Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

በአዲስ አበባ የኮቪድ መከላከያዎችን ተግባራዊ ያላደረጉ 167 ሺ 4መቶ ያህል ስዎች በፖሊስ ተይዘዋል

ዋዜማ ሬዲዮ- የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለቆጣጠር የወጣው መመርያ ቁጥር 30/2013 ከመስከረም 25 2013 ዓም ጀምሮ እየተተገበረ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በርካታ አንቀፆችን በያዘው በዚህ መመርያ የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭት መከላከያ የሆኑትን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጨንብል (ማስክ) ሳያደርጉ መቀንሳቀስ እና አካላዊ ርቀትን አለመጠበቅ አግባብ ባለው የወንጀል ህግ እንደሚያስቀጡ ተደንግገዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በአዲስ አበባ ከተማ ከመጋቢት 17 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2013 ዓም ባለው ጊዜ ብቻ 167 ሺህ 396 ግለሰቦች መመርያውን ጥሰው መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለዋዜማ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን የተወሰደው እርምጃ የማስተማሪያ እና የማስጠንቀቂያ ብቻ ነው ፡፡

“ይሄን ሁሉ ሰው በየጊዜው እንሰር ብንል በቂ የማሰሪያ ስፍራ ካለመኖሩ በተጨማሪ ያን ሁሉ ሰው በአንድ ቦታ ማድረግ ጭራሽ ለበሽታው መስፋፋት ምክኒያት መሆን ነው፡፡ ስለዚህ ያለው አማራጭ ማስተማሪያ የሆኑ ቅጣቶችን መቅጣት ነው፡፡፡” ብለዋል ኮማንደር ፋሲካ፡፡

እንዲህ ያለው ማስተማሪያ ቅጣት ሲተገበር ለምን ብለው ውዝግብ በፈጠሩ 68 ግለሰቦች እና የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ፍፁም ችላ ባሉ 26 ተቋማት ላይ ምርመራ ተደርጎባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ትናንት ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓም ባወጣው መረጃ መሰረት አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ 270,527 ግለሰቦች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 4,127 ግለሰቦች ህይወታቸው አልፏል፡፡ [ዋዜማ ሬዲዮ]

The post በአዲስ አበባ የኮቪድ መከላከያዎችን ተግባራዊ ያላደረጉ 167 ሺ 4መቶ ያህል ስዎች በፖሊስ ተይዘዋል appeared first on Wazemaradio.

Source:: http://wazemaradio.com/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3-%E1%8B%A8%E1%8A%AE%E1%89%AA%E1%8B%B5-%E1%88%98%E1%8A%A8%E1%88%8B%E1%8A%A8%E1%8B%AB%E1%8B%8E%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%89%B0%E1%8C%8D/