Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

ሆድ ለባሰው …

ሰሞኑን ወሬው ሁሉ ስለ ኳስ ሆኗል፡፡ ሬዲዮው፣ ቴሌቪዥኑ ፣ ጋዜጣው፣ ድረ ገጹ ፣ ማኅበራዊ መረቡ፣ ምን አለፋችሁ ሁሉም ሰው ስለ ኳስ አውርቶ ፣ ኳስን ተንፍሶ፣ ኳስን ጠጥቶ፣ ኳስን ተመግቦ ፣ ኳስን አልሞ የሚኖር ነው የሚመስለው፡፡ እንዴት ደስ ይላል ባካችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከ31 ዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ መቻሉ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ብዙዎቻችን ከዚህ በፊት በአፍሪካ ዋንጫ ሲጫወት አላየን ወይን አልሰማንም፡፡ 31 ዓመት የአንድ ጎልማሳ ዘመን ነው፡፡ ለብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች ክብር ይግባቸው እና ይህ ቁጥር 50 ወይም 100 ሆኖ የአንድ ሰው ዘመን እያልን እዳንቆጥር ታሪካችን ለውጠውታል፡፡ እኔ እንኳን በእድሜዮ ለምሥራቅ አፍሪካ ወይም ለወጣቶ ካልሆነ በቀር ስለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ዜና ሰምቼ አላውቅም፡፡ ዘንድሮ ግን ጉድ ብለን ያለፈውን ታሪካችንን ሁሉ እረስተን ቡድናችን እንዴት ይሸነፋል እስክንል የሚያበቃ ድፍረት ሰጡን፡፡
ቡድናችን ከዛምቢያ ጋር እኩል በመውጣቱ ፌሽታ አድርጎ ማን እንደ ኢትዮጵያ እያለ ሲደነፋ የነበረው ሁሉ በቡርኪና ፋሶ በመረታታችን አይናችሁን ላፈር አይነት ነገር የሚሉ ሰዎች በየመድረኩ ስሰማ ስለ ስለ ኳስም ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስም ያላቸውን አመለካከት እጅግ አናሳ እንደሆነ በቀላሉ ገመትኩ፡፡ ምን አልባት ሕዝቡ ሆድ ብሶት ይሆናል እና ኳሱ ማጭድ ሆኖበት ነው ብዮ ተስፋ አደረኩ፡፡ በድህነት፣ በችግር፣ በስደት፣ በመለያየት፣ በሃይማኖት ነጻነት፣ በፓለቲካው ወዘተ ውስጣዊ ሰላም ያጣው ችግሩን ለደቂቃም እንኳን የሚያስረሳው መድኃኒት ሲፈልግ ለነበረው እና በዚህም ሆድ ለባሰው ሕዝብ ከ31 ዓመት በኋላ በለስ የቀናው ቡድናችን ቢሸነፍ እንዴት አያስለቅሰው፡፡
በዚህ መስፈርት ካልሆነ በቀር ብዙ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ፣ ብዙ ኢንተርናሽናል ልምድ ካላቸው ቡድኖች ጋር ከ 31 ዓመት በኋላ መሳተፍ የቻለ ፣ በቂ የወዳጅነት ጨዋታ ያላገኘ ፣ አንድ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ያለው ቡድናችን ከመሳተፍ እና ጥሩ ጨዋታ ከማሳየት በላይ መጠበቅ የለብንም፡፡ በእርግጥ እግር ኳስ ለሚያውቅ ሰው ከላይ ያሉት መስፈርቶች ሁሉ ባዶ ሊሆኑ እንደሚሉ መንገር አይገባም፡፡ ብዙ ቢሊዮን ዶላር በአመት የሚያፈሱ ቡድኖች በትንንሾቹ ሲደበደቡ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ሁሉ ነገር በተደከመለት መጠን እንደሚገኝ መዘንጋትም አያስፈልግም፡፡ ቡድናችን ልጅ ነው ፤ ቡድናችን ብዙ ወጪ ያልተደረገበት ነው ፤ ቡድናችን ብዙ ፕሮፌሽናል ልምድ የሌለው ነው፡፡ ነገር ግን ቡድኑ ከተከፈለበት በላይ ባደረገው ጥረት ለአፍሪካ ዋንጫ በቅቶ ታሪካችንን መለወጡ ብቻ ለእኛ በቂ ነው፡፡ ከዛ አልፎ ደግሞ ደስ የሚል ውጤት ስንሰማ ደስታችን እጥፍ ድርብ መሆኑ ግልት ነው ለምን ተሸነፍን ማለት ግን … ብዙም አይዋጥም … በእርግጥ ቅድም እንዳልኩት እኔንም ያሳሰበኝ ከላይ የዘረዘርኳቸው መጠነ ሰፊ የሆኑ ችግሮችንን የመርሻ ጊዜያችን ማጠሩ ግን ያበሳጫል … ያሳዝናል … ያስለቅሳል፡፡
አሁን ቢሆን ከሚቀጥለው ጨዋታ ተአምር ልንጠብቅ አይገባም፡፡ ፈታ ብለን … በ31 ዓመት አንዴ ያገኘነውን አጋጣሚ በደስታ እናሳልፈው፡፡ ቡድናችንን እንደግፈው … በደቡብ አፍሪካ ያሉ ወገኖቻችን ኢትዮጵያዊያን ለኳስ ያለንን ፍቅር እንደመሰከሩልን በዓለም ዙሪያ ያለን ኢትዮጵያዊያንን በጋና እንደግፍ … በጋራ አይዟችሁ እንበላቸው … እኛም አጋጣሚውን እንደሰትበት ብናሸንፍ እና ወደቀጣዩ ዙር ብናልፍ የደስታ ጊዜያችን ይራዘማል፡፡ ባይሆንልን እና ከውድድሩ ብንወጣ ደግሞ የአለም ዋንጫን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.