Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

ችግርና መፍትሔ

መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2012

ብዙ ሰዎች እኔ ስለማኅበረሰባዊ ችግሮች ስጽፍ መፍትሔ አታቀርብም እያሉ ይወቅሱኛል፤ ችግራቸው ይገባኛል፤ እነርሱ ግን የኔ ችግር የገባቸው አይመስለኝም፤ አንደኛ እኔ ሥራ አስፈጻሚ አይደለሁም፤ እኔ በግለሰብ ደረጃ የአገሬንና የማኅበረሰቡን ችግር መገንዘብና ማስገንዘብ የምፈልግ የሀሳብ ሰው ነኝ፤ ከዚህ ውጭ ብወጣ አድማጭ ካለመኖሩ ሌላ ጠብ ይሆናል፤ በጃንሆይ ጊዜ አንድ ሀሳብ አቅርቤ በጀማ የተለየውን መርሀቤቴን አውራጃ እንዲሆን አስደርጌአለሁ፤ ሌሎችም ጥቃቅን ነገሮች አሉ፤ ግን ጮኬ ጮኬ ያልሆነልኝም ብዙ አሉ፤ ለምሳሌ ከእጅ ወደአፍ የሚያመርተው ገበሬ ግብር መክፈል የለበትም፤ አንዱ የችጋር ምክንያት ይህ ነው፤ እሰካሁን ጆሮ አላገኘም!
መፍትሔ ካላመጣህ ስለችገር አትናገር ወይም አትጻፍ የሚሉ ካሉ አስቸጋሪ ነው፤ እኔ ችግሩን ሳየው እንዳየሁት አቅርቤው የሚነካው እንደነካው ይመልሳል፤ ያልገባው እንዳልገባው ቢጠይቅ መልካም ነው፤ ሌሎች ሀሳቡን ይዘው ይበልጥ እያፍታቱ ወደላቀ ደረጃ ያደርሱታል ብዬ አምናለሁ፤ ወድቆ ከቀረም ዋጋ የለውም ማለት ነው፤ የአንድ ሰው ሀሳብ ነው!

Source:: https://mesfinwoldemariam.wordpress.com/2020/04/01/%E1%89%BD%E1%8C%8D%E1%88%AD%E1%8A%93-%E1%88%98%E1%8D%8D%E1%89%B5%E1%88%94/