Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

በፀጥታ ምክንያት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የባንክ አገልግሎት ተቋረጠ

ዋዜማ-በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የፋኖ ታጣቂዎች በተቆጣጠሯቸውና ወጣ ገባ በሚሉባቸው ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉን ዋዜማ ተረድታለች፡፡

በዞኑ የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ወረዳዎች መካከል መንዝ ላሎ፣ ግሼ ራቤል፣ አንፆኪያ ገምዛና ቀወት እንደሚገኙበት ዋዜማ በየወረዳዎቹ የባንክ ቅርንጫፎች አረጋግጣለች፡፡ የባንክ አገልግሎቱን በተጠቀሱት ወረዳዎች እንዲያቋርጡ የተገደዱት የግል ባንኮች ጭምር መሆናቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በተጠቀሱት ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት የተቋረጠው ካለፈው አርብ ሰኔ 7/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ዋዜማ ተረድታለች፡፡ ከአርብ ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ስዓት ድረስ በመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ፣ በግሼ ራቤል ወረዳ ራቤል ከተማ፣ በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ መኮይ ከተማና ቀወት ወረዳ ራሳ ከተማ ባንኮች እንደተዘጉ ናቸው፡፡

በአንጻሩ የአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ አካል በሆነችው ማጀቴ ከተማ ባንኮች አገለግሎት መስጠት መቀጠላቸውን ዋዜማ ከከተማዋ ነዋሪዎች ሰምታለች፡፡ ምንም እንኳን በከተማዋ አገልግሎት ባይቋረጥም ባንኮች ለደንበኞቻቸው የሚሰጡት ወጪ ገደብ ተጥሎበታል ተብሏል፡፡ 

አገልግሎቱ የተቋረጠው ባንኮቹ ድንገተኛ ትዕዛዝ ከመንግሥት አካል ከደረሳቸው በኋላ መሆኑን፣ የየወረዳዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የግል ባንኮች ሰራተኞች ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡ ድንገተኛ የተባለው ትዕዛዝ ለባንኮቹ የተላለፈው የሸዋ ቀጠናን ከሚመራው ኮማንድ ፖስት መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በተጠቀሱት ከተሞች የሚገኙ የባንኮች ቅርንጫፎች የኮማንድፖስቱ ትዕዛዝ የደረሳቸው በየዲስትሪክቶቻቸው በኩል መሆኑ ጠቁመዋል፡፡ ባንኮቹ ከኮማንድ ፖስቱ የደረሳቸው ትዕዛዝ “ኮማንድ ፖስቱ አካባቢውን ከጽንፈኞች እስከሚያጸዳ ድረስ አገልግሎት አቁሙ” በሚል የተገለጸ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ምንም አንኳን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት ጊዜ ቢያበቃም አካባቢው በወታደራዊ ኮማንድ ፖስት መመራቱን ቀጥሏል፡፡ ባንኮች ሥራ እንዲያቆሙ በኮማንድ ፖስቱ አማካኝነት ትዕዛዝ የተላለፈውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት ቀን ገደብ ከባቃ በኋላ ነው፡፡

ዋዜማ ስለ ጉዳዩ የባንክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ወረዳዎች የሚገኙበት ሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የቀጠናው ኮማንድ ፖስት አባል አቶ መካሽ አለማየሁን ለማነጋገር ሞክራለች፡፡ ይሁን እንጅ የዞኑ አስተዳዳሪ ስልክ አንተው ካነጋገሩን በኋላ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡ ስልክ ዘግተዋል፡፡ ስልኩ ከተቋረጠ በኋላ በድጋሚ ቢደወልላቸውም ባለመመለሳቸው ከመንግሥት ወገን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

አገልግሎት የተቋረጠባቸው ቅርንጫፎች ላይ ይሰሩ የነበሩ የባንክ ሰራተኞች ወደሌላ ሌላ ቦታ ሥራ እየተመደቡ ነው ተብሏል፡፡ ለአብነትም የመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ ቅርንጫፍ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞች፣ ወደ መንዝ ማማ ወረዳ ምላሌ ከተማ ቅርንጫፎች ተዘዋውረው ሥራ መጀመራቸውን ለዋዜማ አረጋግጠዋል፡፡

በተጠቀሱት ከተሞች የሚገኙ ባንኮች በዕለቱ ትዕዛዙ ከደረሳቸው በኋላ የቀኑን ሂሳባቸውን ዘግተው፣ ወዲያ አገልግሎት ማቆማቸውን የየቅርጫፎቹ ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡

የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ወረዳዎች መካከል የመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማን ጨምሮ፣ የግሼ ወረዳው ከተማ ራቤልን ጨምሮ፣ ይህ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ስዓት ድረስ በፋኖ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ዋዜማ ከአየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ሰምታለች፡፡

ሌላኛው የባንክ አግልግሎት የተቋረጠበት የአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ መቀመጫ መኮይ ከተማ በመንግሥት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኗን ዋዜማ ተረድታለች፡፡ የመንግሥት ኃይሎች ከተማዋን የተቆጣጠሩት በዚሁ ሳምንት ሲሆን፣ ከዚያ በፊት የፋኖ ታጣቂዎች ከተማዋን ተቆጣጥረው መሰንበታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ [ዋዜማ]

The post በፀጥታ ምክንያት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የባንክ አገልግሎት ተቋረጠ first appeared on Wazemaradio.

The post በፀጥታ ምክንያት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የባንክ አገልግሎት ተቋረጠ appeared first on Wazemaradio.

Source:: https://wazemaradio.com/%E1%89%A0%E1%8D%80%E1%8C%A5%E1%89%B3-%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%8A%95%E1%8B%AB%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%88%B0%E1%88%9C%E1%8A%95-%E1%88%B8%E1%8B%8B/?utm_source=rss&utm_medium=rss&utm_campaign=%25e1%2589%25a0%25e1%258d%2580%25e1%258c%25a5%25e1%2589%25b3-%25e1%2588%259d%25e1%258a%25ad%25e1%258a%2595%25e1%258b%25ab%25e1%2589%25b5-%25e1%2589%25a0%25e1%258a%25a0%25e1%2588%259b%25e1%2588%25ab-%25e1%258a%25ad%25e1%2588%258d%25e1%2588%258d-%25e1%2588%25b0%25e1%2588%259c%25e1%258a%2595-%25e1%2588%25b8%25e1%258b%258b

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.