Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

Ethiopia Commodity Exchange (ECX) Daily Trade Data - 28 March 2023

ECX Logo

Here is the daily commodity trade data from Ethiopia Commodity Exchange (ECX) for items traded on 28 March 2023.

[…]

የሀገር ውስጥ የዋጋ ንረት የወጪ ንግዱን ፈተና ውስጥ ጨምሮታል

Gebremeskel Chala, MoTI- FILE

  • ቡና ላኪዎች ውል ለማቋረጥ ተገደዋል
  • የበሬ ስጋ የወጪ ንግድ ሊቆም ጫፍ ላይ ደርሷል

ዋዜማ- በሀገር ውስጥ ያለውና በቁጥጥር ስር ሊውል ያልቻለው የዋጋ ንረት የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ እየተፈታተነው እንደሆነ ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች ያሰባሰበችው መረጃ ያመለክታል።

የተለያዩ ምርቶችን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ላኪዎች ከሀገር ውስጥ የሚገዙበት ዋጋ ከፍተኛ ጭማሬን እያሳየ በመምጣቱ ከሌሎች ሀገራት ላኪዎች ጋር መወዳደር እያቃታቸው በመምጣቱ ነው።

የስጋ የወጪ ንግድ በዚህ አመት ከፍተኛ የሆነ የተወዳዳሪነት ችግር አጋጥሞት የምንዛሬ ገቢያቸው እያሽቆለቆለ ከመጡት ከቀዳሚዎቹ ነው። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የስጋ ላኪ ኩባንያ ባለሀብት ለዋዜማ እንደነገሯት የስጋ ምርት በስፋትና በዋነኝነት በሚላክበት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ዱባይ) ገበያ የኢትዮጵያ ምርት በኬንያ ከፍተኛ ብልጫ እየተወሰደበት ከገበያ እየወጣ ነው ።

ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ለውጭ ገበያ ልካ 120 ሚሊየን ዶላር አካባቢ ካገኘችበት የስጋ ምርት ውስጥ 90 በመቶውን ድርሻ የፍየል ስጋ ይይዛል።

“አሁን ላይ የፍየል ስጋን ውጭ ለመላክ ከሀገር ውስጥ የምንጠየቀው ዋጋ ከፍተኛ ጭማሬን አሳይቷል ” የሚሉት ባለሀብቱ ከአንድ ወር በፊት ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች በኪሎ 340 ብር የነበረው የፍየል ስጋ አሁን 400 ብር ገብቷል ። ይኸው ዋጋ የዛሬ አመት 270 ብር ነበር ብለዋል። (ዋጋው የሚወጣው ፍየሎቹ በላኪዎቹ ታርደው በሚሰራ ልኬት ነው።)

በውጭ ምንዛሬ ሲሰላ አሁን ለፍየል ስጋ በኪሎ ለሀገር ውስጥ አቅራቢዎች 7.4 የአሜሪካ ዶላርን መክፈል ይጠበቅብናል የሚሉት ነጋዴው ብሄራዊ ባንክ ደግሞ ይሄንኑ ምርት ለውጭ ገበያ በኪሎ በትንሹ በ6.6 የአሜሪካ ዶላር እንድንሸጥ ነው ያዘዘን ይላሉ።

ይህ ኪሳራ መሆኑን የሚያነሱት ሌላ በስጋ የወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰብ ” ወጪያችንን ከግምት ያስገባ ዋጋን ተምነን እንዳንሸጥ ችግር የሆነብን የጎረቤት ሀገር ኬንያ ላኪዎች በተሻለ ዋጋ ከሀገራቸው አቅርቦት ስላላቸው በዱባይ ገበያ እንዳንፎካከር አድርጎናል “ ይላሉ።

የኬንያ ላኪዎች አንድ ኪሎ ግራም የፍየል ስጋን ከሀገራቸው አቅራቢዎች በ3.8 የአሜሪካ ዶላር ያገኛሉ። ይህንንም ዱባይ ላይ 6 ዶላር እየሸጡት በመሆኑ የኢትዮጵያን ላኪዎች ከገበያ እያስወጧቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ስጋ ላኪዎች ይናገራሉ።

በዚህ በጀት አመት ለውጭ ገበያ የተላከ ስጋ በመጠንም በውጭ ምንዛሬ ግኝትም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው። ባለፈው በጀት አመት የመጀመርያ ሰባት ወራት ውስጥ 13800 ቶን ስጋ ለውጭ ገበያ ተልኮ 68 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የተገኘ ሲሆን በዚህ በጀት አመት የመጀመርያ ሰባት ወራት 9600 ቶን ስጋ ተልኮ የተገኘው የውጭ ምንዛሬ የ11 ሚሊየን ዶላር ቅናሽ አሳይቶ 57 ሚሊየን ዶላር ነው።

በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ንረት የበሬ ስጋ ላኪዎችን ተወዳዳሪ ማድረግ ስላልቻለ አብዛኞቹ ላኪዎች የበሬ ስጋን መላክ አቁመዋል። የስጋ የወጪ ንግድ ባለፈው አመት ከግብርና ምርቶች ከቡና ቀጥሎ 120 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት ቀዳሚ ነበር።በዚህ አመት ግን ተመሳሳይ ውጤት ማስመዝገቡ ጥርጣሬ ውስጥ ወድቋል።

ቡናችን

የቡና የወጪ ንግድም በሀገር ውስጡ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ሳቢያ ፈተና ካንዣበባቸው ውስጥ ነው። በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች እንደነገሩን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚገዛ ቡና እጥፍ ሊደርስ የሚችል የዋጋ ጭማሬን ማሳየቱን ገልጸዋል።አንድ ኪሎ እሸት ቡና ከገበሬ ላይ የሚገዛበት ዋጋ 110 ብር ደርሷል። አምና ዋጋው 60 ብር ገደማ ነበር።

አንድ ኪሎ ለውጭ የሚቀርብ ቡናን ለማምረት ሰባት ኪሎ እሸት ቡና ያስፈልጋል። ስለዚህ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ደረጃ አንድ ፣ አንድ ኪሎ ቡናን አንድ ላኪ ከ770 ብር ያላነሰ ወጪ አውጥቶ ከሀገር ውስጥ ይገዛል። ይህ በውጭ ምንዛሬ 14 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው።

ሆኖም በአለም ገበያ እንደየ ጥራትና የበቀለበት ሀገር የተለያየ ሆኖ የአንድ ኪሎ ቡና ዋጋ ከ7 እስከ 8 የአሜሪካ ዶላር ነው። በኒው ዮርክ ዓለማቀፍ የቡና ግብይት ላይ ደግሞ ዋጋ ደግሞ ካለፈውም አመት የአንድ ዶላር አካባቢ ቅናሽ አሳይቶ አንድ ፓውንድ (ግማሽ ኪሎ አካባቢ) ቡና በ1.9 ዶላር አካባቢ ነው የሚሸጠው።

አሁን ያለው የአለም የቡና ዋጋ የኢትዮጵያ ላኪዎች ከሀገር ውስጥ ከሚሰበስቡበት ዋጋ በእጅጉ በማነሱ በርካታ ላኪዎች ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል።ዋዜማ ከታማኝ ምንጮቿ እንዳረጋጠጠችው ከሆነ ከፍተኛ ቡና ላኪ የሚባሉ ሳይቀሩ አሁን ያለው ዋጋ ቀድሞ በገቡት ውል ላይ ሰፊ ልዩነት ስላለው ለመላክ የገቡትን ውል አላከበሩም። 100 ያህል ውል ያፈረሱ ላኪዎች እንዳሉም ሰምተናል።

ቡና ባለፈው አመት 1.4 ቢሊየን ዶላር በማስገኘት ክብረወሰን አስመዝግቦ ነበር። በወቅቱ 300 ሺህ ቶን ቡና ለአለም ገበያ ቀርቧል። በዚህ በጀት አመት የመጀመርያ ሰባት ወራት የተላከው ቡና 126 ሺህ ቶን ሲሆን ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር በመጠን ያነሰ ነው። የተገኘው 702 ሚሊየን ዶላርም በቀሪ አምስት ወራት ውስጥ የባለፈውን አመት ገቢም ሆነ በመንግስት የታቀደውን ሁለት ቢሊየን ዶላር ለማስገኘቱ ጥርጣሬ ፈጥሯል።

ባለፈው አመት ከወጪ ንግድ አራት ቢሊየን ዶላር የተገኘ ሲሆን በዚህ አመት የመጀመርያ ሰባት ወራት ሁለት ቢሊየን ዶላር እንደተገኘ መረጃዎች ያሳያሉ። [ዋዜማ]

The post የሀገር ውስጥ የዋጋ ንረት የወጪ ንግዱን ፈተና ውስጥ ጨምሮታል first appeared on Wazemaradio.

The post የሀገር ውስጥ የዋጋ ንረት የወጪ ንግዱን ፈተና ውስጥ ጨምሮታል appeared first on Wazemaradio.

[…]

Japan and Ethiopia to Collaborate for the Development of Horticulture

Japan Horticulture

Ethiopia and Japan penned an agreement to collaborate in the implementation the second phase of the Small Holder Farmers Empowerment Project which is aimed at developing horticulture in Ethiopia. The first phase of the project was implemented in Amhara and Oromia Regional States. The second phase targets Sidama and Southern Nations, Nationalities, and Peoples Regional State.

[…]

Ethiopia: Ministry Working to Facilitate Government-Guaranteed Loans to Enterprises

Ethiopian Enterprises

The Ministry of Labour and Skills is working to make government-guaranteed loans available to enterprises. During a consultation held on challenges faced by enterprises in Ethiopia, Nigusu Tilahun, State Minister of Ministry of Labour and Skills, stated that the envisaged scheme would solve financial challenges for enterprises and enhance their effectiveness.

[…]

Why Free Trade Agreements with the EU will hurt African countries!

EPAs is not a Panacea for Africa’s Economic and Social Crisis but deepen the Crisis! Nor can AGOA be the engine of economic development that is based on science and Technology Fekadu Bekele (Ph D) …

Why Free Trade Agreements with the EU will hurt African countries! Read More »

The post Why Free Trade Agreements with the EU will hurt African countries! first appeared on Zehabesha Latest Ethiopian News, Videos, Photos & Headlines.

[…]

Why Free Trade Agreements with the EU will hurt African countries!

EPAs is not a Panacea for Africa’s Economic and Social Crisis but deepen the Crisis! Nor can AGOA be the engine of economic development that is based on science and Technology Fekadu Bekele (Ph D) …

Why Free Trade Agreements with the EU will hurt African countries! Read More »

The post Why Free Trade Agreements with the EU will hurt African countries! first appeared on Zehabesha Latest Ethiopian News, Videos, Photos & Headlines.

[…]

Grandpa Was An Emperor will be shown in Los Angeles from April 7 to the 13th

Ethiopians for Constitutional Monarchy Grandpa was an Emperor Trailer | 2023 Grandpa Was An Emperor will be shown in Los Angeles from April 7 to the 13th at the Laemmles Town Center in Encino, with …

Grandpa Was An Emperor will be shown in Los Angeles from April 7 to the 13th Read More »

The post Grandpa Was An Emperor will be shown in Los Angeles from April 7 to the 13th first appeared on Zehabesha Latest Ethiopian News, Videos, Photos & Headlines.

[…]

Emahoy Tsegué-Maryam Guèbrou, an Ethiopian nun, composer and pianist, has died at the age of 99.

According to the country’s state-run news outlet Fana Broadcasting Corporate, she died in Jerusalem. Guèbrou had been living at the Ethiopian Monastery there for almost 40 years. As a child, she spent time as a prisoner …

Emahoy Tsegué-Maryam Guèbrou, an Ethiopian nun, composer and pianist, has died at the age of 99. Read More »

The post Emahoy Tsegué-Maryam Guèbrou, an Ethiopian nun, composer and pianist, has died at the age of 99. first appeared on Zehabesha Latest Ethiopian News, Videos, Photos & Headlines.

[…]

በጌዴኦ ዞን ከሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ውስጥ 98 በመቶ የሚሆኑት ለማስተማር ብቁ አይደሉም

Gedeo- Dilla- FILE

ዋዜማ- በጌዴኦ ዞን 320 ትምሕርት ቤትዎች የሚገኙ ሲሆን የትምህርት ሚንስቴርን መመዘኛ አሟልተው ‘’ትምሕርት ቤት ‘’ለመባል የሚበቁት 13 ብቻ መሆናቸውን ዋዜማ ከዙኑ ትምሕርት መምሪያ ኃላፊ ሰምታለች፡፡

ከ80 በላይ የትምህርት ቤት የደረጃ መለኪያዎች ቢኖሩም በጌድኦ ዞን የሚገኙት ትምህርት ቤቶች ግን መሰረታዊ የሚባሉትን የደረጃ መለኪያዎች እንኳን የሚያሟሉ አይደሉም።

ከእነዚህ መካከል ከፍተኛውን ስፍራ የሚይዙት የግንባታ ሁኔታ፣ ለተማሪዎች እና ለመማር ማስተማር ምቹ መሆን፣የሚያስፈልግ የሰው ሐይል፣ቤተ መፅሐፍት፣ቤተ ሙከራ፣ውሃ ፣መብራት ፣መፀዳጃ ቤት፣የትምህት አመራር እና አስተዳደር ናቸው፡፡

በመመዘኛዎቹ መሰረት በጌዲኦ ዞን የሚገኙ 98 በመቶ ትምሕርት ቤቶች የጥራት ደረጃን የሚያሟሉ አይደሉም፡፡

በዞኑ በርከት ያሉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ፡፡ በ2015 ዓ.ም ትምህርት በመከታተል ላይ ከሚገኙ 266 ሺህ 700 ተማሪዎች ውስጥ ከ18ሺህ በላይ የሚሆኑት ትምህርታቸውን አቋርጠዋል፡፡

ዋዜማ ከዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘማች ክፍሌ እንደሰማችው ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከሚያቋርጡባቸው ምክንያቶች መካከል የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ቀውሶች፣ በጌዲዮ ዙሪያ ያለው የጸጥታ ስጋት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡

በጸጥታ ስጋት የተነሳ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ ይህን ተከትሎ 2014 ዓ.ም አምስት ትምህርት ቤቶች አገልግሎት መስጠት ባለመቻላቸው ተዘግተዋል፡፡ ዘንድሮም በጌዲኦ ዙሪያ በሚገኙ አራት ወረዳዎች ‘’የኦነግ ሸኔ’’ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ነዋሪዎች ተረጋግተው መኖር ስላልቻሉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት በዞኑ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ምጣኔ በመቶኛ ሲሰላ 14 በመቶ የነበር ሲሆን ዘንድሮ ወደ 6 በመቶ ዝቅ ብሏል ። ምንም እንኳን ቁጥሩ የመቀነስ አዝማሚያ ቢኖረውም ችግሩ ቀላል የሚባል አይደለም ሲሉ የትምሕርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘማች ክፍሌ ገልጸዋል፡፡

የቡና አብቃይ በሆነችው ጌዲኦ ተማሪዎች በትምሕርታቸው እንዲቀጥሉ ከማድረግ ይልቅ ወደ ቡና ንግድ እና ስራ እንዲገቡ በማሕበረሰቡ ይበረታታሉ፡፡ [ዋዜማ]

The post በጌዴኦ ዞን ከሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ውስጥ 98 በመቶ የሚሆኑት ለማስተማር ብቁ አይደሉም first appeared on Wazemaradio.

The post በጌዴኦ ዞን ከሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ውስጥ 98 በመቶ የሚሆኑት ለማስተማር ብቁ አይደሉም appeared first on Wazemaradio.

[…]

Reflections on Forging a “Refashioned” US-Ethiopia Partnership

Al Mariam’s Commentaries March 27, 2023 US Secretary of State Antony Blinken visited Ethiopia on March 15, 2023. His mission was to refashion, reinvigorate and reinvent the strong partnership between the US and Ethiopia that …

Reflections on Forging a “Refashioned” US-Ethiopia Partnership Read More »

The post Reflections on Forging a “Refashioned” US-Ethiopia Partnership first appeared on Zehabesha Latest Ethiopian News, Videos, Photos & Headlines.

[…]

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.