Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የህልውና አደጋ አንዣቦበታል

Fincha Sugar Factory

ዋዜማ – ከጥቂት ዓመታት በፊት ሀገሪቱ በቢሊየን የሚቆጠር ብድር አፈላልጋ በሀገሪቱ አስር የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባትና ያሉትን ለማዘመን ስራ ጀምራ ነበር። የብዙዎቹ ግንባታ ተካሂዷል። የኦሞ ኩራዝ አካባቢ አራት ፋብሪካዎች 35 ቢሊየን ብር ወጥቶባቸው ተገንብተዋል። መንግስት እነዚህ ፋብሪካዎች አዋጭ አይደሉም በሚል ወደ ግል ይዞታ እንዲዛወሩ ያለፉትን ሶስት አመታት ዝግጅት ሲያደርግ ነበር።

ፋብሪካዎቹ አሁንም ጉዳያቸው በእንጥልጥል እንዳለ ነው። ከተመሰረተ 45 አመታትን ያስቆጠረው ነባሩ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ በመስከረም ወር ስራ እንደሚጀምር ቢጠበቅም አልተሳካለትም። በተጨማሪም በመንግስትና ኦነግ ሸኔ መካከል በሚፈጠረው ተደጋጋሚ ግጭት መደበኛ ተግባሩን ማከናወን አልቻለም።ዋዜማ ጉዳዩን ከድርጅቱ ሰራተኞች ጠይቃ ለመረዳት ሞክራለች።

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፣ በወቅቱ የሚያስፈልገው ጥገና ሊደረግለት ባለመቻሉ እና ፋብሪካው በዋናነት ጥቅም ላይ የሚያውላቸው፣ ፋይቭራዘር እና ሸራውድ የተሰኙት ማሽኖች ከአገልግሎት ውጪ በመሆናቸው ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ስራ ማቆሙን የፋብሪካው ሰራተኞች ለዋዜማ ተናግረዋል።

ፋብሪካው ከዚኽ ቀደም ባለው ልምድ መሠረት፣ ክረምት ላይ ጥገና ተደርጎለት መስከረም ወር ላይ ወደ ሥራ ይገባ እንደነበር የገለፁት ምንጮች፣ አኹን ላይ ግን አስፈላጊ የሚባሉት የማምረቻ ቁሳቁሶች ጭምር ባለመሟላታቸው ስራ ማቆሙን ገልፀዋል።

ፋብሪካው ስራ ያቆመው በቀደመው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ እንደሆነ የጠቀሱት የፋብሪካው ሰራተኞች፣ አስፈላጊዎቹ ማሽኖች ተሟልተው፣ ፋብሪካው ወደ ስራ እንዲገባ በተደጋጋሚ ጥያቄያቸውን ለፋብሪካው አስተዳደር ቢያቀርቡም፣ ማሽኖቹ ከውጭ እንደሚገቡ እና እስከዛሬ የዘገየቱም በውጭ ምንዛሬ ዕጥረት እንደሆነ ሲነገራቸው ከመሰንበቱ ውጪ በተግባር የተደረገ ነገር እንደሌለም ጠቁመዋል።

በፋብሪካው ከ2 ሺ 700 በላይ ቋሚ እና ከ 8 ሺ በላይ ጊዜያዊ ሰራተኞች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን፣ ፋብሪካው አስፈላጊው ጥገና ተደርጎለት በቅርቡ ስራ የማይጀምር ከሆነ ደሞዛችን ሊቆም ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳሉ ለዋዜማ ተናግረዋል።

በአካባቢው የሚኖሩ ከ70 ሺ በላይ ሰዎችም ህልውናቸው ከዚሁ ፋብሪካ ጋር የተገናኝ እንደመሆኑ፣ ወደ ስራ የማይገባ ከሆነ የእነዚህ ነዋሪዎች ሕይወትም አደጋ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ዋዜማ ለመረዳት ችላለች።

ፋብሪካው ከጊዜ ወደ ጊዜ የማምረት አቅሙ በከፍተኛ መጠን እያሽቆለቆለ መሄዱን የጠቀሱት ምንጮች፣ ከዚህ ቀደም በዓመት ከ1.2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስኳር ያመርት የነበረ ሲሆን፣ ስራ እስኪያቆም ድረስ በዓመት ከ200 ሺ ኩንታል ያነሰ የስኳር ምርት ብቻ ሲያመርት እንደነበርም አስረድተዋል፡፡ ለዚህም በዋናነት እንደ ምክንያት የተጠቀሰው ለምርት የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎች አለመሟላታቸው እና በስራ ላይ ያሉትም ዕድሳት ከተደረገላቸው ብዙ ጊዜ በመቆጠሩ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ፋብሪካው ከ35 ሺ ሄክታር በላይ የሸንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት ቢኖረውም፣ በአካባቢው ባለው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር የተነሳ ለስኳር ምርት ግብአት የሚሆነውን የሸንኮራ አገዳ እንደሚፈለገው ለፋብሪካው ማቅረብ አለመቻሉም ለዚህ መሰሉ የምርት ማሽቆልቆል አንዱ ምክንያት መሆኑም ተጠቅሷል።

የሸንኮራ አገዳውን ለማምጣት፣ ፋብሪካው ካለበት ቦታ ከ35 እስከ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ያህል መጓዝ እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ሰራተኞቹ፣ በዚያ አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን መካከል ከፍተኛ ውጊያ በመኖሩ የተነሳ፣ ያንን ማድረግ አለመቻሉን ተናግረዋል።

ይኽም በአካባቢው የሸንኮራ አገዳ ለፋብሪካው በማቅረብ ለሚተዳደሩ አርሶ አደሮች የነበረውን የስራ ዕድል እንዲዘጋ በማድረጉ የተነሳ፣ አርሶ አደሮቹ ችግር ላይ መውደቃቸውንም ጭምረው ነግረውናል፡፡ በተጨማሪም በፋብሪካው ውስጥ ለምርት ስራ የሚውሉ ማሽነሪዎች፣ ተሸከርካሪዎች እንዲኹም የተለያዩ ቁሳቁሶች ላይ በሁለቱ ኃይሎች መካከል በየጊዜው በሚደረጉ ግጭቶች ከፍተኛ ውድመት እንደሚደርስም ተናግረዋል፡፡

በፋብሪካው ውስጥ ሌላው እንደ ችግር የሚነሳው የደሞዝ ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የፋብሪካው ሰራተኞች፣ ደሞዝ ወቅቱን ጠብቆ ሊከፍል አለመቻሉ ሌላኛው ተግዳሮት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዚኹ ምክንያት ከሦስት ዓመት ወዲኽ ከ1 ሺ በላይ የሚሆኑ የፋብሪካው ቋሚ ሰራተኞች ስራ መልቀቃቸውንና አኹን ላይ 2ሺ 700 የሚሆኑ ሰራተኞች ብቻ ከመኖራቸው ባለፈ፣ ወደ 10 ሺ ይጠጉ ከነበሩት የቀን ሰራተኞች መካከል 8ሺ ያህሉ ብቻ አሁን በስራ ላይ እንዳሉ እኒኹ የዋዜማ ምንጮች ጠቅሰዋል።

ሰራተኞቹ አክለው እንደተናገሩት፣ ስለ ደሞዝ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች አስተዳደር ክፍሉን በምንጠይቅበት ወቅት፣ “ፋብሪካው ይቀጥል፣ አይቀጥል ባልታወቀበት ሁኔታ ስለ ደሞዝ ለማውራት ያስቸግራል” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸውም ነግረውናል፡፡

የፋብሪካውን አመራሮች በስልክ ለማነጋገር ጥረት ብናደርግም መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። [ዋዜማ]

The post ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የህልውና አደጋ አንዣቦበታል first appeared on Wazemaradio.

The post ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የህልውና አደጋ አንዣቦበታል appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - 6 November 2023

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 6 November 2023.

[…]

አራት የመንግስታዊ ሚዲያ ጋዜጠኞች ኮበለሉ

Solomon Alemu, Fana Broadcast editor in Chief ( Photo-SM)

ዋዜማ- ለመንግስት ቅርብ በሆኑና በገዥው ፓርቲ በሚተዳደሩ የመገናኛ ብዙሀን ሲሰሩ የነበሩ አራት ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው መኮብለላቸውን ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጠናል።

ባለፉት ስድስት ወራት ቢያንስ አስራ ሶስት የግል መገናኛ ብዙሀንና የብይነመረብ ጋዜጠኞች ከሀገር መሰዳዳቸውን ዋዜማ ያሰባሰበችው መረጃ ያመለክታል። የግል መገናኛ ብዙሀን ጋዜጠኞች ስደት ባለፉት ሶስት አመታት በርከት ብሎ የታየ ቢሆንም ያለፉት ሶስት አስርት ዓመታት የየዕለት ክስተት ነበረ።

የመንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ኩብለላ ላለፉት ሀያ አመታት ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም በዚህ ሰሞን አራት የፋና ብሮድካስትና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ጋዜጠኞች ከሀገር ወጥተው አልተመለሱም።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ሀያ ለሚጠጉ አመታት በተለያዩ ደረጃዎች ያገለገለው ሰለሞን አለሙ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአሜሪካ የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረቡን ሰምተናል። ሰለሞን አለሙ ከጥቂት ወራት በፊት ፋና ለስራ አሜሪካ ልኮት ነበረ ።በመሀል ተመልሶ የነበረ ቢሆንም እንደገና ፈቃድ ጠይቆ በቀረው የቪዛ ጊዜ ወደ አሜሪካ በመጓዝ በዚያው የጥገኝነት ጥያቄን አቅርቧል። ሰለሞን አለሙ ፋናን ከሪፖርተርነት አንስቶ እስከ ዘርፍ ዳይሬክተርነት ያገለገለ አርታኢ የነበረ እና ; ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የቴሌቪዥን ስርጭትን ከጀመረ አንስቶ የቴሌቪዥን ዜና ዘርፍን በሀላፊነት የመራ ነው።

የፋና ዲጂታል ሚድያን በሀላፊነት ሲመራ የነበረው መቆያ ሀይለማርያምም በእንግሊዝ ሀገር ጥገኝነት መጠየቁ ተሰምቷል።መቆያ ሀይለማርያምም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከ15 አመታት በላይ የሰራ እና ከታችኛው እርከን ጀምሮ እስከ ዲጂታል ዘርፍ ዳይሬክተርነት ያገለገለ ነው።

መቆያ ሀይለማርያም ከዚህ ቀደም በእንግሊዝ ሀገር የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን የተከታተለ ሲሆን ከዚያ መልስም ለአመታት ተቋሙን ሲያገለግል ነበር። ሆኖም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ እንግሊዝ ተመልሶ ጥገኝነት መጠየቁ ተሰምቷል።

ተስፋዬ ከበደ በፋና ቴሌቪዥን ውስጥ በአርታኢነት ሲያገለግል የነበረ ጋዜጠኛም እንዲሁ በቅርቡ ለስልጠና በሚል ተቋሙ በሚያውቀው መልኩ ወደ አሜሪካ ሄዶ እንዳልተመለሰ መረዳት ችለናል።

በቅርቡ ፕሬዝዳንት ሰሀለወርቅ ዘውዴ የተገኙበትን በአሜሪካ የተደረገ ከግብርና ጋር የተያያዘ ጉባኤን ልትዘግብ አብራ የተጓዘችው የኢቢሲ ጋዜጠኛ መቅደስ ጥላሁን በአሜሪካ ከአየር ማረፊያ ተሰውራ ካብልላለች።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የሁለቱ ጋዜጠኞች የቅርብ ወዳጆች እንደነገሩን ጋዜጠኞቹን ወደ ስደት እንዲያመሩ ያስገደዳቸው በሰራ ቦታቸው ያለ አድሏዊ አሰራርና የተካረረ የብሄር ፖለቲካ ሲሆን በመጠኑም ቢሆን ወደ ውጪ ሀገራት ለመጓዘ ያገኙትን ዕድል ላለማሳለፍ በማሰብ እንደሆነ ነግረውናል። የተሰደዱትን ጋዜጠኞች አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። [ዋዜማ]

The post አራት የመንግስታዊ ሚዲያ ጋዜጠኞች ኮበለሉ first appeared on Wazemaradio.

The post አራት የመንግስታዊ ሚዲያ ጋዜጠኞች ኮበለሉ appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopia: ESL Generates Over Birr 13 Billion in Three Months

ESL Logo 2

Ethiopian Shipping and Logistics (ESL) has reported a revenue exceeding Birr 13 billion during the first quarter of the current fiscal year.

[…]

Ethiopia: Dire Dawa on the Path to Becoming an Industrial and Commercial Center

Dire Dawa

Dire Dawa, is on track to become a major industrial and commercial center, according to the Trade, Industry, and Investment Bureau of the city.

[…]

የመምህራን ባንክ ሊቋቋም ነው

Prof Birhanu Nega- FILE

ዋዜማ- የመምህራንን ኢኮኖሚያዊ ችግር ለማቃለል ይረዳል የተባለ “የመምህራን ማህበር ባንክ” ለመመስረት ዕቅድ መኖሩን ሰሞኑንን ለ3ኛ ጊዜ በጂግጂጋ በተካሄደው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አመታዊ ጉባዔ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መናገራቸው ዋዜማ ሰምታለች፡፡

ሚንስትሩ የማህበሩን ባንክ መመስረት በተመለከተ በስብሰባው ተገኝተው ይፋ ባደረጉበት ንግግር መንግስት በሚያደርገው እገዛ ባንኩን እውን ለማድረግ ጥናቶችና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውንና በቀጠይ በጉዳዩ ላይ ከማህበሩ ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ወይይት ይደረግበታል መባሉን ዋዜማ ተረድታለች፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ከ 700ሽህ በላይ አባላት ያሉት የመምህራን ማህበሩ በየጊዜው የሚያነሱትን የደመወዝ ማስተካካያና የኑሮ ሁኔታ መሻሻል ለማካካስ ይረዳል በሚል እሳቤ በሁሉም ክልሎች ለመምሀራን የቤት መሰሪያ ቦታ አቅርቦት እየተመቻቸ ቢሆንም መምህራኑ በሚከፈላቸው ደመወዝ ቤት መስራት ቀርቶ የዕለት ፍላጎታቸውን ማሳካት እንደተሳናቸው እየተጠቀሰ በተደጋጋሚ ጥያቄ እየቀረበላቸው መሆኑን ሚንስትሩ በመድረኩ አንስተዋል፡፡

ይመሰረታል የተባለው ባንክ ይህንን የመምህራኑን ችግር ለመፍታትና በቀረበላቸው የቤት መሰሪያ ቦታ ላይ ቤት እንዲገነቡ ብደር የሚቀርብና የሚደግፍ ይሆናል፡፡

መንግስት ባንኩ አንዲመሰረት እገዛ ቢያደርግም በዋነኝነት ግን በአገሪቱ ለሚገኙ መምሀራን የአከስዮን ሽያጭ በማቅረብ በባለቤትነት እንዲይዙት ይደረጋል ተብሏል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚመሰረተው ባንክ በተጨማሪ በአንዳንድ ክልሎች የሚገኙ የክልል መምህራን ማህበራት የክልል መምህራን ቁጠባ ማህበራትን ለማቋቋም ትልም እንዳላቸው ተሰምቷል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በጂግጂጋ ከተማ ለሶስት ቀናት በተካሄደው ስብሰባ የኢትዮጵያ መምህራን እና ማህበሩን ወደ ቀደመ የሙያ ክብሩ ለመመለስ ብርቱ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡ [ዋዜማ]

The post የመምህራን ባንክ ሊቋቋም ነው first appeared on Wazemaradio.

The post የመምህራን ባንክ ሊቋቋም ነው appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopia Garners USD 356 Million from Coffee, Tea, Spices Export

coffee-plant

Ethiopia has earned over USD 356 million from the export of 70,480 tons coffee, tea, and spice in the first quarter of the current fiscal year, according to the Ethiopian Coffee and Tea Authority (ECTA).

[…]

Ethiopia: Dashen Bank Posts Strong Performance in 2022/23 Fiscal Year

dashen-bank-logo

Dashen Bank, a leading private bank in Ethiopia, has announced impressive financial results for the last fiscal year. The bank reported a total income of Birr 18 billion and a profit before tax of Birr 5 billion. The bank’s profit before tax for the current year exceeded the previous year’s by 31.9%

[…]

Ethiopia: Bank Deposit Accounts Increase to 129.52 Million

NBE Logo

The number of bank deposit accounts in Ethiopia has risen from 98.59 million in June 2022 to 129.52 million in June 2023, the National Bank of Ethiopia revealed.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.