Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

Eritrea appoints Semere Russom as Ambassador to Ethiopia

Asmara, Eritrea – President Isaias Afwerki has appointed the current Minister of Education, Mr. Semere Russom as Ambassador to Ethiopia, according to Information Minister Yemane G.Meskel. Semere Russom, age 75, began his professional life as a teacher. He traveled to the United States as a student at the University of Oklahoma, but terminated his studies […] […]

Discourse on the concept of Medemer (መደመር)

Medemer is a rallying cry popularized by the Ethiopian PM Dr. Abiy to rally his people to be included in the big tent he is pitching. It is a brilliant method of building a mass movement from scratch. It is positive, catchy and plays to the human need to be included. No one wants to […] […]

አብይ ምናችን ነው?

ለመነሻ፤ ሀ፦ “አሁንም…ኢትዮጵያ አንድ አብዮት ያስፈልጋታል። ልጆቿን የማይበላ አብዮት! ራሱን የማይውጥ አብዮት! ሳይንቲፊክ ሪቮሉሽን። በሳይንስና ቴክኒዮሎጂ የታገዘ አብዮት። ለውጥን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ የለም። ለውጡ ሆዳቸውን ከሚያጎልባቸው ጥቂቶች በቀር።” ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ በዴርቶጋዳ መፅሀፍ ላይ በ2001 ዓ/ም እንደፃፈው ወይም በራዕዩ እንዳስቀመጠው። እነሆ በሃያዎቹ መጀመሪያ ዕድሜው ላይ ይገኝ የነበረው ወጣቱ ባለራዕይ ደራሲ እንደታየው ሳይንሳዊው አብዮት፤ ልጆቹን የማይበላው አብዮት፤ […] […]

የሽብር ወንጀልና ተያያዥ ከፍተኛ ወንጀሎችን በመክሰስና በማሰፈረድ የሚታወቁት አቃቤ ሕግ ብርሀኑ ወንድማገኝ ተሰናበቱ

IMG_1680

ዋዜማ ራዲዮ- የፌደራሉ ዋና ዓቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ለዓመታት በርካቶችን ባልተጨበጠ የሽብር ወንጀልና ተያያዥ ከፍተኛ ወንጀሎችን በመክሰስና በማሰፈረድ የሚታወቁትን ዓቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝን ከኃላፊነት በማሰናበት በቦታቸው አቶ ፍቃዱ ፀጋን መሾሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዋና ዓቃቤ ህጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ አቶ ብርሃኑ ሐምሌ 12፣ 2010 ዓ.ም የመስሪያ ቤታቸውን የለውጥ ሂደት (ሪፎርም) በተመለከተ የተለያዩ ርምጃዎችን ለስራተኞቹ ያስተዋወቁ ሲሆን በአቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ ሲመራ የነበረውን ጭምሮ የበርካታ ዳይሬከቶሬት ኃላፊዎችን በማንሳት በአዲስ እንደተኩ የውስጥ ምንጮች ለዋዜማ አረጋግጠዋል፡፡
አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ ለዓመታት የሽብርና የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን የዚሁ የፌደራሉ መንግሰት ዋና ዐቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ቁልፍ ሰዎች አንዱ እነደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡

በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቴ አመራሮችንና አባላቶቻቸውን እንዲሁም የመብት አቀንቃኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪዎችንና የተለያዩ ግለሰቦችን የመንግሰት አቃቤ በመሆን በተለያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በሽብርና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች ክስ በመመስራትና በማሰፈረድ ይታወቃሉ፡፡

እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ጉዳይ በበጎ የማይንሳው አቶ ብርሃኑ ወንድምአገኝ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር የሚገኙ ተከሳሾችን የፍርድ ሁደት በማጓተትና በእስር የሚገኙ ታራሚዎች የመብት ጥሰት እዲፈጸምባቸው ተደጋጋሚ ምክንያት ይሆኑ እንደነበርም ወቀሳ ሲሰማባቸው ይሰማል፡፡
ዋና ዓቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ በጻፉት የሹመት ደብዳቤ አቶ ፍቃዱ ጸጋ የተባሉ ነባር የህግ ባለሙያ አቶ ብርሃኑ ወንድምአገኝን እንዲተኩ ማድረጋቸውንና አቶ ተመስገን ላጲሶን በምክትል ዳይሬከተር መሾማቸውን የዋዜማ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ሌሎች በርካታ ሀላፊዎችም በአዳዲስ የተተኩ ሲሆን ለሹም ሽር ምክንያት የሆነው የቀደሙት ሀላፊዎች የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የነበሩ በመሆናቸው ጭምር እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ስር የሚቀጠሩ ዓቃብያነ ህጎች ከዚህ በኋላ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባልነት ነጻ መሆን እንዳለባቸው የሚያስገድድ ድንጋጌ የያዘ መመሪያ መውጣቱ ታውቋል፡፡

The post የሽብር ወንጀልና ተያያዥ ከፍተኛ ወንጀሎችን በመክሰስና በማሰፈረድ የሚታወቁት አቃቤ ሕግ ብርሀኑ ወንድማገኝ ተሰናበቱ appeared first on Wazemaradio.

[…]

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካበደረው 33 ቢሊየን ብር አርባ በመቶው ተበላሽቷል ፣ ባክኗል

DBE President Bahre Esayas

Former DBE President Bahre Esayas

ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካበደረገው ብድር በአጠቃላይ የተበላሸው ብድር ምጣኔ 40 በመቶ ደረሰ ።

ልማት ባንኩ አሁን ላይ የሰጠው ብድር ወይንም (outstanding loan) ከ33 ቢሊዮን ብር የሚያልፍ ሲሆን ፤ ከዚህ ውስጥ የተበላሸው ብድር ማለትም (non performing loan) 14 ቢሊዮን ብር መጠጋቱን የባንኩ ምንጮቻችን ነግረውናል ። ይህም ባንኩ የተጋረጠበትን ትልቅ ፈተናና ሀገሪቱ ያለችበትን ኢኮኖሚያዊ ዉጥንቅጥ እንዳባባሰው የዘርፉ ሙያተኞች ያስረዳሉ።

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ህግ መሰረት የልማት ባንክ የተበላሸ ብድር ምጣኔ ካበደረው ገንዘብ ከ15 በመቶ መብለጥ የለበትም ።

ልማት ባንክ የሚያበድረው ገንዘብ በቀጥታ ከቆጣቢዎች ጋር የተገናኘ ሳይሆን መንግስት በተለያዩ መንገዶች አግኝቶ እንዲያበድር የሚሰጠው ገንዘብ ነው ። ልማት ባንኩ ከተቀመጠለት ገደብ ከእጥፍም በላይ ሆኖ የተበላሸ የብድር ምጣኔው የባንኩን ህልውና አደጋ ውስጥ የጣለበት ደረጃ ላይ ደርሷል ።

የጨርቃጨርቅ ዘርፉና ቱርኮች
ባንኩ 14 ቢሊዮን ብር የደረሰ ብድሩ እንዲበላሽ ትልቁን ሚና የተጫወቱት ያለ ምንም የባለሀብቶች ማጣራት ስራ በተለይም ለጨርቃ ጨርቅና ለሰፋፊ እርሻዎች የሰጠው ብድር መሆኑ የልማት ባንኩ ምንጮቻችን ነግረውናል ።

በጨርቃ ጨርቁ ዘርፍ በተለይም የቱርክ ባለሀብቶች በልማት ስም ያለ ጀርባ ታሪክ ጥናት የተሰጣቸው ብድር ባንኩ አሁን ለደረሰበት የአፈጻጸም ወድቀት ምክንያት መሆኑ ይነሳል ። ከነዚህ መካከል ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በተለይም በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብዙ ተብሎለት የነበረው የቱርኩ አይካ አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ተጠቃሽ ነው ።
ይህ ፋብሪካ ለሀገሪቱ የአምራች ኢንዱስትሪ ሽግግር ብዙ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ሲጠበቅ አሁን ላይ ብቻውን ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የተበደረው ገንዘብን ሳይከፍል የመመለሻ ጊዜው አልፎበታል ። ከጨርቃ ጨርቅ ኩባንያዎችም ለልማት ባንኩ ያልተመለሰ ብደር ምጣኔ ከፍ ማለት ትልቁን አስተዋጽኦ ያበረከተው ይሄው አይካ አዲስ ነው ።
የባንኩ ሰራተኞች አስደንጋጭ ያሉት ክስተት- ይህ ኩባንያ በዚህ የአፈጻጸም ዝቅተኝነት ውስጥ እያለ ተጨማሪ ብድር ሊፈቀድለት እንደሆነ መሰማቱ ነበር ።
በአዳማ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካውን ከፍቶ የነበረው ሌላኛው የቱርክ ኩባንያ ኤልሲ አዲስም ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ተበድሮ ከሀገር መሰወሩ የሚታወስ ነው ። ይህ ኩባንያ ጥሎት የሄደው ፋብሪካን ለጨረታ በማውጣት ልማት ባንኩ ብድሩን ሊያስመልስ ቢጥርም ኤልሲ አዲስ የተበደረው ገንዘብና ጥሎት የኮበለለው ፋብሪካ ያላቸው የገበያ ዋጋ በፍጹም የሚጣጣም ሆኖ አልተገኘም ።ኢ ቱር እና ኤንጅል የተባሉ ኩባንያዎችም በጥቅሉ ከልማት ባንኩ የተበደሩትን ገንዘብ መመለስ አቅቷቸው የመመለሻ ጊዜያቸው አልፏል ።

ኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪን እቀላቀልባቸዋለሁ ያለችው የጨርቃጨርቅ ዘርፍም የልማት ባንኳ የተበላሸ ብድር ዋነኛ ምንጭ ሆነዋል ።
ኩባንያዎቹ ገና ለገና ከውጭ ሀገራት ስለመጡ ማንነታቸው ሳይጣራ የተሰጣቸው ብድር አንዱ ለዚህ ምክንያት ሲሆን በሌላ በኩል የፋብሪካዎቹ ባለቤቶች የሚያስገቡት ማሽን ብዙ የሰራ እና በብድር የወሰዱትን ገንዘብ የማይመጥን ሆኖ በተደጋጋሚ ተገኝቷል ።
ለምሳሌ አይካ አዲስ ያረጀ ማሽንን በውድ ዋጋ አስገብቶ ከዚህ ቀደም መገኘቱ ይታወሳል ።

ስፋፊ እርሻና ውንብድና

በሰፋፊ እርሻ ላይ ተሰማርተው ለልማት ባንኩ ብድርን ያልመለሱ ባለሀብቶች ለዚህ የተበላሸ ብድር ወይንም ለnon performing loan ያላቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል ።በዚህ ረገድ በጉልህ ስማቸው የሚነሳው በጋምቤላ ክልል የበደሩት ባለሀብቶች መሆናቸው ይታወቃል ።
በዚህ ክልል የነበረው የብድር አሰጣጥ ከፍተኛ ችግር የነበረበት መሆኑ ሲነሳ ቆይቷል ፤ ብድር አሰጣጡ ማንነት ላይ የተመሰረተ ፤ ብድር የሚሰጠው በዝናብ ላይ ለተመሰረተ እርሻ መሆኑ ፤ በሌላ በኩል አንድ መሬት ላይ ሁለት ካርታየተሰጣቸው ሁለት ባለሀብቶች ለአንድ መሬት ለሁለት ባለሀብቶች ብድር የተሰጠበት ሁኔታ እንዳለ ባንኩ ደርሶበታል ።
በጋምቤላ ክልል 45 ሺህ ሄክታር ወይንም የአዲስ አበባ ከተማን ስፋት የሚቀራረብ መሬት ለተለያዩ ባለሀብቶች ተደራርቦ ካርታ መሰጠቱ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በጥናት መለየቱ ይታወሳል ።
ከዚህና ሌሎች ችግሮች ጋር ተያይዞ ዘርፉ ብዙም መንቀሳቀስ ሳይችል ቀርቷል ።
ልማት ባንኩ ከጥቂት ወራት በፊት ባወጣው መረጃ መሰረት ለሰፋፊ እርሻዎች ከሰጠው ብድር 5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ብድር ውስጥ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ብድሩ መበላሸቱን ገልጾ ነበር ።ከዚህ ጋር ተያይዞ ለዚህ ዘርፍ ብድር መስጠት እስከማቆም የደረሰ እርምጃም ተወስዶ ነበር ።
በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ መፍትሄዎች ይወሰዳሉ ቢባልም የባንኩን የተበላሸ ብድር ምጣኔ መቀነስ አልተቻለም ። ከወራት በፊት ባንኩ ራሱ የተበላሸ ብድር ምጣኔዬ ካበደርኩት 25 በመቶ ነው ብሎ የነበረ ሲሆን ፤ በወራት ልዩነት ውስጥ ምጣኔው 40 በመቶ መድረሱ ተሰምቷል ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እዚህ ችግር ውስጥ መውደቁ ለተደጋጋሚ ጊዜ የባንኩ አመራረ እንዲቀያየር አስገድዶታል ።
እስከ 2009 አ.ም የመጀመርያ ወራት ድረስ ባንኩን በፕሬዚዳነትነት ያገለገሉት አቶ አሳያስ ባህረ ለባንኩ ውድቀት ተጠያቂ ናቸው በሚል እንዲሱ ተደርጎ በምትካቸው በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ የነበሩት ጌታሁን ናና ፕሬዚዳንት መሆናቸው የሚታወስ ነው ።
አቶ ጌታሁን ባላቸው አቋም የባንኩን አፈጻጸም ያስተካክሉታል ቢባልም በደረሰባቸው ግምገማ ከጡረታቸው በፊት ራሳቸው መልቀቂያ አስገብተው ምክትል የነበሩት አቶ ሃይለኢየሱስ በቀለ አሁን ላይ ፕሬዚዳንት ሆነዋል ።
ከዚህም ሲያልፍ በልማት ባንኩ ውስጥ የተሰሩ ስህተቶች የወንጀል ተጠያቂነት ያመጣሉ ተብሎ አቶ ኢሳያስ ባህረና የቀድሞው የብድር አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ታደሰ ሀጢያ ላይ በፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ተጀምሮ እንደነበር ተሰምቷል ።

ችግሩ ከልማት ባንክ ያልፋል
ይህ ባንክ የትርፍ ገንዘብ የሚያመጣበት ሁኔታ ከባንኮች የተለመደ ስራም በተለያ መልኩ መሆኑ አስገራሚ ሆኗል ። ለወትሮው ባንክ ትርፍ ማግኘት ያለበት ካበደረው ከሚያገኘው ወለድ ቢሆንም ልማት ባንኩ ግን በካዝናው ባለው ገንዘብ የግምጃ ቤት ሰነድን ከብሄራዊ ባንክ በመግዛት ከሚገኝ ወለድ ነው ትርፍ የሚያገኘው ።

ይህ ባንክ የሚያበድረውን ገንዘብ የሚያገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የግል ባንኮች ብድር ሲሰጡ ከሰጡት ብድር 27 በመቶውን ከማእከላዊ ባንኩ ቦንድ እንዲገዙ በማድረግ ነው ፤ ይህም በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የልማት ባንኩ ብደር የህዝብ ገንዘብ ተደርጎ ይቆጠራል።

ብሄራዊ ባንክ በዚህ መልኩ ከግል ባንኮች በቦንድ የሰበሰበው ገንዘብ ከ60 ቢሊዮን ብር ማለፉን ተናግሯል ።
ይህ ገንዘብ ልማት ባንክ እንዲያበድረው እየተሰጠው ልማት ባንኩም እየከሰረ ነው ። የኪሳራው ሰንሰለትም ብዙዎችን ነው የሚጎዳው ።
የዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር የፋይናንስ አካሄድ የሚፈትነው የልማት ባንክ ጉዳይ ይመስላል ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾሙ ሰሞን በሸራተን ሆቴል ከባለሀብቶች ጋር በነበራቸው ቆይታ የልማት ባንካችንን የብድር አሰጣጥ ሁኔታ እናየዋለን ጠብቁን ማለታቸው የሚታወስ ነው ። [ዋዜማ ራዲዮ]

The post የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካበደረው 33 ቢሊየን ብር አርባ በመቶው ተበላሽቷል ፣ ባክኗል appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopian Wins SKYTRAX Best Airline in Africa Award for 2nd Time

Ethiopian Airlines, the largest Aviation Group in Africa and SKYTRAX certified Four Star Global Airline, is pleased to announce that it has won SKYTRAX World Airline Award for the Best Airline in Africa for second successive year. Skytrax is the most respected global air transport rating organization that conducts the world’s largest annual airline passenger […] […]

ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!

አፍቃሪ ህወሓት የሚዲያ ተቋማት የማኅበራዊ ድረገጽ ተዋናዮቹን ጨምሮ “ቀለበት ውስጥ ገብተናል” በማለት የተጀመረውን ለውጥና ከኤርትራ ጋር የተያዘውን አስደማሚ የሰላም ሂደት ሲቃወሙ ሰንበተዋል። አሁንም ምክንያት በመለጣጠፍ እየተቃወሙ ነው። ድርጅታቸው ህወሓት የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ አራት ኪሎ ላይ ከወሰነ በኋላ ትግራይ ገብቶ ውሳኔውን የማያውቀው እስኪመስል ድረስ እየሸራረፈ ሲቃወም ሰንብቷል። በመጨረሻ ባወጣው መግለጫ […] […]

ኢትዮ ቴሌኮም ሀላፊዎቹን አባረረ

Outgoing CEO Andualem Admassie PhD

Outgoing CEO Andualem Admassie PhD

  • የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ በመሰለል መረጃው ለሶስተኛ ወገን ይተላለፍ ነበር

ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮ-ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴን ጨምሮ የተለያዩ የድርጅቱ ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው መነሳታቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮ-ቴሌኮም ምክትል ስራ አስፈፃሚ ወሮ ፍሬሕይወት ታምሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።
የግዥ፣ የሰው ሀይልና የኦፐሬሽን ሀላፊዎችም ተነስተዋል።
ሀላፊዎቹ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ በተፃፈ ደብዳቤ እንዲሰናበቱ መደረጉንም ለመረዳት ችለናል።
ዶ/ር አድማሴ በሀላፊነት በቆዩበት ወቅት ድርጅቱን ህገ ወጥ ለሆነ ተግባር ክፍት በማድረግና የአንድ አካባቢ ሰዎች የድርጅቱን አገልግሎት ለወንጀል እንዲጠቀሙበት አድርገዋል በሚል ሲወነጀሉ ቆይተዋል።
በድርጅቱ ላይ ምዝበራ ሲፈፀም ማስቆም አለመቻላቸው፣ የደህንነት መስሪያቤቱን እንደ ሽፋን በመጠቀም ግለሰቦች ከድርጅቱ የደንበኞችን ምስጢር እንዲያወጡ መንገድ ማመቻቸታቸው በድክመት ይነሳባቸዋል።
የኦፐሬሽን ሀላፊ የነበሩት አቶ ኢሳይያስ ዳኘው ከሀላፊነታቸው የተነሱት ቀደም ባሉት ቀናት ሲሆን ከሕወሐት ጋር በመመሳጠር የድርጅቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በቁጥጥር ስር አውለው እንደነበር የድርጅቱ ባልደረቦች ይናገራሉ።
አቶ ኢሳያስ የሜቴክ ሀላፊ የነበሩት ክንፈ ዳኘው ወንድም ናቸው።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ በኢትዮቴሌኮም ትብብር የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮና የሌሎች ባለስልጣናትን የስልክ ግንኙነቶች በመጥለፍ መረጃውን ለሶስተኛ ወገን የማቀበል ስራ ሲሰራ እንደነበረም በድርጅቱ የቴክኒክ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ለዋዜማ ተናግረዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ማናቸውንም ስራዎቹን ያከናውን የነበረው በኢትዮ ቴሌኮም ወጪ እንደነበርና ተቋሙን ለከፍተኛ ምዝበራ አጋልጦት መቆየቱን የድርጅቱ ባልደረቦች ለዋዜማ ያስረዳሉ።

በየዘፉ የነበሩና በደህንነት መስሪያ ቤቱ ጭምር ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች ባለፉት ሳምንታት ከስራቸው እንዲሰናበቱ መደረጉ ይታወቃል። ” በብሄር ማንነታቸን ብቻ ከስራ እንድንባረር ተደርገናል” ያሉ የትግራይ ብሄር አባላት የሆኑ ሰራተኞች ቅሬታቸውን ወደ ህግ ለመውሰድ እየተዘጋጁ ነበር። ድርጅቱ ግን ብሄርን መሰረት ያደረገ እርምጃ አልተወሰደም ሲል እየተከራከረ ነው።

የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተፈራ ደርበውም ድርጅቱን በተገቢው መምራት ባለመቻላቸው በቅርቡ ከሀላፊነት ለማንሳት ዝግጅት እየተደረገ እንደነበርም ስምተናል።

The post ኢትዮ ቴሌኮም ሀላፊዎቹን አባረረ appeared first on Wazemaradio.

[…]

Ethiopian Airlines makes historic flight to Eritrea

Ethiopian Airlines said its “bird of peace” flew to Eritrea, after the end of the “state of war”. “I am in cloud nine,” flight captain Yosef Hailu told the BBC. Relatives and friends are expected to be reunited for the first time since a 1998-2000 border war between the two nations shut air and road […] […]

አቶ ኦባንግ ለምን በይፋ አምባሳደራችን አይሆንም

አሁን ኢትዮጵያ ልትጓዝበት እየተጠረገ ያለው መንገድ ከቀደሙት ሁሉ የተለየ ይመስላል። አዲሱ መንገድ ጥላቻን በመስበር የኢትዮጵያን ህዝብ ያለ ልዩነት በፍቅር ተጋምዶ እንዲጓዝበት ታስቦ የሚዘጋጅ ነው። ይህ የሆነበት ዋና ምክንያት የሩቁን ትተን ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የተኬደበት የጥላቻ፣ የዘረኝነት፣ የቂም፣ የመለያየት፣ የጎጠኝነት ድምሩ አጠቃላይ አገራዊ አደጋ በማስከተሉ ነው። ይህ እውነት ሊካድ በማይችል መልኩ የታየ በመሆኑ አዲሱን ጥርጊያ […] […]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.