Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

ላንድማርክ ሆስፒታል እነበቀለ ገርባን ማረሚያ ቤት ድረስ ሄጄ ማከም አልችልም አለ

Bekele Gerba

ዋዜማ ራዲዮ- በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራሮች የረሀብ አድማ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ መታመማቸው እና ላንድማርክ በተባለ የግል ሆስፒታል ለመታከም መጠየቃቸው ይታወሳል።

በመንግስት ሆስፒታል ነው መታከም ያለባቸው በማለት ይህን ጥያቄ እና የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ይሁንታ የተቃወመው ጠቅላይ አቃቤህግ ለጠቅላይ ፍርድቤት ይግባኝ ብሎ ነበር።
ይህን ተከትሎ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎት የካቲት 16 ቀን 2013ዓም የላንድማርክ ሆስፒታል ፍቃደኝነትን እና ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልኩ የህክምና ሞያው በሚፈቅደው ደምብ መሰረት የሀኪሞች ቡድን በማደራጀት ተከሳሾች ባሉበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሄዶ ሙሉ ህክምና እንዲሰጥ ወስኖ ነበር።

ይሁን እንጂ ላንድማርክ ሆስፒታል የህክምና መሳሪያዎቼን ነቅዬ ማረሚያ ቤት ድረስ ሄጄ አላክምም በማለት ለፍርድ ቤቱ በደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል።

የተከሳሾች ጠበቆችም ደምበኞቻቸው ወደ ሆስፒታሉ ተወስደው ለመታከም እንዲፈቀድላቸው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ (አርብ) የይግባኝ አቤቱታ አስገብተዋል።[ዋዜማ ራዲዮ]

The post ላንድማርክ ሆስፒታል እነበቀለ ገርባን ማረሚያ ቤት ድረስ ሄጄ ማከም አልችልም አለ appeared first on Wazemaradio.

Source:: http://wazemaradio.com/%E1%88%8B%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8A%AD-%E1%88%86%E1%88%B5%E1%8D%92%E1%89%B3%E1%88%8D-%E1%8A%A5%E1%8A%90%E1%89%A0%E1%89%80%E1%88%88-%E1%8C%88%E1%88%AD%E1%89%A3%E1%8A%95-%E1%88%9B/