Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

የህዳሴ ግድብ ድርድር መቋጫው ላይ ደርሷል?

ዋዜማ- የሕዳሴ ግድብ ደርድርን በተመለከተ በአራት ወራት ጊዜ ከስምምነት ለመድረስ የግብፅና የኢትዮጵያ መሪዎች ቃል መግባታቸውን በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል። በሰባት ዓመታት ስምምነት መድረስ የተሳናቸው ግብፅ ፣ኢትዮጵያና ሱዳን ላለፈው አንድ ዓመት ምንም ይፋዊ ድርድር ሳይካሄድ እንዴት በአራት ወራት ከስምምነት እንደሚደርሱ እርግጠኛ መሆን ቻሉ? ዋዜማ በግድቡና በድርድሩ ዙሪያ ሲካሄዱ የነበሩና እየተካሄዱ ያሉ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎችን ተመልክተናል

የግድቡ ግንባታ ያለበት ደረጃ

የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በዚህ አመት መጨረሻ ወር ማለትም ነሀሴ ወይንም እስከ ቀጣዩ አመት የመጀመርያ ወር መስከረም ድረስ አራተኛ ዙር ሙሌቱን እንደሚያከናውን መንግስት መግለጹ ይታወሳል። ሆኖም መንግስት አራተኛ ዙር ሙሌቱ ይከናወናል ከሚል መረጃ ውጭ የግድቡ የደርሰበትን ቁመና እና በአራተኛው ዙር ምን ያክል ውሀ ይይዛል በሚለው ላይ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

ዋዜማ ከምንጮቿ ከሰበሰበችው መረጃ እንደተረዳችው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአራተኛው ዙር ውሀ ሙሌቱ የሚይዘው የውሀ መጠን ከ10.8 እስከ 11 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ይገመታል። ይህም ግድቡ በአጠቃላይ የሚይዘውን ውሀ ከ32 እስከ 33 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ ያደርገዋል። የሕዳሴው ግድብ ላለፉት ሶስት ዙር ሙሌቶች በጥቅሉ 22 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀን ይዞ ቆይቷል።

በ2012 አ.ም ክረምት ወራት ላይ ለመጀመርያ ጊዜ 4.9 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ የያዘ ሲሆን ; በቀጣዩ የ2013 አ.ም የክረምት ወቅት ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች ሳቢያ የግድቡን ግንባታ እንደተፈለገው ማከናወን ባለመቻሉ የተያዘው ውሀ 1.8 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ብቻ ነበር። ባለፈው አመት ግን ግድቡ በግንባታ አንጻር መልካም የነበረ በመሆኑ ተጨማሪ 14 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሀ በመያዝ አጠቃላይ የውሀ መጠኑን ወደ 22 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ተጠግቷል።

የሕዳሴው ግድብ የጥቅጥቅ ኮንክሪት ግንባታ የመሀልኛው ክፍል ቁመቱ 120 ሜትር ወይንም 620 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ደርሷል።ሆኖም ዳር እና ዳር ያለው የግድቡ ቁመት ከመሀልኛው አንጻር የተወሰነ ሜትር ዝቅታ ስላለው ይህን ለማስተካከል ነው አራተኛውን ዙር የውሀ ሙሌት ወቅት ገፋ ማድረግ የተፈለገው።

በ2014 አ.ም የክረምት ወቅት ሶስተኛው ዙር ሙሌት ሲከናወን የግድቡ ዋነኛ ክፍል ቁመት 100 ሜትር ወይንም ከባህር ወለል በላይ 600 ሜትር ላይ ነበር። ላለፈው አንድ አመትም ተጨማሪ የ20 ሜትር ግንባታን በማከናወን የመሀልኛውን የግድቡን ክፍል ቁመት 120 ሜትር ወይንም ከባህር ወለል በላይ 620 ሜትር ላይ ማድረስ ተችሏል።

ድርድርና ዲፕሎማሲ

የግድቡ ዲፕሎማሲ ጉዳይም ከሰሞኑ አነጋጋሪ ነገሮች ተከስተውበታል። ሱዳን ኢትዮጵያ የግድቡን ድርድር አስመልክቶ ልትሄድበት ባሰበችው መንገድ ላይ ኩርፊያ ውስጥ መግባቷን ዋዜማ መረዳት ችላለች። የኩርፊያው ምንጭም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሳምንታት በፊት የሱዳንን ፖለቲካዊ ችግር ለመፍታት በግብጽ ከተደረገው ጉባኤ ጎን ለጎን ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር በግድቡ ዙርያ የሚደረግ ድርድርን በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ መስማማታቸው ተገልጿል።

ሱዳን አሁን ላይ በጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሀን እና በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ሀይሎች ጦርነት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እያለች የህዳሴው ድርድር በአራት ወራት እንዲያልቅ ሁለቱ ሀገሮች መስማማታቸው ሀገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ለእንዲህ አይነቱ ድርድር ዝግጁ ባለመሆኗ በሁለቱ ሀገራት የመገለል ስራ እንደተሰራባት ቆጥራዋለች።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሱዳን ሰዎች ባገኟቸው አጋጣሚዎች ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት እየገለጹ እንደሆነ ዋዜማ ከዲፕሎማሲ ምንጮቿ ሰምታለች።

ኢትዮጵያ እና ግብጽ የሕዳሴው ግድብ ድርድርን በአራት ወራት እንዴት ሊያገባድዱ እንዳቀዱ በይፋ ያስታወቁት ዝርዝር የለም።

ከመሪዎቹ መግለጫ አንድ ቀን በኋላ ዋዜማ ላቀረበችው ጥያቄ የኢትዮጵያ የተራዳሪዎች ቡድን አባላት በግብፅና በኢትዮጵያ መሪዎች መካከል ድርድሩን በአራት ወራት ለመቋጨት ስለተደረሰው ስምምነት መረጃ እንዳልነበራቸው ነግረውናል። ባለፈው ሳምንት በድጋሚ ላቀረብነው ጥያቄ ደግሞ ምንም አይነት ዝርዝር መግለጫ መስጠት እንደማይችሉ ገልፀውልናል።

በሩሲያ ሶቺ ከአራት ዓመት በፊት የግብፅና የኢትዮጵያ መሪዎች በድንገት በደረሱት ስምምነት ድርድሩ ወደ አሜሪካ ሄዶ ከሶስት ዙር ያልተሳካ ሙከራ በኋላ መቋረጡ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ተይዞ ቆይቷል። እስካሁን የተገኘ ውጤት የለም።

የአፍሪቃ ህብረት ድርድርን ለማሳካት ሙከራ ያደረጉት የወቅቱ ሊቀመንበር የነበሩት የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ትሸከዲ ተጨባጭ ውጤት ላይ ሳይደረስ የሊቀመንበርነት ጊዜያቸውን ጨርሰዋል። እስከ አሁንም ከአፍሪቃ ህብረት በኩል በድርድሩ የተሳካ ነገር የለም።

አሁን ለብዙዎች ጥያቄ የሆነው የግብፅና የኢትዮጵያ መሪዎች በአራት ወራት ከስምምነት ለመድረስ የሚያደፋፍር ምን አማራጭ አገኙ የሚለው ነው።

የዔምሬትስ ስውር ዲፕሎማሲ

ያለፉት ሁለት ዓመታትን የተባበሩት አረብ ዔምሬትስ የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ ለማደራደር ሙከራ ስታደርግ እንደነበረና በሚያዚያ ወር 2013 ዓም ከኢትዮጵያ የተወከለ የተደራዳሪ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ በምስጢር ወደ ዱባይ ማቅናቱን ዋዜማ መረጃ አላት።

ይህን ተከትሎ ዔምሬትስ ባደራጀችው መድረክ 28 ዙር ድርድሮችና ምክክሮች ተደርገዋል።

በተባበሩት አረብ ዔምሬትስ የተደረጉት ድርድሮች ይዘት በሶስቱም ሀገራት በከፍተኛ ሚስጥር እንዲያዝ የተደረገ ቢሆንም ግን ሂደቱ ብዙም ስኬት የተመዘገበበት አይደለም። እንደውም በኢትዮጵያ በኩል ድርድሩን በኮሞሮስ ሊቀመንበርነት እየተመራ ወዳለው የአፍሪካ ህብረት የመመለስ ፍላጎት አለ።

ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ግንባታን እያከናወነች እና ውሀም እየያዘች በመሆኑ ግብጽ እና ሱዳን እንደበፊቱ የግድቡ ቁመት እና የውሀ መጠን ላይ መደራደር አዋጭ ባለመሆኑ ፣ ኢትዮጵያ ውሀ ስትሞላ አስገዳጅ ስምምነቶችን እንድትፈርም እና ግድቡ በረጅም ጊዜ ስራውን ሲያከናውን በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ድርቅ ቢያጋጥም ውሀ እንድትለቅ የሚያስችል አስገዳጅ ስምምነት ማስር ዋና ግባቸው ሆኗል።

ኢትዮጵያ ደግሞ ይህ ጥቅሟን የሚነካ እና አስተማማኝ ባልሆነ የውሀ ፍሰት ላይ አስገዳጅ ስምምነትን መፈረም ተገቢ አይደለም የሚል አቋም ይዛለች።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልሲሲ በአራት ወራት እናሳካዋለን የሚሉት ስምምነት መሰረቱ የአፍሪቃ ህብረት ድርድር ይሁን የተባበሩት ዓረብ ዔምሬትስ አልያም አዲስ ስምምነት ይፋ አላደረጉም። [ዋዜማ]

To reach Wazema editors please write via wazemaradio@gmail.com

The post የህዳሴ ግድብ ድርድር መቋጫው ላይ ደርሷል? first appeared on Wazemaradio.

The post የህዳሴ ግድብ ድርድር መቋጫው ላይ ደርሷል? appeared first on Wazemaradio.

[…]

Egypt and Ethiopia: Abiy Ahmed Announced to Delay the Fourth Filling

Beth Daley/ The Conversion Egypt and Ethiopia have waged a diplomatic war of words over Ethiopia’s massive new dam – the Grand Ethiopian Renaissance Dam – on the Blue Nile, which started filling up in July 2020. The political row has threatened to get out of hand on occasion but now the two countries have …

Egypt and Ethiopia: Abiy Ahmed Announced to Delay the Fourth Filling Read More »

[…]

የዮሐንስ ቧያለው ያለ መከሰስ መብት እንዲነሳና በአገር ክህደት እንዲከሰሱ ተጠየቀ 

ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የአማራ ምክርቤት ስብሰባ ላይ የሰላ ሒስ የሰነዘሩት የምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው ያለመከሰስ መብት ተነስቶ በአገር ክህደትና በመሳሰሉ ወንጀሎች እንዲቀጡ ጥያቄ መቅረብ ጀምሯል። አቶ ዮሐንስ ከስብሰባው በኋላ ሲናገሩ ተሰምተዋል በተባለው የድምጽ ቅጂ በአገር ክህደት ሊያስጠይቃቸው ይገባል የሚል ሃሳብ እየተሰጠ ነው። አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከጥቂት ቀናት በፊት በተጠናቀቀው የአማራ ክልል ምክርቤት ስብሰባ ላይ […] […]

The Gutting of the CSA of Ethiopia and the Christening of Oromummaa

Yonas Biru, PhD Yesterday, I published a piece titled “Unprecedented Economic Data Fabrication Threatens the Survival of Ethiopia.” One of the issues I flagged was the dismissal of professionals at the Central Statistical Agency (CSA) who refused to publish fabricated data. One of the disagreements between the Prime Minister and CSA officials was the so-called …

The Gutting of the CSA of Ethiopia and the Christening of Oromummaa Read More »

[…]

Ethiopia: Benishangul Gumuz Regional State’s Tourism Sector Shows Growth while SNNPR’s Tourism Sector Misses Targets

SSNPR 101

In the 2022/2023 fiscal year, the Benishangul Gumuz Regional State received a total of 40,600 tourists, resulting in an income of Birr 103 million 199 thousand. Out of the total visitors, 40,000 were domestic tourists and 600 were foreign tourists. This represents an 18 percent increase in the performance of the tourism sector compared to the previous year. The improved performance can be attributed to factors such as relative peace in all three zones of the region, the development of tourist destinations, and their accessibility to visitors.

[…]

Unprecedented Economic Data Fabrication Threatens the Survival of Ethiopia

Yonas Biru, PhD As one who has spent his professional life at the World Bank working on global economic comparison, I am keenly aware that nations manipulate their data for various reasons. Such activities are often rampant during election years. I am also aware that some nations have two datasets – one is what they …

Unprecedented Economic Data Fabrication Threatens the Survival of Ethiopia Read More »

[…]

የማዳበሪያ ዕጥረት አለ በሚባልበት የአማራ ክልል 400 ኩንታል ማዳበሪያ ተያዘ

አቶ ዮሐንስ ቧያለው በክልላቸው ምክር ቤት ፊት ስለ ማዳበሪያ አቅርቦት ዕጥረት አምርረው በተናገሩና የክልሉ ገብርና ቢሮ ሥራ መሥራት ያልቻለ ደመወዝ በነጻ የሚበላ ነው ብለው ባፌዙበት ማግስት በአማራ ክልል 400 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ በሕገወጥ መልኩ ሲሰራጭ መያዙን ኢቢሲ ዘግቧል። በአማራ ክልል ማዳበሪያን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ሲወራ የሰነበተው ሤራ ምን እንደሆነ ማሳያ ነው። የዜናው ሙሉ መረጃ ከዚህ […] […]

The Horn of Africa States Grains and Food Production

By Dr. Suleiman Walhad July 23rd, 2023 And the wrong message that they will be dying of hunger and there will be less bread on the tables in many parts of the African continent, will continue. A large part of the grains received in Africa were mostly coming from Ukraine, some 25,000 MT in the …

The Horn of Africa States Grains and Food Production Read More »

The post The Horn of Africa States Grains and Food Production first appeared on ZeHabesha | Ethiopia News, Video, Analysis and Opinion.

[…]

Time is on Fano’s Side !

The Amhara Fano Resistance and Counter-Offensive emerged out of the primordial instinct for survival ! The genocidal Abiy kleptocracy committed horrific acts of genocide and ethnic cleansing against the AMHARAs, who exhibited extraordinary patience and forbearance in the face of various levels of atrocity against them over 45 years some of the worst genocidal massacres …

Time is on Fano’s Side ! Read More »

The post Time is on Fano’s Side ! first appeared on ZeHabesha | Ethiopia News, Video, Analysis and Opinion.

[…]

Rastafarians with Selassie’s reported death in 1975

The following was written by Charles A. Price of Temple University in the United States for The Conversation, an independent and nonprofit source of news, analysis and commentary from academic experts. The week of July 23, 2023, thousands of Rastafarians, known for their dreadlocks and for treating marijuana as a sacrament, will gather in Jamaica …

Rastafarians with Selassie’s reported death in 1975 Read More »

The post Rastafarians with Selassie’s reported death in 1975 first appeared on ZeHabesha | Ethiopia News, Video, Analysis and Opinion.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.