Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.

በራያ አላማጣ በትግራይ ታጣቂዎችና ነዋሪዎች መካከል ውጥረት ተባብሷል፤ ሶስት ሰዎች ተገድለዋል

ዋዜማ – የትግራይ ታጣቂዎች በራያ አላማጣ ከተማ በሁለት ሳምንት ውስጥ ሦስት ሰላማዊ ሰዎችን ገድለው፣ አምስት ሰዎችን ማቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለዋዜማ ተናግረዋል።

በከተማዋ በሚገኝ ትምህርት ቤት ካምፕ አድርገው ተቀምጠዋል የተባሉት ታጣቂዎች፣ ቅዳሜ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም አንድ ወጣት መግደላቸውን ነዋሪዎች ገልጠዋል።

ዋዜማ ያነጋገራቸው የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች እንደነገሩን የተገደለው ወጣት፣ ያሬድ መልካሙ የተባለ የኤሌክትሪክ ባለሙያ ነው። ወጣቱ የተገደለው በጥይት ተመቶ ነው ተብሏል።

ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ በሌሊት በግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ቦምብ አፈንድተው ሁለት ሰዎችን ገድለው፣ አራት ሰዎችን አቁስለዋል ሲሉ የአይን እማኞች ለዋዜማ ነግረዋል።

እንዲሁም ባለፈው ሐሙስ ምሽት ላይ አንድ ሰው በሽጉጥ ተመቶ ቆስሎ፣ በወልዲያ ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ነው መሆኑን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

የትግራይ ኃይሎች የተወነጀሉባቸውን  ግድያዎች መፈጸማቸውን የፈረሰው የቀድሞው አስተዳደር የአላማጣ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ኃይሉ አበራ ለዋዜማ አረጋግጠዋል።

ወጣቱ ያሬድ መልካሙ ሕዝብ እያየ በአደባባይ ከተደበደበ በኋላ በጥይት መገደሉን ተከትሎ፣ የከተማው ሕዝብ ወጥቶ ተቃውሞ ማሰማቱን የአይን እማኞች ለዋዜማ ተናግረዋል።

በትናንትናው ዕለት እሁድ ደግሞ ቅዳሜ  ከተገደለው ወጣት ስርዓተ ቀብር በኋላ ሕዝቡ በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ተቃውሞ አሰምቷል።

በተቃዎሞ ላይ በርካታ ሕዝብ አደባባይ ማውጣቱን የሚያመላክት ተንቀሳቃሽ ምስል ዋዜማ ከስፍራው ደርሷት ተመልክታለች።

በእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች ከአካባቢው እንዲወጡና ለተገደሉት ሰዎች ፍትህ የሚጠይቁ መፈክሮች ተሰምተዋል።

የወጣቱን ግድያ ተከትሎ የተደረገው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የፌዴራል መንግሥት ሕግ እንዲያስከብር የተጠየቀበትም ነበረ ተብሏል። እንዲሁም “የማንነት ጥያቄ” በዚሁ ሰልፍ ላይ መነሳቱን ዋዜማ ከደረሳት መረጃ ተረድታለች።

ባለፈው ሳምንት በቦምብ ፍንዳታ ሰላማዊ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ሕዝቡ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም በተመሳሳይ አደባባይ ወጥቶ ነበር።

ሕዝቡ አደባባይ ከወጣ በኋላ በአካባቢው የተሰማራውን የአገር መከላከያ ሰራዊት አዛዞች በሃይማኖት አባቶች፣ በአገር ሽማግሌና ወጣት ተወካዮች በኩል የሕዝቡን ጥያቄ አድምጠዋል ተብሏል።

የተነሳው ዋና ጥያቄ “ታጣቂዎች ከተማ ውስጥ ገብተው ማኅበረሰቡን እያንገላቱት ነው ይውጡልን” የሚል መሆኑን ከተወካዮቹ መካከል እንዱ ለዋዜማ ገልጸዋል።

የትግራይ ኃይሎች በማኅበረሰቡ ላይ ዘረፋ፣ ድብደባ፣ ዛቻና ስወራ ከመፈጸም አልፈው ሰዎችን መግደላቸው በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ዋዜማ ያነጋገርናቸው ተወካዮች ጠቁመዋል።

ዋናው ጥያቄያቸው የፌዴራል መንግሥት የትግራይ ታጣቂዎችን እንዲያስወጣላቸው መሆኑን የገለጡት ተወካዩ፣ አፋጣኝ መፍትሔ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከአላማጣ አካባቢ የተወሰኑ የትግራይ ታጣቂዎችን መውጣታቸውን ገልጠው ነበር። 

ምንም እንኳን ጌታቸው የተወሰነ ኃይል አስወጥተናል ቢሉም፣ ታጣቂዎቹ ከተማ ላይ ገብተው ትምህርት ቤት ካምፕ አድርገው ተቀምጠዋል ተብሏል። ታጣቂዎቹ ወደ አካባቢው ከገቡ በኋላ ትምህርት ተቋርጦ ተማሪዎች ቤት መዋላቸውን ተገልጧል።

የትግራይ ኃይሎች አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ የጤና አገልግሎትን ጨምሮ መንግሥታዊ አገልግሎቶች ከተቋረጡ ሁለት ወር ገደማ ተቆጥሯል። 

በግጭቱ ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ እንዲሁም ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች የተጠለሉ ዜጎች በብዛት አልተመለሱም ተብሏል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ቃል አቀባዮች ለጉዳዩ መልስ እንዲሰጡን ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። [ዋዜማ]

The post በራያ አላማጣ በትግራይ ታጣቂዎችና ነዋሪዎች መካከል ውጥረት ተባብሷል፤ ሶስት ሰዎች ተገድለዋል first appeared on Wazemaradio.

The post በራያ አላማጣ በትግራይ ታጣቂዎችና ነዋሪዎች መካከል ውጥረት ተባብሷል፤ ሶስት ሰዎች ተገድለዋል appeared first on Wazemaradio.

Source:: https://wazemaradio.com/%E1%89%A0%E1%88%AB%E1%8B%AB-%E1%8A%A0%E1%88%8B%E1%88%9B%E1%8C%A3-%E1%89%A0%E1%89%B5%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%8B%AD-%E1%89%B3%E1%8C%A3%E1%89%82%E1%8B%8E%E1%89%BD%E1%8A%93-%E1%8A%90%E1%8B%8B%E1%88%AA/?utm_source=rss&utm_medium=rss&utm_campaign=%25e1%2589%25a0%25e1%2588%25ab%25e1%258b%25ab-%25e1%258a%25a0%25e1%2588%258b%25e1%2588%259b%25e1%258c%25a3-%25e1%2589%25a0%25e1%2589%25b5%25e1%258c%258d%25e1%2588%25ab%25e1%258b%25ad-%25e1%2589%25b3%25e1%258c%25a3%25e1%2589%2582%25e1%258b%258e%25e1%2589%25bd%25e1%258a%2593-%25e1%258a%2590%25e1%258b%258b%25e1%2588%25aa

Categories

A sample text widget

Etiam pulvinar consectetur dolor sed malesuada. Ut convallis euismod dolor nec pretium. Nunc ut tristique massa.

Nam sodales mi vitae dolor ullamcorper et vulputate enim accumsan. Morbi orci magna, tincidunt vitae molestie nec, molestie at mi. Nulla nulla lorem, suscipit in posuere in, interdum non magna.