Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

Study Agreement Signed with US Firm to Explore Ethiopia's Natural Gas Potential

deal-with-us-firm-mar-2022

The Ethiopian government signed an agreement with the US firm Netherland, Sewell & Associates, Inc. (NSAI) to explore Ethiopia’s natural gas deposits and its economic potential.

[…]

ከበርካታ ዓመታት ኪሳራና ብልሹ አሰራር አገግሞ የነበረው ልማት ባንክ አዲስ ፈተና ገጥሞታል

Development Bank of Ethiopia- FILE

  • በስድስት ወራት ውስጥ ያገኘው ትርፍ የእቅዱን 3.4 በመቶ ሲሆን ተጨማሪ 100 ሚሊየን ብርም የተበላሸ ብድር ውስጥ ገብቷል

ዋዜማ ራዲዮ- ከበርካታ ዓመታት ብልሹ አሰራርና የኪሳራ ጉዞ ተላቆ ባለፈው አመት ከፍተኛ የተባለውን 3.4 ቢሊየን ብር ትርፍ አስመዝግቦ የነበረው ልማት ባንክ የዚህ በጀት አመት የመጀመርያ ስድስት ወራት አፈጻሙ ከፍተኛ ማሽቆልቆል እንደገጠመው ዋዜማ ራዲዮ ከምንጮቿ መረዳት ችላለች።

የልማት ባንኩ በ2014 አ.ም በጀት አመት የመጀመርያ ስድስት ወራት ከታክስ በፊት 1.3 ቢሊየን ብርን ለማትረፍ አቅዶ ተንቀሳቅሷል። ሆኖም በተጠቀሰው ጊዜ ባንኩ ማትረፍ የቻለው 47 ሚሊየን ብር ብቻ ነው። በመቶኛ ሲቀመጥም የእቅዱን 3.4 በመቶ ብቻ ነው ማትረፍ የቻለው። ይህም በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ የሚኖረው አፈጻጸም ስኬታማ ስለመሆኑ ከወዲሁ አጠራጣሪ አድርጎታል።

የመረጃ ምንጮቻችን እንደነገሩን ከሆነ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጀት አመቱን ሲጀመር በመበላሸት ላይ ያለ ወይንም መመለሱ አጠራጣሪ የሆነ ብድር መጠኑ 20.8 ቢሊየን ብር የነበረ ሲሆን በበጀት አመቱ ስድስት ወራት ውስጥም የተበላሸ ብድር መጠኑን ወደ 12 ቢሊየን ብር ዝቅ ለማድረግ ዕቅድ ነበረው።

ሆኖም የተበላሸ ወይንም መመለሱ አጠራጣሪ የሆነው የባንኩ ብድር መጠን ከመቀነስ ይልቅ ጨምሮ ታይቷል። የልማት ባንኩ የተበላሸ ብድር መጠንም አሁን ላይ 20.9 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን ከአጠቃላይ ዕቅዱ የ100 ሚሊየን ብር ጭማሪ አሳይቷል።

ሆኖም የባንኩን እንቅስቃሴ በቅርበት የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንደነገሩን ሀገሪቱ ከነበረችበት ሁኔታ አንጻር 47 ሚሊየን ብር ትርፍ መገኘቱም በክፉ የሚነሳ አይደለም። ካለፈው አመት ሀምሌ ወር እስከዚህ አመት ታህሳስ ወር ድረስ የሰሜኑ ጦርነት ከትግራይ ወጥቶ ሰሜን ሸዋ መድረሱ የልማት ባንኩን ብድር የማይመልሱ ተበዳሪዎችን ቀጥር በመጨመሩ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል።

ሆኖም የትግራይ እና የአማራ ክልል ተቀንሶ ሲታይ የልማት ባንኩ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ አፈጻጸም እንዳለው መረዳት ችለናል። እንዲሁም በ2014 አ.ም ጅማሬ ላይ መንግስት ሀገሪቱ ላይ የኢኮኖሚ አሻጥር እየተሰራ ነው በሚል ባንኮች ብድር እንዲያቆሙ ማዘዙ የባንኩ ተበዳሪዎች ተጨማሪ ካፒታል አግኝተው ምርት አምርተው በመሸጥ ብድር እንዳይከፍሉ ማድረጉም ሌላው ለባንኩ አፈጻጸም መወረድ በምክንያትነት ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ልማት በቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት ዮሀንስ አያሌው (ፒ ኤች ዴ) መመራት ከጀመረ አንስቶ ከፍተኛ መሻሻሎችን አሳይቶ ቆይቷል። በተለይ ባለፈው አመት ባንኩ የነበሩበትን የተለያዩ ውዝፍ ስራዎች በመስራት እንዲሁም የአንዳንድ ከፍተኛ ተበዳሪ ኩባንያዎችን ችግር አቃሎ ወደ ብድር ከፋይነት በማስገባት 3.4 ቢሊየን ብር ማትረፍ ችሏል። ይህም ብቻ ሳይሆን ባንኩ አበድሮት ከነበረው ከ40 ቢሊየን ብር በላይ የተበላሸ የነበረውን 51 በመቶ የብድር ምጣኔ ወደ 20 በመቶ ለማስገባት ተችሎ ነበር። [ዋዜማ ራዲዮ]

The post ከበርካታ ዓመታት ኪሳራና ብልሹ አሰራር አገግሞ የነበረው ልማት ባንክ አዲስ ፈተና ገጥሞታል appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Trade Data - March 22, 2022

ECX

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX), of items traded on March 22, 2022.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Trade Data - March 21, 2022

ECX

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX), of items traded on March 21, 2022.

Unwashed Export Coffee

Symbol

Average Price

Bale

UBL

3,777

Jimma

UJM

3,183

Local Coffee

Symbol

Average Price

Local Unwashed

LU

3,124

Local Washed

LW

4,151

Wollega Sesame

Symbol

Average Price

Whitish Wollega

WWSS

7,908

Green Mung Bean

Symbol

Average Price

Shoa

GMBS

8,450

Soya Beans

Symbol

Average Price

Gojam

SBGJ

4,554

Speckled Bean

Symbol

Average Price

Black Pea Bean

BPB

3,900

White Gray Speckled Bean

WGS

4,000

  • For coffee, price is in (Birr/Feresula), 1Feresula = 17Kg.
  • For all other commodities, price is in (Birr/Quintals), 1Quintal = 100Kg.

Source: ECX data sent to 2merkato.com

[…]

Safaricom, Ethiopian Electric Utility Sign Pole Lease Agreement

safaricom-eeu-deal

Safaricom Ethiopia has signed a three-year pole lease agreement with Ethiopian Electric Utility (EEU) to enable aerial fiber installation through the existing poles infrastructure in Addis Ababa and across the country. Aerial cabling is easier to repair and deploy across the country, Safaricom Ethiopia noted.

[…]

Ethiopian Electric Utility: Over 46 Thousand Households Gain Access to Electricity in a Month

eeu-performance-meeting-feb-2022

Ethiopian Electric Utility (EEU) announced it has provided access to electricity for 46,603 households during the 30-day period since February 8, 2022. The figure has risen by 34 percent compared to the same period last year, with additional 15,768 households benefiting, EEU related.

[…]

Ethiopia Shelves Ethio Telecom's Partial Privatization Process

ministry-of-finance

Ethiopia’s Ministry of Finance announced that the Ethiopian government has “chosen to postpone the [partial] privatization process” of Ethio Telecom.

[…]

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ የ15 ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ምደባ አካሄደ

CBE Headquarters New building -FILE

  • የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ቁጥር እንዲቀንስ ተደርጓል
  • የባንኩ ትልልቅ ደንበኞች የሚስተናገዱበት አዲስ ክፍል ተቋቁሟል

ዋዜማ ራዲዮ- ከ2010 አ.ም ጀምሮ በተለያዩ የማሻሻያ ትግበራዎች ውስጥ ያለፈው ግዙፉ መንግስታዊ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 15 ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ምደባ አካሂዷል። ይህም አራት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደ ምደባ ነው።

ምደባው የተካሄደው ባንኩ ባስጠናው አዲሰ መዋቅር አማካኝነት ሲሆን ጥናቱንም ያካሄደውም መሰረቱን አሜሪካ ያደረገው መካንዚ(Mckinsey) የተባለ የስራ አመራር አማካሪ ድርጅት ሰለመሆኑ ዋዜማ ራድዮ ከዚህ ቀደም መዘገቧ ይታወሳል።

በመዋቅሩ የመጀመርያ ትግበራም የ15 የምክትል ፕሬዝዳንቶች ምደባ ባለፈው ሳምንት ተካሂዷል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 24 ምክትል ፕሬዝዳንቶች የነበሩት ሲሆን በተደረገ የክለሳና ማሻሻያ ስራ የምክትል ፕሬዝዳንቶች ቁጥር ወደ 18 ዝቅ ተደርጎ ቆይቷል ፣ በአዲሱ ምደባ ደግሞ ባንኩ በ15 ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተዋቅሯል።

በዚህም አቶ ኀይለኢየሱስ በቀለ የብድር አስተዳደር ዘርፍን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ ተመድበዋል። አቶ ኀይለኢየሱስ የኮንስትራክሽን እና ቢዝነስ ባንክ በንግድ ባንክ ከመጠቅለሉ በፊት ባንኩን በስራ አስኪያጅነት የመሩ ፣ ከዚያም የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በምክትል ፕሬዝዳንትነትና እና በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉ እና በተፈጠሩ አለመግባባቶች ከሀላፊነታቸው የተነሱ መሆናቸው ይታወሳል።

ንግድ ባንኩ ትልቅ ለውጥ አመጣበታለሁ ብሎ በምክትል ፕሬዝዳንት እንዲመራ ያቋቋመውን የዎልሴል ባንኪንክ ክፍልን ደግሞ አቶ ሙሉነህ ለማ ይመሩታል።አቶ ሙሉነህ ባንኩን እስካሁንም በምክትል ፕሬዝዳንትነት እያገለገሉ ያሉ ናቸው። አሁን የሚመሩት የዎልሴል ባንኪንግ አገልግሎትም ከግል አካውንት ውጪ የባንኩ ትልልቅ ደንበኞች ተለይተው አገልግሎት የሚሰጥበት ስርአት ነው። በዚህ የምከትል ፕሬዝዳንትነት መደብ ስር ያሉ ሰራተኞችም ዋነኛ ስራቸው ደንበኞች የሚፈልጉትን አገልግሎት ተከታትሎ ማስፈጸም እንደሆነም ዋዜማ ሬዲዮ ከምንጮቿ ሰምታለች።

በሌላ በኩል ደግሞ ወይዘሮ ማክዳ ዑመር የኦዲት ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል። የፋሲሊቲ ማኔጅመት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ወደ ሰው ሀይል ምክትል ፕሬዝዳንትነት የተሸጋሸጉ ሲሆን የሰው ሀይል ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ጡሪ ከቦታቸው ተነስተዋል። እመቤት መለሰ የስትራቴጂክ ዕቅድና ሽግግር ዘርፍ እንዲሁም ሙሉነህ አቦየ ሪስክ ማኔጅመኘት ኤንድ ኮምፕሊያንስ ምክትል ፕረዝዳንቶች ሆነው ከተመደቡት መካከል ናቸው።

በሌላ በኩል የባንኩ የህግ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ሱሪ ፈቀታ እና የቢዝነስ ዴቨሎፕመንች ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ይስሀቅ መንገሻም ተነስተዋል። በቀጣይም የዳይሬክተሮች ምደባ እንደሚከናወን ሰምተናል።

ግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህንን መዋቅር ለተወዳዳሪነትና ለበለጠ ውጤታማነት እንደሚፈልገው ተገልጿል።

በ2012 አ.ም አጋማሽ አካባቢ አቶ አቢ ሳኖ የባንኩን ፕሬዝዳንትነት ከአቶ ባጫ ጊና ከመረከባቸው በፊት ንግድ ባንኩ ከፍተኛ የትርፍ ማሽቆልቆል ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል። የ2012 አ.ም የባንኩ ትርፍ 14 ቢሊየን ብር ሲሆን ይህም በባንኩ ታሪክ ብዙም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከቀደመው አመት አንጻር የ1.4 ቢሊየን ብር ቅናሽ አሳይቶ ነው።

በዚያው 2012 አ.ም ባንኩ ያሰባሰበው ተቀማጭ ከ2011 አ.ም ከ30 ቢሊየን ብር በላይ ቀንሶ ወደ 54 ቢሊየን ብር ወርዷል።

ከአቶ ባጫ መነሳት በኋላ በነበረው የአቶ አቤ ሳኖ ፕሬዝዳንትነት ወቅት የአሰራር ማሻሻያዎችን በማድረግ ባንኩ ከገባበት አደጋ መውጣት ችሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2013 አ.ም ትርፍ ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ሆኗል። እንዲሁም ባንኩ በዚያው አመት ከ140 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ በማሰባሰብ አጠቃላይ ተቀማጩን 735 ቢሊየን ብር አድርሷል። ያለፈው አመት ትርፉም በባንኩ ታሪክ ያልታየም ነበር። የባንኩ ሀብትም አንድ ትሪሊየን ብርን ተሻግሯል።

ከበርካታ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ያልተመለሰ ብድር ችግር ውስጥ ገብቶ የቆየው ንግድ ባንኩ መንግስት ያቋቋመው የልማት ድርጅቶች ዕዳ አስተዳደር ኮርፖሬሽን የልማት ድርጅቶችን ዕዳ መውረሱን ተከትሎ ያልተመለ ብድር ምጣኔው ተስተካክሏል። አሁን ባለው መረጃም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበላሸ ብድር ምጣኔ 4.6 በመቶ ሲሆን ይህም ለንግድ ባንኮች ከተቀመጠው የ5 በመቶ የተበላሸ ብድር ምጣኔ አንጻር መልካም የሚባል አፈጻጸም ነው። [ዋዜማ ራዲዮ]

The post የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ የ15 ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ምደባ አካሄደ appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Trade Data - March 18, 2022

ECX

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX), of items traded on March 18, 2022.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Trade Data - March 17, 2022

ECX

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX), of items traded on March 17, 2022.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.