Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 37 ቢሊየን ብር የካፒታል ማሳደጊያ እንዲሰጠው ተወሰነ

  • የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘቡ ከአለም ባንክ ይገኛል ተብሏል

ዋዜማ- መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁን ካለው 43 ቢሊየን ብር ካፒታል በተጨማሪ ከ37.1 ቢሊየን ብር በላይ(650 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር) የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብ እንዲሰጠው ተወሰነ። ውሳኔውም የንግድ ባንኩን አጠቃላይ ካፒታል ከ80 ቢሊየን ብር በላይ የሚያደርገው ሲሆን፣ይህም ከሌሎች ከግል ባንኮች አንፃር ያለውን የበላይነት እጅግ ያገዝፈዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካፒታል እንዲያድግ የተወሰነው ትላንት ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ/ም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ ሲሆን ፣ በዚህም ምክር ቤቱ ፣ በባንኩ የሪፎርም እና የካፒታል ማሳደጊያ ዕቅድ ላይ መምከሩን ገልጾ ፣ የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በሙሉ ድምጽ መወሰኑም ታውቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመግለጫው ለባንኩ የሚሰጠውን የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብን ያልገለጸ ሲሆን ፣ ዋዜማ የካፒታል ገንዘቡ ከሚተላለፍበት ከገንዘብ ሚኒስቴር ምንጮቿ ባገኘችው መረጃ ለመንግስታዊው ባንክ የሚሰጠው የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብ ከ37 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑን አረጋግጣለች።

የዋዜማ ምንጮች አክለው እንደገለጹትም የመንግስታዊውን ባንክ ካፒታል በዚህ ደረጃ ለማሳደግ የተፈለገበት አንዱ ምክንያት ኢትዮጵያ የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ገበያ እየከፈተች በመሆኑ መንግስታዊውን ባንክ ጠንካራና ተወዳዳሪ አድርጎ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖም በመገኘቱ ነው።

የካፒታል ማሳደጊያው ገንዘብም ከአለም ባንክ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቻችን ነግረውናል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም ባንክ እና ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) ጋር እያደረገ ባለው ድርድር የሀገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት ማጠናከር የሚለው አንዱ አጀንዳ በመሆኑ ፣ ለንግድ ባንክ የሚገኘው የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብም ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር የምትፈራረማቸውስምምነት አካል መሆኑንም ተገንዝበናል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከሰሞኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2017 ዓ/ ም በጀትን በንባብ ባቀረቡበት ወቅት : አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ከኢትዮጵያ የሚፈልጓቸውን ብር ማዳከም አይነት ፖሊሲዎችን ሀገሪቱ በቅርቡ አትተገብርም ማለታቸው ከእነ አለም ባንክ ጋር እየተደረገ ያለውን ድርድር ያከተመለት ቢያስመስለውም ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከአለም ባንክ በሚገኝ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካፒታል ማሳደጊያ ገንዘብ ላይ ከውሳኔ መድረሱ የሀገሪቱን እና የገንዘብ ተቋማቱን የድርድር አዝማሚያ አመላካች ሆኗል።።

በከፍተኛ ደረጃ ካፒታሉ እንዲያድግ የተወሰነለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰጠው ብድርም በሰበሰበው ቁጠባም በእያንዳንዳቸው አንድ ትሪሊየን ብር ያለፈ ብቸኛ የኢትዮጵያ ባንክ ነው። [ዋዜማ]

The post የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 37 ቢሊየን ብር የካፒታል ማሳደጊያ እንዲሰጠው ተወሰነ first appeared on Wazemaradio.

The post የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 37 ቢሊየን ብር የካፒታል ማሳደጊያ እንዲሰጠው ተወሰነ appeared first on Wazemaradio.

Source:: https://wazemaradio.com/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%8B%B5-%E1%89%A3%E1%8A%95%E1%8A%AD-37-%E1%89%A2%E1%88%8A%E1%8B%A8%E1%8A%95-%E1%89%A5%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%8A%AB%E1%8D%92/?utm_source=rss&utm_medium=rss&utm_campaign=%25e1%258b%25a8%25e1%258a%25a2%25e1%2589%25b5%25e1%258b%25ae%25e1%258c%25b5%25e1%258b%25ab-%25e1%258a%2595%25e1%258c%258d%25e1%258b%25b5-%25e1%2589%25a3%25e1%258a%2595%25e1%258a%25ad-37-%25e1%2589%25a2%25e1%2588%258a%25e1%258b%25a8%25e1%258a%2595-%25e1%2589%25a5%25e1%2588%25ad-%25e1%258b%25a8%25e1%258a%25ab%25e1%258d%2592

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.