Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

Ethiopia: Addis Ababa Exhibition Center Revamp Stalled in Bureaucracy

Addis Chamber of Commerce

Addis Ababa Chamber of Commerce and Sectoral Associations (AACCSA) initiated a design study seven years ago to modernize the Addis Ababa Exhibition Center, a cornerstone facility for over 40 years. However, the project remains stalled due to governmental delays and a lack of approval.

[…]

Ethiopia: Somali Region Inaugurates Car Assembly Factory in Jigjiga

Car Manufacturing

Somali Regional President Mustefie Mohamed presided over the inauguration of a new car assembly factory in Jigjiga city. The factory, constructed at a cost of Birr 250 million, represents a significant development initiative for the region.

[…]

Ethiopia: Addis Ababa City Revenue Bureau Surpasses Expectations in Tax Collection

Addis Ababa Logo

Addis Ababa City Revenues Bureau (AACRB) announced a successful performance in tax collection, exceeding expectations for the past nine months.

[…]

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data – 13 May 2024

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 13 May 2024.

[…]

Ethiopia: Ethio-Djibouti Railway Marks New Era with Handover Ceremony

EDR LOGO

In Addis Ababa, the Ethio-Djibouti Railway transitioned to joint management by Ethiopia and Djibouti. For the past six years, the Chinese Railway Construction Corporation (CRCC) co-managed the line as part of China’s Belt and Road Initiative.

[…]

“ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ

በሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ መገኘቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አማራ ክልል ውስጥ ያሉ ታጣቂዎችን ከፍፍሏል። ትህነግ በድርጅት ደረጃ በውስጡ አለመጋባባት እንዳለበት፣ ከጊዜያዊ አስተዳደሩም ጋር ስምምነት እንደሌለው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ዳዊት ከበደ […] […]

ማንን እንመን ትህነግን? ወይስ ያየነውን፣ የሰማነውንን በዓይናችን የመሰከርነውን?

ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው February 4, 2021 11:10 am by Editor 2 Comments (Edit) በማይካድራ ሳምሪ በተሰኙ የተደራጁ ወጣቶች የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው ወንጀል የበለጠ እንደሆነ ኢንተርፖል አስታወቀ። ዓለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር በወርሃ ህዳር 2020 ዓ.ም በመላው ዓለም የተፈፀሙ 10 አስከፊ […] […]

Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF

Sudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan in support of the Sudanese Armed Forces (SAF). Civil war broke out in Sudan in April last year involving Rapid Support Forces (RSF) led by Hamdan Dagalo and Sudanese Armed Forces (SAF) led by military chief […] […]

በራያ የተቋረጡ የህዝብ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ፌደራል መንግስትና የትግራይ ክልል ውይይት እያደረጉ ነው

Photo- FILE

ዋዜማ- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በቅርቡ በተቆጣጠረው የራያ አካባቢ መስረታዊ የህዝብ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ከፌደራል መንግስቱ ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑንና በመግባባት እየሰራ እንደሆነ ለዋዜማ ተናግሯል።

በቅርቡ በሕወሓት ታጣቂዎች እና በአካባቢው ሚሊሻዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ፣ የማንነትና የወሰን ጥያቄ በሚነሳባቸው የራያ አካባቢዎች ኹሉም የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ መሆናቸውን፤ እንዲሁም መደበኛ እንቅስቃሴዎች በአብዛኛው መስተጓጎላቸውን ዋዜማ በሥፍራው ካሉ ነዋሪዎች አረጋግጣለች።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የደቡብ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ፣ በራያ አካባቢዎች መሰረታዊ የሚባሉ ግልጋሎቶችን ማለትም ትምህርት ቤቶችን፣ ባንኮችን፣ እንዲሁም የጤና ተቋማትን እና የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ውይይት ጀምረናል ሲሉ ለዋዜማ ተናግረዋል።

አገልግሎቶችን ለማስጀመር የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተናጠል እንቅስቃሴ ጀምሯል ያሉት አስተዳዳሪው፣ ለአብነትም መድኀኒቶችን ወደተለያዩ አካባቢዎች ማሰራጨት እንደጀመረ ጠቅሰዋል።

አስተዳዳሪው፣ ከጦርነቱ ቀደም ብሎ የነበሩ የመንግሥት ሰራተኞች ወደ ሥራ እንዲመለሱ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው፣ የአካባቢውን የህዝብ ስብጥር ለመቀየር እና ለፖለቲካ ዓላማ ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች በመንግሥት ሠራተኛነት ስም የተመደቡ ከ4 ሺሕ በላይ ሰዎች ሲቀሩ የቀድሞ ሠራተኛ አገልግሎት እንዲጀምር እያደረግን ነው ብለዋል።

አስተዳዳሪው ጦርነቱን ተጠቅመው “ሕገ-ወጥ አስተዳደር” መስርተው ነበር ያሏቸው እና አሁን ፈርሰዋል የተባሉት ኃይሎች፣ የአካባቢውን የመማሪያ መጽሐፍት እንዲሁም ካርታ ቀይረው ነበር ሲሉ ወቅሰዋል።

በፌደራሉ የትምህርት ሥርዓት መሰረት ትምህርት ቤቶችን ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ሃፍቱ ኪሮስ ተናግረዋል።

በአካባቢው ሁኔታ ላይ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ጥሩ ተስፋ የሚሰጥ መተጋገዝ መኖሩን የገለጹት አስተዳዳሪው፣ አሁን ላይ በአካባቢው ያሉት የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ ኃይሎች ከእኛ ጋር በቅርበት ይሰራሉ፤ በቀጣይም እየተጋገዝን የምንሰራበትን ሁኔታ እየፈጠርን ነው ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(ኦቻ) ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ከኮረም፣ ዛታና ኦፍላ ወረዳዎች እንዲሁም ከራያ አላማጣ፣ ባላ እና አላማጣ ከተሞች በቅርቡ በሕወሓት ኃይሎችና በአካባቢው ሚሊሻዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ የተፈናቀሉ 36 ሺሕ የሚደርሱ ዜጎች በሰቆጣ እና ቆቦ ከተሞች እንደሚገኙ አስታውቆ ነበር። ሆኖም አስተዳዳሪው ኦቻ ያወጣው መግለጫ መሬት ላይ አይገኝም፤ “የተፈናቀለ ሰው የለም” በማለት መግለጫውን አጣጥለውታል።

ይልቁንም አሁን በፈረሰው መዋቅር ውስጥ የነበሩ አመራሮች እና ከሌሎች አካባቢዎች በመንግሥት ሰራተኛ ስም መጥተው የሰፈሩ ሰዎች ተንቀሳቅሰው ሊሆን እንደሚችል ግን ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

በደቡብ ትግራይ ዞን ከእነዚህ አካባቢዎች ተፈናቅለው በመኾኒ እና በማይጨው መጠለያ ጣቢያዎች የነበሩ ከ41 ሺሕ በላይ ሰዎች ነበሩ ያሉት ሃፍቱ፣ ወቅቱ የዘር ወቅት በመሆኑ የፌደራል የጸጥታ ሃይሎች ይቆጣጠሩታል፣ በቅርበትም የእኛ ሚሊሻዎችና ፖሊሶች አሉበት ብለን በምናስባቸው ቦታዎች ሄደው የሚያርሱ ሰዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው በአካባቢው በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ነዋሪዎች፣ በአሁኑ ወቅት ኹሉም ትምህርት ቤቶች ዝግ መሆናቸውን ገልጸው፣ በአካባቢው ያሉ የትግራይ ታጣቂዎች ትምህርት ቤቶች ካሁን ቀደም ሲጠቀሙበት የነበረው በአማራ ክልል የተዘጋጀውን መጽሐፍ አንቀበልም እያሉ መሆኑን ገልጸዋል።

የመንግሥት ጤና ተቋማት በመድኀኒት እና በህክምና ቁሳቁስ ምክንያት ባብዛኛው አገልግሎት የማይሰጡ ሲሆን፣ የግል ጤና ተቋማት ከፍተኛ ገንዘብ በማስከፈል አገልግሎት ለመስጠት ሙከራ ያደርጋሉ።

የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ኹሉም ዝግ መሆናቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ በአንዳንድ ቦታዎች የትግራይ ክልል ሰንደቅ አላማ ተሰቅሎ ማየታቸውን ነግረውናል። እንዲሁም ገጠር ውስጥ ባሉ መንደሮች እና በአንዳንድ ትንንሽ ከተሞች ከትግራይ ክልል የመጡ ናቸው ያሏቸው ሰዎች ማህበረሰቡን ሰብስበው እያወያዩ ነው ብለዋል።

ከገጠር ቀበሌዎች ወደ ወረዳ ከተሞች እንዲሁም ከአንድ ወረዳ ወደ ሌላ ወረዳ ለመጓጓዝ አስተማማኝ ሰላም ባለመኖሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ባብዛኛው መቋረጡንም ጠቅሰዋል። ሆኖም ከአላማጣ ወደ መቀሌ እንዲሁም ከአላማጣ ወደ ቆቦ የሚደረጉ የመኪና ጉዞዎች ዋጋቸውን ከእጥፍ በላይ በመጨመር ጉዟቸውን መቀጠላቸውን ዋዜማ ተረድታለች።

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት፣ በአላማጣ እና ኮረም ከተሞች በይፋ የሚንቀሳቀሰው የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ቢሆንም በአጃቢዎቻቸው የሚንቀሳቀሱ ከትግራይ ክልል የመጡ አመራሮች አሉ ብለውናል።

ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እስከ 50 ሺሕ የሚገመቱ ከአካባቢው የተፈናቀሉ ዜጎች በሀሙሲት፣ ሰቆጣ፣ ቆቦ እና ወልዲያ ከተሞች ተጠልለው እንደሚገኙም ገልጸዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ፣ ጦርነቱን ተክትሎ በአማራ ክልል ስር የተቋቋሙ አስተዳደሮች እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም. መፍትሄ ያገኛሉ ሲሉ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል። [ዋዜማ]

The post በራያ የተቋረጡ የህዝብ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ፌደራል መንግስትና የትግራይ ክልል ውይይት እያደረጉ ነው first appeared on Wazemaradio.

The post በራያ የተቋረጡ የህዝብ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ፌደራል መንግስትና የትግራይ ክልል ውይይት እያደረጉ ነው appeared first on Wazemaradio.

[…]

በትግራይ 81 በመቶ ወጣት ስራ-አጥ ነው፣ 89  በመቶ ወጣቶች ትዳር መመስረት አንፈልግም ብለዋል

PHOTO-FILE

ዋዜማ- ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ የነበረችው ትግራይ በጦርነቱ ማግስት ከገጠሟት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አንዱ የወጣቶች በገፍ ክልሉን እየለቀቁ መሰደድ ነው።

በትግራይ ስደት ከጦርነቱ በፊትም የነበረ ቢሆንም ከጦርነቱ በኋላ ግን እጅግ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ እንደጨመረ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር የወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ሓይሽ ሱባጋድስ ለዋዜማ ተናግረዋል።

እድሜያቸው ከ 15 እስከ 18 የሚሆኑ ታዳጊዎች ትምሕርታቸውን አቋርጠው ከአገር እየወጡ እንደሆነ፣ አብዛኞቹ በየመን እና ሳውዲ አረቢያ እስር ቤት ወስጥ ቀሪዎቹ ደግሞ በሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች እጅ እንዳሉና በርካታ ወጣቶችም በመንገድ ላይ እና በበረሃ እየሞቱ እንደሆነ መረጃዎች ይደርሱናል ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል።

ከወራት በፊት የመንን አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊገቡ ሲሉ በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ከተገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንና፣ ጅቡቲ ላይ በጀልባ መስጠም አደጋ ሕይወታቸውን ካጡት መካክል፣ አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች መሆናቸውን ኃላፊው ለዋዜማ አረጋግጠዋል።

ይህ አስደንጋጭ ክስተት እየታየ እንኳን በቀሪዎቹ ወጣቶች ላይ የመሰደድ ፍላጎት ሲቀንስ አለመታየቱ በትግራይ ክልል ያለው ችግር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያል ይላሉ ሓይሽ።

እንደ አይ ኦ ኤም ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያወጡት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በዚህ ውቅት እንደ አገር ያለው የስደት ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የሚያሳይ ሲሆን ፣ በትግራይ ያለው ግን ከዚያ የተለየና ለመቆጣጠርም አዳጋች የሆነ ነው።

ትግራይ ውስጥ ባሉ የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከ 500 ሺሕ በላይ ተፈናቃይ ወጣቶች አሉ፣ በመጠለያ ጣቢያው በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ ባለመኖሩና ምንም አይነት ለነገ የሚሉት ተስፋ የሚታያቸው ባለመሆኑ ወጣቶቹ ስደትን ቀዳሚ ምርጫቸው አድርገዋል ብለዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ ወጣቶቹ በብዛት እየተሰደዱ ያሉት ከምሥራቅ እና ደቡብዊ ዞኖች፣ከሰሜን ምዕራብ እና ሰሜናዊ የትግራይ አካባቢዎች፣ከመቀሌ ከተማ እና አካባቢዋ በተወሰነ መልኩ እንደሆነ ኃላፊው ሓይሽ ተናግረዋል።

ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እንዲሁም የሕገ ወጥ ደላሎች ማታለያ ለመሰደዳቸው ሌላው ምክንያት እንደሆነ ሓይሽ ያስረዳሉ።

ዋዜማ በዚሁ ጉዳይ ላይ የትግራይ ክልል ወጣቶች ማኅበርን ያነጋገረች ሲሆን ማኅበሩ በክልሉ ያለው ሥራ አጥነት ያስከተለው የወጣቶች ስደት እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲል ገልጿል።

የክልሉ ወጣቶች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ሠናይ ከሓሳይ ለዋዜማ እንደተናገሩት ማኅበሩ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በመተባበር በ 10 ወርዳዎች፣ በ 30 ቀበሌዎችና በ1 ሺህ 200 መቶ ወጣቶች ላይ ፈጣን የዳሰሳ ጥናት ማድረጉን ገልጸዋል።

የጥናቱም ፍለጋ ከጦርነቱ በኋላ የወጣቱ መተዳደሪያ ምንድነው?፣ትምሕርት ጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ከማግኘት አንጻር ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል የሚሉ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ለዋዜማ አስረድተዋል።

ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶች ባለመኖራቸውና በክልሉ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም የሚጨበጥ ተስፋ ባለመኖሩ ምክንያት ካሉት ወጣቶች መካከል ግማሽ ያህሉ የመሰደድ ሃሳብ ያላቸው እንደሆኑ በተደረገው ጥናት መሰረት ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።

ጥናቱ እንደሚያመለክትው በዚህ ወቅት ትግራይ ውስጥ ካሉ ወጣቶች መካከል 81 በመቶ የሚሆኑት ሥራ አጥ መሆናቸውን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ እነዚህ ወጣቶች አብዛኞቹ ከጦርነቱ በፊት የራሳቸው ተቋም የነበራቸው፣ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ፣ መልካም የሚባል ሕይወት ሲመሩ የነበሩ መሆናቸውና ከጦርነቱ በኋላ ግን ያላቸውን ጥሪት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ያጡ ናቸው ሲሉ።

ከትምህርት ፍላጎት ጋር ተያይዞ በወጣቶቹ ላይ በተደረገው ጥናት ካሉት ወጣቶች መካከል 78 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የመማር ፍላጎት የሌላቸው ናቸው የሚሉት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦቻቸን ያላቸውን ነገር በሙሉ ስላጡ እኛን የሚያስተምሩበት አቅም የላቸውም የሚል እንደሆነ አብራርተዋል።

ከሥራ ፈጠራ አንጻር፣ 31 በመቶ የሚሆኑት የራሳችን ሥራ ፈጥረን እንሰራለን የሚሉ እንደሆኑ 29 በመቶዎቹ ደግሞ በተለያዩ መንግሥታዊና የግል ተቋማት ተቀጥረን መስራት አለብን የሚል ሃሳብ ያላቸው፣ ቀሪዎቹ ግን የመሰደድ ፍላጎት ያላቸው ናቸው ብለዋል

ከነዚህ የመሰድድ ፍላጎት ካላቸው ውስጥ 53 በመቶዎቹ እድሜያቸው ከ 26 እስከ 35 ባለው መካከል የሚገኝ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ግን ከ 15 እስከ 25 ባለው መካከል እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዞ በክልሉ ካሉ ወጣቶች 78 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የበይነ መረብ አገልግሎት እንደማያገኙ 97 በመቶ የሚሆኑት የኮምፒዩተር አገልግሎት፣ 29 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የስልክ አገልግሎት የሌላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ሥራ ለመፈለግና የሚወጡ የሥራ እድሎችን እንዲሁም ማስታወቂያዎችን ለማየት አስቻይ ሁኔታ የላቸውም በማለት ተናግረዋል።

ከማኅበራዊ ሕይወታቸው ጋር ተያይዞ 89 በመቶ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ትዳር የመያዝ፣ ኃላፊነት የመውሰድና ቤተሰብ የመመስረት ፍላጎት እንደሌላቸው ባደረጉት ጥናት ማረጋገጣቸውን ተናገረዋል።

በሌላ በኩል ትግራይ ከጦርነቱ መገባደድ በኋላ የዝናብ እጥረት ያስከተለው ድርቅ፣ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ተደማምረው የደቀቀው ምጣኔ ሀብቷ ለወጣቱ መሰደድ ሌላው ምክንያት ነው ብለዋል።

ዋዜማም በሕገወጥ መንገደ ተሰደው በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙትን የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች በስልክ አነጋግራለች።

ሕሉፍ ዓባይ ተወልዶ ያደገው በሽረ እንዳ ሥላሴ ከተማ ገባር ሽረ በተባለ አካባቢ እንደሆነ ለዋዜማ የገለጸ ሲሆን፣ በዚያም የሚተዳደረው በብረት ብየዳ ሥራ እንደነበር፣ በጦርነቱ ምክንያት ግን ያለው ሃብት ንብረት በሙሉ እንደወደመትና ባዶ እጁን እንደቀረ ይናገራል።

ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት መሆኑን የሚገልጸው ሕሉፍ የሚያደርገው ቢጠፋው የራሱንንና የቤተሰቡን ሕይወት ለማሰንበት በሕገ ወጥ መንገድ መሰደድን መምረጡን ገልጿል።

ሕሉፍ ያሰበውና የሆነው ለየቅል እንደሆነበትና በሳውዲ አረቢያ የጸጥታ ኃይሎች ተይዞ በእስር ቤት ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት መግፋት ከጀመረ አምስት ወራት መቆጠራቸውን አስረድቷል።

ሌላኛው ከውቅሮ ከተማ ተሰዶ እንደወጣና ትምህርቱን ከአስራ አንደኛ ክፍል እንዳቋረጠ የሚናገረው ሀበን ተስፋይ ቤተሰቦቹ ሊያስተምሩት አቅማቸው ባለመፍቀዱ ስደትን መምረጡን ገልጿል።

በእስር ቤቶቹ ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰደው የወጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች መኖራቸውን ዋዜማ በእስር ቤቱ ወስጥ ካሉ ሰዎች ማረጋገጥ ችላለች።

ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረቻቸው የክልሉ ወጣቶች ቢሮና የወጣቶች ማኅበር ወጣቶቹን ከስደት ለመታደግ በፌዴራል መንግስቱም ይሁን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት እጅግ አነስተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። [ዋዜማ]

The post በትግራይ 81 በመቶ ወጣት ስራ-አጥ ነው፣ 89 በመቶ ወጣቶች ትዳር መመስረት አንፈልግም ብለዋል first appeared on Wazemaradio.

The post በትግራይ 81 በመቶ ወጣት ስራ-አጥ ነው፣ 89 በመቶ ወጣቶች ትዳር መመስረት አንፈልግም ብለዋል appeared first on Wazemaradio.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.