Solution for the Current Crisis

Yonas Biru, PhD (Unedited Document, for lack of time) Three things have become clear after the current war. First, the weakness and incompetence of the Abiy Administration. His refusal to surround himself with subject matter …

Some Quick Thoughts on Immediate Solution for the Current Crisis Read More »

[…]

በምትኩ ካሳና ግብረአበሮቹ ላይ የሌብነት ክስ ተመሠረተ

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ግብራበሮቹ ላይ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ በዛሬው እለት ክስ መስርቷል፡፡ ተከሳሾች 1ኛ አቶ ምትኩ ካሳ ጉትሌ (የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩ) ፣2ኛአቶ አራጋው ለማ (የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የፋይናንስ ዳይሬክተር)፣ 3ኛ አቶ የማነ ወ/ማሪያም (የኤልሻዳይ […] […]

የትህነግ ፍቅር ያከነፈው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጀርባ ከአሸባሪው ትህነግ ጋር በመደራደር የራሱን ህግ ጥሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጀርባ ከአሸባሪው ትህነግ አመራር ጋር በቀጥታ በመደራደር የራሱን ሕግ መጣሱ ታውቋል። የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባለፈው ሳምንት ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን ሊቀመንበር ከሆነው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ዋና ጸሀፊው ይህንን ከአሸባሪው ድርጅት መሪ ጋር የመነጋገራቸው መረጃ የታወቀውም፤ […] […]

U.N. Ships Ukrainian Grain To Ethiopia

By Katharine Houreld (Reuters) – A ship carrying wheat from Ukraine to the drought-stricken Horn of Africa docked on Tuesday, the United Nations said, the first to make the journey since the Russian invasion six …

U.N. Ships Ukrainian Grain To Ethiopia Read More »

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - 29 August 2022

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 29 August 2022.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.